Logo
FIDEL POST NEWS
ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ

ነገ ለ25ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ይካሄዳል። በዚህም ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።

ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
- ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
- ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
- ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
- ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት  (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
- ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት  አደባባይ)
- ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
-  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)
- ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ) ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ይዘጋሉ።

በተገለፁት መስመሮች ላይ ከዛሬ ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ፖሊስ አሳውቋል።

ለውድድሩ ተሳታፊዎች ፦ " ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ " ሲል ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

ማሳሰቢያ ፦ ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳስቧል።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 0111110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም ይቻላል።

AddisAbabaPolice
9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.