30 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዳላስ ከተማ በተካሄደው የሪፐብሊካን ፓርቲ ታሪካዊ የምርጫ ቅስቀሳ መድረክ ላይ ያልተጠበቀ ቃል በመግባት አሜሪካውያንን አስገርመዋል። ትራምፕ በንግግራቸው፣ በመጪው የህዳር ወር አጋማሽ ምርጫ (Midterm election) ሪፐብሊካኖች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን እና ሴኔቱን ካሸነፉ፣ ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ አዋቂ ዜጋ 5,000 ዶላር በ«ትራምፕ ዲቪደንድ» ስም እንደሚከፍሉ ቃል ገብተዋል።
ይህ ክፍያ ከአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ስኬት እና ከውጭ ምርቶች ላይ ከሚሰበሰበው የታሪፍ ገቢ የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ክፍያ ባለፈው ዓመት ለወታደሮች ከተሰጠው የ1,776 ዶላር ክፍያ ጋር አመሳስለውታል። ሆኖም ይህ ክፍያ ኮንግረሱ ሊያጸድቀው ይገባል ወይ የሚለው ላይ ግልጽ መረጃ አልሰጡም። ከንግግራቸው በኋላ ዴሞክራቶች እርምጃውን በመጪው ምርጫ የሚጠብቃቸውን ሽንፈት ለማስቀረት የተደረገ "ተስፋ የቆረጠ ሙከራ" ሲሉ አጣጥለውታል።
የትራምፕ የ5 ሺህ ዶላር ክፍያ ቃል ትልቅ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክርክር አስነስቷል። በኢኮኖሚው በኩል፣ ይህን ያህል ገንዘብ ለ245 ሚሊዮን አዋቂ አሜሪካውያን ማደል ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ቀድሞውንም በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለውን የአሜሪካን የዋጋ ግሽበት በእጅጉ ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት በኢኮኖሚስቶች ዘንድ አሳድሯል። በፖለቲካው መስክ ደግሞ፣ ይህ ድርጊት መራጮችን በገንዘብ ለመደለል እንደተደረገ የስልጣን ማቆያ ስልት እና "ድምጽ የመግዛት ሙከራ" (Vote buying) ተደርጎ እየተተቸ ይገኛል። በታሪክ እንደሚታየው፣ በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዝዳንት ፓርቲ በአጋማሽ ምርጫ ብዙ መቀመጫዎችን ያጣል፤ ትራምፕም ይህን ታሪካዊ ሽንፈት ለመቀልበስ የፈጠሩት አዲስ ስትራቴጂ ይመስላል።
ትራምፕ የገቡት የ5 ሺህ ዶላር ቃል ፖለቲካዊ ትኩረት ለመሳብ የተወረወረ ትልቅ ካርድ ቢሆንም፣ በተግባር ላይ መዋሉ ግን እጅግ አጠራጣሪ ነው! ኮንግረሱ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል ውሳኔ በቀላሉ የሚያጸድቀው አይሆንም። በመሆኑም ይህ ቃል ከአሜሪካውያን የኑሮ ውድነት ጭንቀት ጋር በመጫወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የተደረገ ስልት መሆኑን መረዳት ይገባል!

1 month ago
''ድንጋይ ብላ'' ስድብ አይደለም
#ethiopia | ሁናጉንዲ የተባለው ግለሰብ ገና ከ10 ዓመት እድሜው ጀምሮ ጡብ፣ አፈርና ድንጋይ የመመገብ እንግዳ ልማድ በማዳበሩ የብዙዎችን ቀልብስቧል።
ከዓመታት በፊት የጡብ ስብርባሪዎችንና ጠጠሮችን ሲመገብ የሚያሳይ መረጃ ይፋ ከሆነ በኋላ ታሪኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ሲሆን ቤተሰቦቹ ይህንን ጎጂ ልማድ እንዲተው ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም ሊያቆም አልቻለም።
እንዲያውም ከተለመዱ የምግብ አይነቶች ይልቅ አፈርን እንደሚመርጥ የሚናገረው ፓኪራፓ ይህ ያልተለመደ ባህሪው በመላው ዓለም የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገልጹት ከምግብ ውጭ ያሉ ቁሳቁሶችን የመመገብ ስሜት "pica'' ከሚባል የጤና መታወክ ጋር የተያያዘ ነው።
ምንም እንኳን ፓኪራፓ ይህ ልማዱ ምንም አይነት የጤና ችግር እንዳላስከተለበት ቢናገርም፣ ጡብ፣ ድንጋይ ወይም የተበከለ አፈር መመገብ ጥርስን ከመጎዳቱም በላይ ለምግብ ፍጨት ችግሮች ሊዳርግ ስለሚችል ከፍተኛ አደጋ አለው ተብሏል።
