በጥናት ላይ በተመሠረተ ኦፕሬሽን የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ሀሠተኛ ሠነዶችን ማዘጋጀት፣ ማሠራጨትና መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ህገ ወጥ ድርጊት የሚገቡ ግለሠቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተደረገም ይገኛል። በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጎማ ቁጠባ ፖሊስ ጣቢያ በክ/ከተማው ወረዳ 7 ቀጠና 1 አካባቢ ሀሠተኛ ሠነዶችን በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ የወንጀለኞች ጥናት አድርጓል።
ፖሊስ ጥናቱን መነሻ በማድረግና የፍርድ ቤት የቤት መበርበሪያና የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ
👉ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ፣
👉ፖስፖርት፣ የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎች፣
👉የ10ኛና የ12ኛ መልቀቂያ
👉የትግራይ ክልል መታወቂያ
👉የአማራ ክልል መታወቂያ
👉የየአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ፣
👉የተሽከርካሪ ቦሎ፣
👉የተለያዩ ሪሲቶች፣
👉የልደት ካርድ፣
👉ሊሰራ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ መታወቂያ፣
👉የፖለቲካ ጥገኝነት ለሚጠይቁ ግለሰቦች የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እነዚህኑ ሠነዶች ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው፦
👉1018 የተለያዩ ማህተሞች፣
👉1 ፕሪተር፣
👉1 ህትመት ማሽን፣
👉2 ላፕቶፕ ፣
👉2 ስካነር፣
👉1አጉሊ መነፅር፣
👉2 ማሸጊያ ማሽን፣
👉8ሲዲዎች፣
👉1 መጠረዣ፣
👉1የፖስፖርት ማሽን፣
👉11የማህተም መርገጫ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።
ህብረተሠቡ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛና ትውልድ ገዳይ መሆኑን ተረድቶ መሠል ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ተሳትፎውን እንዲያጎለብት የአዲሰ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ተቋማትም ሠራተኞችን በሚቀጥሩበት ወቅት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸው ላይ ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርጉም ጠቅላይ መምሪያው መልዕክቱን ያስተላልፋል።
Addisababapolice

1 year ago