4 months ago
የ3.8 ሚሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ኬብል የዘረፉ ግለሰቦች ተያዙ!
#ethiopia | የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን፣ በመሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ከዘረፉት ንብረት ጋር በቁጥጥር ስር አውሏል።
የተያዘበት ቦታ፦
በየካ ክፍለ ከተማ፣ ኮተቤ ኪዳነ-ምህረት አካባቢ።
የንብረቱ መጠን፦
4 ሺህ 895 ሜትር የኤሌክትሪክ ኬብሎች (ABC እና UG) እንዲሁም 350 ኪ.ግ የሚመዝኑ አልሙኒየምና መዳቦች።
ግምታዊ ዋጋ፦
የተያዙት ንብረቶች በአጠቃላይ 3 ሚሊዮን 895 ሺህ 81 ብር ያወጣሉ ተብሏል።
የተወሰደው እርምጃ፦
ፖሊስ ምስክሮችን በማቅረብ ጉዳዩ በአፋጣኝ በፍርድ ቤት እንዲታይ ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ኬብሎቹ ከየትኛው አካባቢ ተዘርፈው እንደመጡ ለማወቅ ጥልቅ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል።
አሳሳቢ መልዕክት፦
እንዲህ ያሉ የስርቆት ወንጀሎች ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ ከመዳረጋቸው ባለፈ፣ ደንበኞችን ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና ለደህንነት ስጋት እየዳረጉ በመሆኑ ማህበረሰቡ መሰል አጠራጣሪ ድርጊቶችን ሲመለከት በፍጥነት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
#getu #crimealert #addisababapolice #electricinfrastructure #cabletheft #yeka #kotebe #ethiopiaelectricutility #lawenforcement #አዲስአበባ #ፖሊስ #መሠረተልማት #ስርቆት #የካ #ኮተቤ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
"ዜንጦ" ሌቦች : በጠራራ ፀሐይ
በአዶርሰም ሕንፃ የተፈጸመው አስደንጋጭ ዝርፊያ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኘው አዶርሰም ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ፣ እነዚህ በፎቶው የሚታዩ የተደራጁ ወጣቶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች ዘርፈው ተሰውረዋል።
የተዘረፉ ንብረቶች፦
ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ታብሌቶች፣ የፎቶና ቪዲዮ ካሜራዎች እንዲሁም የስልክ መሣሪያዎች።
የሌቦቹ ሙከራ፦
የቢሮውን የደህንነት ካሜራ መረጃ (Footage) ለማጥፋት ቢሞክሩም፣ በሌሎች የደህንነት ካሜራዎች በግልጽ ሊታወቁ ችለዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአድዋን ድል በሚያከብርበት ዕለት በጠራራ ፀሐይ ነው።
የጥቆማ ጥሪ፦
እነዚህን ግለሰቦች የምታውቁ፣ ያያችሁ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ ዝርፊያ የተፈጸመባችሁ ወገኖች ጥቆማ በማድረግ እንድትተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
ጥቆማ ለሚያደርሱ ወገኖች ወሮታ ይከፈላል።
ጥቆማ ለማድረስ፦
ፖሊስ ጣቢያ፦ ቦሌ አደይ አበባ ፖሊስ ጣቢያ
ስልክ፦ 0988188890 ወይም 0907247454
እባክዎ ሌቦቹን ለሕግ ለማቅረብ እንዲቻል ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ይተባበሩ!
#addisababa #bole #crimealert #securitycamera #ethiopia #theftalert #adwavictoryday #communitysafety #አዲስአበባ #ቦሌ #ዝርፊያ #ጥቆማ #ሌቦች

Comments