አርትስ ፕላስ እና ተራኪ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን አጋርነት መስረቱ
#ethiopia | አዲስ አበባ - አርትስ ፕላስ የድምፅ መጻሕፍትን ለአድማጮች በማቅረብ ከሚታወቀው ተራኪ መተግበሪያ ጋር የይዘት ስምምነት ተበየነ። ይህ ስምምነት በተራኪ መተግበሪያ ላይ የሚገኙ የድምፅ መጻሕፍትን በአርትስ ፕላስ በኩል ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።
ተራኪ መጻሕፍትን በድምፅ በማቅረብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኘ ሲሆን፣ በዚህ ትብብር አማካኝነት ይዘቶቹን ለተጨማሪ ተጠቃሚዎች ማቅረብ ያስችለዋል።
በትብብሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ በተራኪ የሚገኙ የልጆች የድምፅ መጻሕፍት በአርትስ ፕላስ መተግበሪያ ላይ ይቀርባሉ። እነዚህ ይዘቶች በአርትስ ፕላስ ኪድስ ምድብ ስር የሚስተናገዱ ሲሆን፣ ለሕፃናት እና ለታዳጊዎች በጎ ሥነ ምግባርን፣ እውቀትን እና የፈጠራ ክህሎትን የሚያጎለብቱ ይሆናሉ።
የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ይህ አጋርነት የሀገሪቱን የኪነ ጥበብ እና የፈጠራ ዘርፍ ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
አርትስ ፕላስ በቅርቡ አገልግሎቱን በይፋ የሚጀምር ሲሆን፣ በሂደቱ ስለሚካተቱ መጻሕፍት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ወደፊት ይፋ ይደረጋሉ።
ድረ ገጽ https://artsplus.tv/
አንድሮይድ https://play.google.com/st...
አይኦኤስ https://apps.apple.com/app... #artsplus #teraki #audiobooks #ethiopianliterature #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 day ago