የፓኪራፓ ታሪክ ያልተለመደና አስገራሚ ቢሆንም ከምግብ ውጭ ያሉ ነገሮችን አብዝቶ መፈለግ ወይም መመገብ ከተሸፈነ የጤና ችግር ጋር የተያያዘ ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያሳያል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
በመኰንን ሸገኔ ስም ሽልማት ተሰየመ
(ከዕዝራ እጅጉ)
#ethiopia | በርካታ ተማሪዎችን ባፈሩት ፣ ከ 50 አመት በፊት ሕይወታቸው ባለፈው በመምህር መኮንን ሸገኔ ስም ሽልማት ተሰየመ።
የአርአያ ሰው ሽልማት ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ዲያቆን ፍሬው ሰይፉ ለተወዳጅ ሚድያ እንደተናገሩት በየዓመቱ በሚሰጠው የአርአያ ሰው ሽልማት ላይ ዘንድሮ ነሐሴ 16 2018 ዓ.ም በተደረገው ሥነ ሥርዓት ሽልማቱ መታሰቢያ የተደረገው ለመምህር መኮንን ሸገኔ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በየአመቱ 'የመኮንን ሸገኔ ሽልማት' በሚል ዘርፍ ለተለያዩ ሰዎች እውቅና እንደሚሰጥ ታውቋል።
የሽልማት ሥነሥርዓቱ ቅዳሜ ነሐሴ 16 2018 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ የተደረገ ሲሆን የመኮንን ሸገኔ ቤተሰቦችም በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
የአባቷን ታሪክ በማፃፍና ለቁምነገር እንዲበቃ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣችው ልጃቸው ካቢው መኮንን ሸገኔ ስትሆን የዛሬ አመት በሰኔ 2017 ዓ.ም መኮንን ሸገኔ የሀገር ባለውለታ" የሚል መጽሐፍ በዕዝራ እጅጉ ተፅፎ መመረቁ ይታወቃል።
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ጨምሮ በርካታ ምሁራንን ለወግ ማዕረግ ያበቁት መምህር መኮንን በአገር ውስጥ እና በባህር ማዶ በሚገኙ ተማሪዎቻቸው ዘንድ የሚወደዱ እና የሚከበሩ እንደሆኑ ይታወቃል።ተማሪዎቻቸውም በዕለቱ የማስታወሻ ስጦታ ለቤተሰቡ እንዳበረከቱ ታውቋል።
መኰንን ሸገኔ፣ የዛሬ 49 ዓመት ሕይወታቸው ያለፈ የዳግማዊ ምኒሊክ፣የድሬደዋ ልዑል መኰንን ፣እና የአዲስ አበባ ልዑል መኰንን ትምህርት ቤቶች ርዕሰ- መምህር የነበሩ ሲሆን በሥራ ላይ ሳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።
ህይወታቸው ሲያልፍ ገና የ5 ዓመት ልጅ የነበረችው ካቢው መኮንንም አባቴ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያዊያን አባት ነው ብላ በማመን ስለ አባቷ ለትውልዱ አንድ አሻራ ለማኖር መነሳቷን ትናገራለች። የአርአያ ሰው ሽልማትም ለመኮንን ሸገኔ ለሰጠው ዕውቅናም ምስጋናዋን አቅርባለች።
በዳላስ በተደረገው የእውቅና ሥነ -ሥርዓት የመኮንን ሸገኔ ቤተሰቦችን ጨምሮ ከተለያዩ ክፍለ -ግዛቶች የመጡ የቀድሞ ተማሪዎች ታድመዋል።
በዳላስ የተሰጠው የአርአያ ሰው ሽልማት ከተመሠረተ 10 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን' እናቀዳድማለን እንጂ አናወዳድርም' የሚለውን መርህ አንግቦ ዘንድሮ ለአገር ባለውለታዎች እውቅና ሰጥቷል። በዕለቱ ሌሎች 9 ባለውለታዎችም በአርአያ ሰው የሽልማት ፋውንዴሽን ዕውቅናው የተበረከተላቸው ሲሆን መርሀ ግብሩም በልዩ ድምቀት እንደተሰናዳ በዳላስ የሚገኘው የተወዳጅ ሚድያ ዘጋቢ አስታውቋል።
ዘጠኙ ዕውቅና የተበረከተላቸው ሰዎች ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ (ላገር በሰሩት ሥራ የኮሎኔል ካሣ ገብረማሪያምን ሽልማት አገኙ)፣ ሐጂ ራህመቶ ሙክታር (የክብር ተሸላሚ፣አርቲስት የትናየት ታምሩ በኪነጥበብ ዘርፍ ፣አቶ ተስፋልደት በላይ ተክሉ የአባታቸውን ሌጋሲ በማስቀጠል፣የቲ እሳቱ፣አኒሳ አደም፣ቶማስ አበበ፣በማህበራዊ ኃላፊነት መወጣት ሲሸለሙ ማህደር ገብረሥላሴ የአመቱ ምርጥ ሬስቶራንት ዘርፍ አሸንፋለች። በተጨማሪም ሊያ ስዩም የህይወት ዘመን ሽልማት ስታገኝ ህፃን ካሳ ሀይሉ ደግሞ ተስፋ የተጣለበት ዘርፍ ላይ ዕውቅናው እንደተበረከተለት ታውቋል።ከተቋማት ደግሞ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ስትሪም ኦፍ ሆፕ በዕለቱ ተመስግኗል።
