በምሽት ክበብ ውስጥ በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገለጸ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ቱሉ ዲምቱ በሚገኝ ሆልስቴ ሆቴል ውስጥ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ በሰዎች መካከል ጠብ ተነስቶ ነበር።
በዚህ ግጭት ወቅት አቡሽ ባዩ የተባለ ግለሰብ በሽጉጥ ተመትቶ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደታወቀው ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 12 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን በስፋት እየገፋበት ይገኛል።
ከተያዙት ግለሰቦች መካከል በፀቡ ላይ በቀጥታ የተሳተፈ አንድ ሰው፣ ከዋናው ገዳይ ጋር አብሮ ሲዝናና የነበረ ሌላ ተጠርጣሪ እንዲሁም ለግጭቱ መነሻ እንደሆነች የተጠረጠረች አንዲት አስተናጋጅ ይገኙበታል።
በወቅቱ በነበረው አለመግባባት ሳቢያ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸመው ግለሰብ ሟች ታጥቆት የነበረውን ሽጉጥ ቀምቶ እንደተኮሰበት የሚያሳዩ ፍንጮችን ማግኘቱን ፖሊስ ጠቁሟል።
የጉዳዩን ዝርዝር የምርመራ ውጤት ወደፊት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
በሌላ በኩል ፖሊስ ከዚህ ድርጊት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የከተማዋን ነባራዊ የሰላም ሁኔታ የማይገልጽ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል።
ህብረተሰቡ የሀሰት ወሬዎችንና አሉባልታዎችን ወደ ጎን በመተው ትክክለኛውን መረጃ ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ የመቀበል ልምዱን ሊያሳድግ እንደሚገባ ያሳሰበው መምሪያው፣ የስጋት ድባብ ለመፍጠር የሚሰሩ አካላትን በተባበረ ክንድ ለማክሸፍ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ
#addisababapolice #crimeinvestigation #ethiopiannews #security #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago