የአባቴን ቤት እሸጣለሁ እንጅ አልቆምም!!
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ መስራችና ባለቤት አሰፋ ጎሳዬ
#ethiopia | ሽቅርቅሪት ቅዳሜ ላይ ቆመን ዕለቷን ያስናፍቋት ስለነበሩት አንዷ "አዲስ አድማስ" ጋዜጣ ትንሽ ብናወራስ!?
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ህልው ሆኖ ወደ አንባቢ የመጣው በወርሃ ጥር 1991 አ.ም የዛሬ 26 አመት ግድም ነበር።
አዲስ አድማስ የንባብ ዐውዱን ከመቀላቀሏ በፊት ይዘትና ቅርጿን በተመለከተ ብዙ ዝግጅት፣ ብዙ ጥንቃቄ፣ ብዙ ምክክር፣ ብዙ ሙያዊ ርብርብ ተደርጎባታል። ይህንን ጥንቃቄና ዝግጅት አሳምረው የሚያውቁት ባለቤቷ አሰፋ ጎሳዬና ጓደኞቹ ጋዜጣዋን "እንከን የለሽ" በሚል እርግጠኝነት የንባብ ዐውዱን ቢቀላቀሉም፤ እንደታሰበውና እንደተለፋበት ያህል ግን ወዲያው ምላሽ አላገኘም። ይልቁንም በሸክም የወጣው ጋዜጣ በሸክም እየተመለሰ፤ በጋዜጣው ዝግጅት ላይ የአቅም አቅማችንን እንተጋ የነበርነውን ሁሉ ልብ የሚያርድ ሁኔታ ተፈጠረ።
እንዴት? ለምን? በሚል ግራ መጋባት ራሳችንን እስከመጠራጠር አደረሰን!
ከዚህ የተነሳም 'ቢሆን፣ ቢደረግ፣ የምንለውን ሃሳብ እያነሳን እየጣልን ተነጋገርን። ብዙዎቻችን ከአንባቢው አለመብሰልና ፈጣን መረጃ ፈላጊነት እንጅ በይዘቱ አንዳች እንከን እንደሌለው እንገምታለን።
ከይዘት ባሻገር አውጥተን አውርደን ቶሎ ተቀባይነት እንዳያገኝ እንቅፋት የሆነበት ሌላው ምክንያት 'ቅርፁ ሊሆን ይችላል' በሚል ግምት ባልተለመደው ብርቱካናማው የስያሜው ቀለም መደብና የጽሑፉ ቅርፅ ላይ አተኮርን። እናም አሰፋን "በቃ ችግሩ ይሄ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ስያሜና ጽሑፍ ሊሆን ስለሚችል እንቀይረው" አልነው። አሰፋም ያቺን ሽራፊ ፈገግታውን እያሳዪን "በመቃብሬ ላይ" በፈረንጅ አፍ On my dead body ወዶ ሳይሆን ተገዶ ይለምዳታል አለን።
"ኪሳራውስ?" ብንለው "የአባቴን ቤት እስኪያስሸጠኝ ሊቀጥል ይችላል እንጅ አላደርገውም" አለን!
አሰፋ "ስኬትህን በመዳፍህ መጨበጥ ካሻህ በያዝከው ነገር ፀንተህ ግፋ፤ እንዳትዝልም ፀንተህ ወጥር Push and Persist" የሚባለው ጽንሰ-ሃሳብ ቀድሞ የገባው ነበር። እናም እንዳለው ሆነ "አዲስ አድማስ" በይዘቱም ይሁን በዝግጅቱ በየሳምንቱ በጉጉት የሚጠበቅና የሚነበብ ተወዳጅ ጋዜጣ ለመሆን በቃ!!
ዛሬ ይህንን ከ26 አመታት በፊት የሆነ ትውስታ ያስመዘዘኝ ትላንት ያነበብኩት የ ናፍቆት ዮሴፍ የቁጭትና መብሰክሰክ ጽሑፍ ነው።
እናም ከእሷ ቁጭትና መብሰክሰክ ተነስቼ "እውን አሰፋ በህይወት ቢኖር አዲስ አድማስ ከህትመት ትወጣ ነበር?" ብዬ እንዳስብ አድርጋኝ ነው!
ሞት ቀደመው እንጅ አሴ ቢኖርማ እንኳን ጋዜጣው ሊቆም ይቅርና ዛሬ በሀገራችን ቁጥር አንድ የሚባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስም "አዲስ አድማስ ቲቪ" የሚባል በሆነ ነበር!!
ቸር ቀዳሚት ትሁንላችሁ! #addisadmas

1 year ago