#የአርአያሰውሽልማት #መምህርመኮንንሸገኔ #ዳላስ #ትምህርት #ዕውቅና #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጠበቃ ሳሮን በርሄ እንዳረጋገጡት፣ በአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ቁጥጥር ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙት የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ (UMD) የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር ዶክተር ብርሃኑ ክብረት በዋስ እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። ጠበቃ ሳሮን ለባልቲሞር ባነር እንደተናገሩት፣ ዓርብ ዕለት በተካሄደው የፍርድ ቤት ውሎ ደንበኛቸው ዶክተር ብርሃኑ በዋስትና ሊለቀቁ ይገባል በማለት አጥብቀው ቢከራከሩም፣ ዳኛው ግን ጥያቄያቸውን አልተቀበሉትም። ለቀረቡት ማስረጃዎች ተገቢው ሚዛን አልተሰጠም ያሉት ጠበቃዋ፣ ከቀረበው አጠቃላይ መዝገብ አንጻር የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት የሌለው ነው በማለት ተችተዋል።
ዶክተር ብርሃኑ የትምህርት ዘርፉን "የዓመቱ ምርጥ መምህር" ሽልማት ከተቀበሉበት የፋርማሲ ኮሌጆች ማህበር ስብሰባ ሲመለሱ፣ ባለፈው ጁላይ 21 ቀን በዳላስ ፎርት ዎርዝ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መያዛቸው ይታወሳል። የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች ዶክተር ብርሃኑ ህጋዊ የስራ ፈቃድ እንዳላቸው በማረጋገጥ፣ ከሁኔታው ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በፍጥነት ተፈትተው ወደ ፋርማሲ ትምህርት ቤቱ መደበኛ ስራቸው እንደሚመለሱ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም መምህሩ በኦክላሆማ በሚገኝ የማቆያ ማዕከል ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ በበኩሉ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር ብርሃኑ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙት በህገወጥ መንገድ መሆኑን አሳውቋል። ተቋሙ ባወጣው መግለጫ፣ ግለሰቡ እ.ኤ.አ ሰኔ 21 ቀን 2021 ወደ ሀገሪቱ የገቡ ሲሆን፣ ቪዛቸው ግንቦት 31 ቀን 2024 ማብቃቱን እና ሀገሪቱን ለቀው ባለመውጣታቸው የኢሚግሬሽን ሂደታቸው እስኪጠናቀቅ በእስር እንደሚቆዩ አስታውቋል። መምሪያው "በእስር መቆየት ምርጫ ነው" በማለት፣ በህገወጥ መንገድ በሀገሪቱ የሚገኙ ሰዎች በፈቃዳቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስችለውን የሞባይል መተግበሪያ (CBP One app) እንዲጠቀሙ አሳስቧል። ለዚህም በራሳቸው ለሚመለሱ ሰዎች የ2,600 ዶላር እና የነጻ የአውሮፕላን ትኬት እንደሚቀርብላቸው መምሪያው ጠቁሟል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገር መከላከያ ፀሀፊ ለሆኑት ፒት ሄግሴዝ፣ አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር በየዓመቱ የምታደርገውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንሱት ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ትራምፕ በእሁድ እለት በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ እንዳሰፈሩት፣ አሜሪካ ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ መስማማቷ እጅግ እንዳላስደሰታቸው በግልጽ ተችተዋል።
ለዚህ አወዛጋቢ ውሳኔ ፕሬዝዳንቱ ሁለት ዋና ዋና መነሻዎችን አንስተዋል። የመጀመሪያው የደቡብ ኮሪያ የዲፕሎማሲ አቋም ሲሆን፣ አሜሪካ ኢራንን ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነፃ ለማድረግ በምታደርገው ጥረት እንድትተባበር ለቀረበላት ጥያቄ ሴኡል "አይሆንም" የሚል ምላሽ መስጠቷ ትራምፕን አስቆጥቷል። ሁለተኛውና ትልቁ ምክንያት ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ያላቸው "እጅግ መልካም" የሆነ ግላዊ ወዳጅነት ነው።
