Logo
FastMereja
ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT) የ9ኛ ዙር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ!
#fastmereja I በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የላቀ የሰው ኃይል በማፍራት ቀዳሚ የሆነው ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)፤ 350 ወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በኦሮሚያ ባህል ማዕከል አዳራሽ ታላላቅ የክብር እንግዶች፣ የቴክኖሎጂ መሪዎች እና ወላጆች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ ላለፉት ወራት በተግባር የታገዘ (Project-Based) ከፍተኛ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ ሲሆን፣ በገበያው እጅግ ተፈላጊ በሆኑት የሚከተሉት ዘርፎች በቂ ክህሎት እና እውቀት ጨብጠዋል፡-

✅ Full-Stack Web Development (ዌብሳይትና ሲስተም ልማት)
✅ Python & Data Science (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዳታ ሳይንስ)
✅ Mobile App Development (የሞባይል መተግበሪያ ልማት)
✅ Cyber Security (የሳይበር ደህንነት)
✅ Digital Marketing & Graphics Design
✅ Video Editing & Basic Computer Skills…

በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ተወካይ አቶ ኪዳኔ ይብጌታ፤ "ዓለም አሁን የምትመራው በቴክኖሎጂ ነው። እኛ ሀገር ቡና ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ እንደሚገኘው ሁሉ፤ እነዚህን ብቁ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለአለም ገበያ በማብቃት (Exporting Talent) ለሀገራችን የዲጂታል ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆን እንችላለን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት እና ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙት ዶ/ር ቢላል ከማል በበኩላቸው፤ "የወደፊቱ ጊዜ የ AI እና የዳታ ነው። ዛሬ የተመረቃችሁ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር (Digital Ethiopia 2030) ወሳኝ ሚና ትጫወታላችሁ" በማለት አደራ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ከአሪፍ ፔይ (ArifPay) እና ከአዲስ ቬሪፋይ (Addis Verify) የተጋበዙ የዘርፉ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በፓናል ውይይት ተሳትፈው ለተመራቂዎች የህይወት እና የሙያ ልምዳቸውን አካፍለዋል።

ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)፤ "ቴክኖሎጂን ከእውቀት ወደ ተግባር" በሚል መሪ ቃል፤ የሀገራችንን ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ለተመራቂዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ! የወደፊት የሥራ ዘመናችሁ የስኬት እና የፈጠራ ይሁንላችሁ!

📍 ሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MiT)
"ነገን ዛሬ እንገንባ!"

📞 +251 987 14 3030
🌐 www.mizantechinstitute.com

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.