ትራምፕ ይህንን ወታደራዊ ልምምድ ሲተቹት፤ "እነዚህ ልምምዶች ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና በአብዛኛው በአሜሪካ የሚሸፈኑ ከመሆናቸውም በላይ፣ እኔ ስልጣን ላይ እስካለሁ ድረስ ምንም አይነት ስጋት ላልፈጠረችብንና አክብሮት ላሳየችን ሀገር (ሰሜን ኮሪያ) ተገቢ ያልሆነ የጥላቻ መልዕክት የሚያስተላልፉ ናቸው" ብለዋል። ልምምዱን ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ አሁን ላይ ጊዜው ስላረፈደ፣ በምትኩ ግን የኦፕሬሽኑ መጠንና ስፋት በከፍተኛ ሁኔታ ተቀንሶ እንዲካሄድ ተወስኗል።
“ኡልቺ ፍሪደም ሺልድ” በመባል የሚታወቀውና ከኦገስት 17 እስከ 27 ሊካሄድ የታቀደው ይህ ወታደራዊ ልምምድ፣ በሁለቱ አጋር ሀገራት መካከል ያለውን ዝግጁነት ለማጠናከር ያለመ ነበር። ሆኖም ሰሜን ኮሪያ ይህንን የጦር ልምምድ "ለወረራ የሚደረግ የጦርነት ትዕይንት" ስትል አጥብቃ ያወገዘችው ሲሆን፣ ተቃውሞዋን በተግባር ለማሳየትም ባለፈው ሳምንት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ተኩሳለች። ሁኔታውን ለማርገብ በሚመስል መልኩ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር አብረው ያሉበትን ምስል ቅዳሜ እለት በማህበራዊ ሚዲያቸው በማጋራት "እኔ እና ኪም ጆንግ ኡን እጅግ በጣም እንግባባለን!" በማለት የሁለቱን ሀገራት ውጥረት ለማርገብ የፖለቲካ ካርዳቸውን ተጠቅመዋል።

(ዘ-ሐበሽ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ በተሰማራው የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ የሚገኙ ወታደሮችን የኑሮ ሁኔታ እና የአእምሮ ጤናን በተመለከተ የሚነሱ ስጋቶችን ውድቅ አደረጉ። ጋዜጠኞች የዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን (ወታደሮች ቤተሰቦች ስላሉበት ሁኔታ ተጨንቀው እንደሆነ ለጠየቋቸው ጥያቄ ፕሬዚዳንቱ "አይ፣ አልተጨነቁም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
መርከቧ በባህር ላይ ዘጠነኛ ወሯን የያዘች ሲሆን፣ ከተገቢው ጊዜ በላይ መቆየቷን በሚነሳው ሀሳብ ላይ ትራምፕ አልተስማሙም። "በፍጹም፣ ይህ በቂ አይደለም" ብለዋል። ይሁን እንጂ አሜሪካ ከኢራን ጋር በሆርሙዝ ስትሬት እና በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ዙሪያ ውጥረት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ ይህች መርከብ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ በሆነች ሌላ መርከብ በቅርቡ እንደምትተካ ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል። ትራምፕ ይህን ያሉት ዛሬ ኦገስት 14 ወደ አየር ሃይል አንድ ከመሳፈራቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።
የጦር ጉዳዮችን የሚዘግቡ ልዩ ሚዲያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የመርከቧን ባልደረቦች ቤተሰቦች ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ በሊንከን ላይ የኑሮ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መጥቷል። ከዚህም ባሻገር በርካታ ራስን የማጥፋት ሙከራዎች መኖራቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል። ይህንን ተከትሎ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ህግ አውጪዎች በሁኔታው ላይ ማጣራት እንዲደረግ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ግዙፏ የኒውክሌር ኃይል ተጠቃሚ መርከብ በህዳር 2025 ከካሊፎርኒያ ወደ ደቡብ ቻይና ባህር ያቀናች ቢሆንም፣ የካቲት 28 አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ አቅጣጫዋን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንድትቀይር ተደርጓል። በባህር ኃይል ትንተና ማዕከል የጥናት ኃላፊ የሆኑት ጆናታን ሽሮደን ለኤኤፍፒ (AFP) እንደተናገሩት፣ የዚህ አይነት መርከቦች አብዛኛውን ጊዜ የሚሰማሩት ለስድስት ወራት ብቻ መሆኑን እና ይህም የወታደሮቹን ደህንነት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
የቤተሰቦቹ ቅሬታ በሚዲያ መዘገቡ፣ በ2024ቱ ምርጫ አሜሪካን በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ውስጥ እንደማያስገቡ ቃል ገብተው ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡት ትራምፕ፣ ይህንን ጦርነት ለማስረዳት ለሚያደርጉት ጥረት ተጨማሪ ፈተና ሆኖባቸዋል። አሁን ያለው ግጭት የፕሬዚዳንቱን የድጋፍ መጠን ወደ ታች እያወረደው እንደሚገኝም ተዘግቧል።
ከወታደሮቹ ቤተሰቦች ከወጡት አሳሳቢ መረጃዎች መካከል ሁለት ወታደሮች ከመርከቧ ላይ ዘለው ለመግባት መሞከራቸው ይገኝበታል። የአሜሪካ ጦር ነሐሴ 3 ቀን አንድ ወታደር ባህር ውስጥ ወድቆ እንደዳነ ቢገልጽም፣ የአእምሮ ጤና ችግር መኖሩን ግን አስተባብሏል። አንድ ወታደራዊ ባለስልጣን በመርከቧ ላይ ራስን የማጥፋት ሀሳብም ሆነ ሙከራ መጨመሩን እንዳላስተዋሉ በመግለጽ፣ በአብርሃም ሊንከን መርከብ ላይ አምስት የሃይማኖት አባቶች፣ አንድ የስነ-ልቦና ባለሙያ፣ አንድ የማህበራዊ ሰራተኛ፣ አንድ የመከላከያ አስተባባሪ እንዲሁም የወታደሮቹን ሞራል ለመጠበቅ 'ካፕቴን ፋቶም' የተባለ ውሻ መኖሩን አብራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም፣ ከባህር ላይ ኑሮ ጋር መላመድ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ወታደሮችን የሚደግፉ ግብዓቶችን እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።

Sponsored by
Surafel
2 months ago
አሜሪካ የዓመቱ ምርጥ መምህር ካለች በኋላ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ኢትዮጵያዊው መምህር
#ethiopia | በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር በርሃኑ ገረሱ ክብረት ከአሜሪካ የፋርማሲ ኮሌጆች ማህበር የ"ዓመቱ ምርጥ መምህር" ሽልማት ተቀብለው በመመለስ ላይ እያሉ በዳላስ-ፎርት ዎርዝ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት እንደገለጸው ዶክተር በርሃኑ እ.ኤ.አ በሰኔ 2021 በሕጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ቢሆንም የተቀመጠላቸው የቪዛ ጊዜ እ.ኤ.አ ግንቦት 31 ቀን 2024 ካበቃ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አስታውቋል።
የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰበውና ዶክተር በርሃኑ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚወደዱና ውጤታማ መምህር መሆናቸውን ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በዊልያም ፓተርሰን ዩኒቨርሲቲ በሱሰኝነት መንስኤዎችና ሕክምና ዙሪያ በምርምር የሰሩት ዶክተር በርሃኑ ያለባቸው የቪዛ ስጋት በፍጥነት ተፈትቶ ወደ ተቋሙ ተመልሰው አጠቃላይ የማስተማርና የምርምር ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ተስፋ ማድረጉን አስታውቋል።

#ቤተልሔም_ሸረፈዲን - " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ ያላት "
( የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ )
**********************************************
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
#በመጨረሻም ፦ ጽሑፉ ለፌስቡክ ረጅም ( አረፍ አረፍ እየተባለ ተነቦ የሚያልቅ ) ነው ። አጥሮ ሁሉም ጋ ከሚደርስ ረዝሞ የሚመለከታቸውና የሚያስፈልጋቸው ቢያነቡት መርጬ ነው ። ሆነ ብዬ ነው ማለት ነው ። ይሁን ። እንግዲህ እያረፋችሁም ፣ እያለፋችሁም አንብቡት ።
ለግጥምም ፣ ለዜማም አልፎ ሂያጅ ነኝ። ( በተለይ ) ለግጥም አልፎ ሂያጅ መሆኔ ያስቆጨኛል ። ግጥም ምኞቴ ነው ፤ ጉድለቴም ። ማንም እንደሚሰማውና እንደሚረዳው ነኝ ። አዚያዚያምን መረዳትም ላይ ጨዋ አላዋቂ ነኝ ። ቤተልሔም ሸረፈዲን " ደስተኛ " ብላ ስለሰየመችው አዲሱ አልበሟ የተሰማኝን ልላችሁ ነው ዳር ዳር የምለው ።
እኔ የምለው ፣ ቤተልሔም ሸረፈዲን ግን ስንት ዓመቷ ነው ? በቅርቡ ትንሽ ልጅ አልነበረችም እንዴ ? ከመቼው አደገች ? ከምኔው አብባ አፈራች ? አልበሟ በተለቀቀበት " ኩራ ስትሪም " ላይ ገጣሚው ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) እንደ ገጣሚነቱ ቃላት ቆጥቦና ሀሳቡን አስውቦ " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ አላት
" እንዳላት ሆና ነው የመጣችው ። የጥበብ ስራ አመዛኙን ሁለቱን ይፈልጋል ። እውቀትም ፣ ተሰጥዖም በዝቶ ኖሯቸው የትም ሳይደርሱ የቀሩ " እገሌ ፣ እገሌ " የምንላቸው ጥቂት የማይባሉ የጥበብ ሰዎች በየአልባሌው ወድቀው ቀርተዋል ። እስቲ እነዚህን ሰዎች አስቧቸው ። የህጻን ልብም ፣ የአዋቂ ጆሮም አታገኙባቸውም ።
10 ዘፈኖች የያዘው " ደስተኛ " አልበም ናትናኤል ግርማቸውና ታምሩ አማረ በጥምረት ፕሮዲዩስ ያደረጉት ነው ። ከጀርባቸው ደግሞ ከብዙ ጥበባትና የጥበብ ሰዎች ጀርባ ያለው ዘላለም ኩራባቸው " ኩራ ስትሪም " ን ይዞ አለ ። ቅንብሩን ፣ ሚክሲንግ እና አሬንጅመንቱን ታምሩ አማረ ፣ ግጥሞቹን ( በሙሉ ) ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) ፣ " ባለቤቴ " እና " እንዴት " ዜማዎችን ዮሴፍ በቀለ ( ጆ ) ፣ " አይታለፍም " ዜማ እሱባለው ይታየው ( የሺ ) ፣ የቀሪዎቹን 7 ስራዎች ዜማዎች በምህረተአብ ደስታ ሲፈጠሩ ከእነዚህ ውስጥ የእበሙ መጠሪያ የሆነው " ደስተኛ " ን ዜማ ናቲና ምህረተአብ በጋራ ሰርተዋቸዋል ።
በአሁኑ ጊዜ አንድ ነጠላ ዜማ መስራት የምረቃ ፕሮግራም ያዘጋጃል ፤ ወዳጅ ዘመድ ያጠራራል ፤ " ሰይፉ በኢቢኤስ " ላይ ያስቀርባል ፤ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ አላስቆም አላስቀምጥ ያስብላል ። አልበም መስራት ( አድማጭ ያልተቀበለውም ቢሆን እንኳ ) እንደ አራሷ ሴት " ምጡን ተዪው ፤ ልጁን እዪው " እየተባለና የስቃዩ ጊዜ እየተረሳ እንጂ ደጋግሞ በስሜት ሞቶ መነሳት ነው ። የሚያገጫጭ ፣ የሚያነጫንጭ ፣ የሚያቀያይምንና " ሁለተኛ ብንገናኝ ! " የሚያባብል ነው ። የምጡ ጊዜ አልፎ ልጁ ሲታይ እየተረሳ ነው አንዱ ሙዚቀኛ ከሌላው ጋር የኖረው ። ቤተልሔም መልካሞችና ህልም ያላቸው ሙያተኞች እጅ ላይ አሳርፏት እንጂ ጀምሮ አለመጨረስ ፣ ወድቆ አለመነሳትም አለ ። ገና በመጀመሪያው አልበም ፣ በትንሽ እድሜ ፣ በጀማሪነት አረዳድ እንዲህ ያለ ስኬታማ አልበም መስራት ደጋግሞ የማያጋጥም ነው ። ህብስት ጥሩነህ እነ አየለ ማሞ ( ማንዶሊን ) እና ታንጎ ሙዚቃ ቤትን እንዳገኘችው አይነት እድለኛነት ይጠይቃል ። የናቲ እና ታምሩ ጥምረት ደግሞ የእነ ኤሌክራትን እና አምባሰልን ዘመን ያስታውሰናል ።
ናቲ " ኩራ ስትሪም " ላይ 4 ዓመት ስላለፈው " ደስተኛ " አልበም ሲናገር " አልበሙን ጀምረነው ባልነው ጊዜ ያልጨረስነው እኛ በዚያ ውስጥ እየተሰራን ስለነበረ ነው " ይለዋል ። ፕሮዲዩሰሮቹ በምን በምን እንደተሰሩ አላውቅም ። ቤተልሔምን ግን በእርግጥም ሰርተዋታል ። አፈሩን ቆፍረውና አልመው ፣ አቡክተው ቤተልሔምን እንደ ውቡ ሸክላ አስጊጠው ሰርተዋታል ። እሷ እንደምትለውም ትንሿ ቤተልሔም " ከብዙ ልምምድ በኋላ የመጣ አልበም " ባለቤት እንትሆን አድርገዋታል ። ቤተልሔም ሸረፈዲን የተባለች ጥንቅቅ ፣ ጥፍጥ ያለ ስራ ያላት ድምጻዊትን ለዘመኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ( ? ) አበርክተዋል ። አሁን የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ቤተልሔም ሸረፈዲን የምትባል ብስል ፣ ትክን ያለች ድምጻዊት አለችለት ። ቤተልሔም ስለ አዲሱ አልበሟ ለኩራ ስትሪም ስትናገር " ይሄን አልበም እንደ መጀመሪያም ፣ እንደ መጨረሻም ስራ አድርጌ ነው የማየው ። " ብላለች ።
ናትናኤል ግርማቸው ገጣሚነት ተሰጥቶታል ። ገጣሚነቱ የቃላት ድርደራ ሳይሆን የሀሳብ ስፋት የታደለው ነው ። ናቲን በራሄል ጌቱ " ኢትዮጵያዬ " ነው ያወቅኩት ። የራሷን የራሄል ጌቱን " ያገሬ ሰው " ፣ በኋላም " ወረት " ን ሰርቶ አስደንቆኛል ። ናቲን በራሄል ጌቱ ( በስራዎቿ ) በኩል ነው ያገኘሁት ። ይህ ሰው ነው ደግሞ ከታምሩ አማረ ጋር ሆኖ ቤተልሔም ሸረፈዲንን ያገኛት ። ሁለቱ በፕሮዲዩሰርነት ባይከሰቱ ቤተልሔም ሸረፈዲን ቢያንስ በዚህ ጊዜ አትወለድም ። የጀርባ አቅሟን ባላውቅም የ10 ግጥም ፣ የ10 ዜማ ፣ የ10 ዜማዎች ቅንብር ፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ክፍያን አትወጣውም ( ብዬ እገምታለሁ ) ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ዘላለም ኩራባቸውን አታገኘውም ። ዘላለም ኩራባቸው ወደ ሙዚቃ ማምረት ስራ ሲገባ ከገንዘብ የነፍስ ጥሪ ትርፉን አስቦ እንደሚሆን አምናለሁ ። ካሁን ቀደም በተናጠል ሲያደርግ የነበረውን ሙያውንና ሙያተኛውን እንደ ታላቅ ወንድም አጋር የመሆን ዝንባሌውን ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶት መምጣቱ ይመስለኛል ። ቤተልሔም እድለኛ ናት ። እነ ንዋይ ደበበ ፣ ሀመልማል አባተ ፣ ጸሐዬ ዮሀንስ እና ዘመንኞቻቸው በመጡበት መንገድ ነው የመጣችው ። ሌላም እድለኛነት ( ከችሎታ ጋር ) አላት ።እነ ጠረፍ ካሳሁን ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ለምለም ኃ/ሚካኤል ፣ ዘቢባ ግርማ ተሰርተው የወጡበት " የኛ " ፕሮጀክት ፣ የእነ አይዳ አሸናፊ እጅም አርፎባታል ።
ከአስሩ የ " ደስተኛ " አልበም ስራዎች በተሸከመው ሀሳብ ( ለእኔ ) " ባለቤቴ " ን የሚያህልልኝ አላገኘሁም ። ለዚህ ዘፈን ከ " ባለቤቴ " ይልቅ " አትክልተኛው " ስምም ሆኖልኛል ። ምናልባት ግን " አትክልተኛው " ለዘፈን ርዕስነት ያንስ ( አይሆን ) እንደሆን አላውቅም ። ሙሉ ዘፈኑን ስንሰማው ገጸባሕሪዋ በምናቧ ከዋለለችለት የምናብ ባለቤቷ ይልቅ የሰው ያልሆነ ፣ ለሰው አዕምሮ " ሞኝ " የሚባል ፣ ለፍጽምና የቀረበ በዝናብም ፣ በጸሐይም ስራውን የማያስተጓጉል ፣ ብርሀን መርጦ የማይመጣ ፣ በጭለማ የማይሸሸግ ፣ የማግኘትም ፣ የማጣትም ጊዜ ወዳጅ ፣ እንደ አምላክ ያለ ብርቱ ሰው ነው ። ባለቤትነቱ ህልም ሲሆን ብርቱ አትክልተኝነቱ ግን እውን ነው ። ይህ ሰው ትትርናውና ቸርነቱ እንደ አምላክ ያለ ነው ። ከማንም ፣ ከምንም የማይጠብቅ ። መስጠት ብቻ የሆነ ። በአበቦቹ መሐል ብቻ አይደለም ያለው ። ልብ ባለበት ሁሉ ነው ።
" በዝናብ አካሉም በዶፉ እየረሰረሰ
የአትክልቶቹን ስር ሲያጠጣ የልምዱን ውሀ እያፈሰሰ
አሉት የማን ነው ጅል ያን አትክልተኛ
ሳቁበት እንደሞኝ ወይኔ
አላወቁም የእሱ ዝናብ መጣ ቀረ
ንፍገትን ለልቡ እንዳላስተማረ ።
*************************
አሰብኩት ከሆነ እንዲህ ለአትክልቱ
እንዴት መልካም ይሆን ለሚወዳት ሚስቱ "
ያለችውን ብርቱና ቸር ሰው ነው . . .
" ቢዘንብም ቢያካፋም ከጎኔ የማይጠፋ
እንደ ባለ አጸዱ ጽኑ ለመውደዱ
ሳላውቅህ ልንገርህ የነገ ውሀ አጣጬ
አርገኝ እንዳልከስም ፍቅርን ተጠምቼ "
እያለች ምኞቷን ፣ መሻቷን ፣ የወደፊት ህልሟን ትነግረናለች ። መልካምነት መስጠት ብቻ ሳይሆን መቀበልንም ይፈልጋል ። ምርጥ ዘር ምርጥ አፈርንም ይፈልጋል ። በተዘራበት ሁሉ አይበቅልም ። እንደ እሷ የሚረዳ ካልተገኘ ሌሎቹ እንዳሉት " የማነው ሞኝ ? " ያስብላል ።
በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ የዚህ የወደድኩት ብርቱ አትክልተኛ ተቃራኒ ቢሆንም የእኔ ከ1ኛ - 3ኛ " ቻው ( ዎ ) " ነው ።
" አልነበረም ከዓይን የተሰወረ
መንገድህን ሳላየው መች ቀረ
ሰነባብቷል መንፈስህ ሸፍቷል
ልቤን ልብህ ቻው ካለው ቆይቷል ።
አልታወጀም እንጂ ፊትም የእኛ ነገር
የተለያየነው አብረን ሆነን ነበር ።
እንባዬ ተማጽኖህ እንዳያስታርቀን
ያለቀው ያኔ ነው ልብህ የሄደ ቀን ።
እያንዳንዱን ቀናት በእንባ እየሰፈርኩኝ
ቻው ስልህ ኖሬያለሁ እየሸራረፍኩኝ ።
ዛሬም ለበደልህ አረከኝ ጣል ጣል
ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል ። "
ይኽ መቸም በየፍቅር ጎጆው ፣ በየትዳር ማጀቱ ፣ በየጓደኝነቱና ወዳጅነቱ አደባባይ የሚታይ የወቅቱ እውነታ ነው ። በየግንኙነታችን " ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል " ። አብዛኛዎቻችን አንድ ላይ ቆመናል እንጂ አብረን አይደለንም ። " አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል " እንዳለው ድምጻዊው ። እግሮቻችን ብቻ አብረው ይጓዛሉ ፤ አካላችን አንድ ላይ ይታያል ፤ ነፍስ የሌለው ስጋ ነው ። አብረን ውለን እናድራለን ፤ በልባችን ግን ተለያይተናል ። አልታወቀን ይሆናል እንጂ እንደ ግልም ፣ እንደ ሀገርም እንዲህ ሆነናል ። ለዚህ ነው አሁን ያለንበት ላይ ያለነው ። ለዚህ ነው በየሰበቡ ሕይወት የሚታክተን ። ለዚህ ነው መኖር ትግል ፣ አብሮነት መተናነቅ የሚሆንብን ( የሆነብን ) ። የቤተልሔም ሸረፈዲን " ቻው " ለአንድ ተፈቃሪ ወንድ የተሰራም ቢሆን ሀሳቡ ግን እዚህ ድረስም የሚመጣ ነው ። ናቲ " ቃሉ ከዜማው ጋር ነው የመጣው " ያለውና ራሷን ድምጻዊቷን አስለቅሶ የተገለጠው " ቻው " ገና ብዙውን ልብ የሚነካ ስራ ይሆናል ።
" ልቤን " ን ላልወደው አስቤ ነበረ መሰለኝ ። የእድሜም ፣ የፍላጎትም ጉዳይ ሆኖ ፈጠን ላሉ ምቶች አልደነግጥ ሆኖ ይሆናል እንጂ ምን ሆኜ ነው ዜማው ፣ ምቱ ፣ በተለይ የድምጻዊቷ አዘፋፈን ከፍ ብሎ የታየበትን ይህን ስራ " ይቆየኝ " ያልኩት ? ባልወደውና ደጋግሜ ባልሰማው ይቆጨኝ ነበር ። ( ለነገሩ ካልወደድኩት ለምን ይቆጨኛል ? ) " ደስተኛ " ርዕስና ሀሳቡ ደስተኛ ካልሆነች ፣ " አልወድሽም " ከተባለችና ከተገፋች ገጸባህሪ የተገኘ ነው ። " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ትላለች ። " አልወድሽም " ተብላና " ብትጎዘጉዝ አበባ ዛሬ አይረባ " ያለች ሴት ራሷን ማታለል ሳይሆን " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ስትል ካዋጣትና ከተቻላት ያድርግላት ። ከእሷ እንባና የልብ ስብራት ምን ጉዳይ አለን ? ብቻ ከአፏ ሳይሆን ከልቧ ይሁን ።
" እንደ ውሀ መውረድ ፣ እንደ ጸሐይ መውጣት
እንደ ጊዜው መክነፍ ፣ እንደ አሸዋ መብዛት
እውነታ መሆኑን ቅንጣት ሳልጠረጥር
እኔስ አምነዋለሁ የልብህን ፍቅር "
ያለችበት " አካልዬ " ለረጋ ያለ ሙዚቃ አፍቃሪ ይሁነኝ ተብሎ የተቀመረ ስራ ነው ። በምርጤነት ከተቀበልኳቸው መካከል አንዱ ነው ።
አንደኛው ሙዚቃ አስተያየት መስጫ ውስጥ ገብቼ ሳነብ " የዚህ አልበም ትልቁ ችግሩ ውስጡ ያሉት ዘፈኖች 10 ብቻ መሆናቸው ነው " ሲል " አድናቆቱን " ገልጿል ። እኔም እንደዚያ ሆኖ ይሰማኛል ። ከአስሩ ሰባቱን ስራዎች በልዩ ሁኔታ ወድጃቸዋለሁ ። አንዱ የዋለልኩበትና ሁለቱ ደግሞ ልብ ያልሰጠኋቸው ናቸው ። ይህ በአንድ አለበም ውስጥ ከበቂ በላይ ስኬታማነት ነው ። ከብዙ ዓመት በኋላ ተሟልቶ ያገኙሁት ምርጤ ነው " ደስተኛ " አልበም ።
እዚህ አልበም ላይ ያለኝ አንድ ( ግላዊ ) ቅሬታ አስሩም ስራዎች የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸው ነው ። እንዳይሆኑ የሚከለክል ደንብ የለም ። ፕሮዲዩሰሮቹ የቤተልሔምን እድሜና የፍቅር ጊዜዋን አስበው ያደረጉት ሊሆን ይችላል ። ያም ቢሆን በዚህ ውጥንቅጡ የወጣ የመከራ ጊዜ ፣ በብዙ ሰው ሰራሽና የአስተሳሰብ ሰንሰለት እግር ከወርች ታስረን መሔጃ ባጣንበት ዘመንና ሀገር ፣ ላለንበት ጊዜ ፣ ለስሜታችን ፣ ለህመማችን ፣ ለሰለለው ተስፋችን የሚሆን አንድ ስራ ልናጣ አይገባም ብዬ አስባለሁ ። ናቲና ምህረተአብ ለራሄል ጌቱ እንደሰጧት " ያገሬ ሰው " ያለ ስራ ቢመርቁልን እንዴት መልካም ነበረ ?
ከቀናት በፊት አስቴር አወቀ ( በድጋሚ ስራዎቿም ቢሆን ) በትንሿ ቤተልሔም ሸረፈዲን ላይ ተደርባ አልበሟን መልቀቋ አስፈርቶኝ ነበረ ። ይህን የመሰለ አልበም ፣ የ4 ዓመት የሚነገርና የማይነገር እልህ አስጨራሽ ድካም መና እንዳይቀር ሰግቼ ነበረ ። ስጋቴ ስጋት ብቻ ሆኖ ቀርቷል ። ቤተልሔም የዋርካው ጥላ ሳያርፍባት አልፋለች ። ገና ገና ትቀጥላለች ፤ ትቀጣጠላለች ።

3 months ago
ቼልሲ አሜሪካ ደርሷል
#ethiopia | የለንደኑ ክለብ ቼልሲ የወደፊት የቡድኑን አቅም ለመገንባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ አሜሪካዊውን ድንቅ ታዳጊ መስመር ተጫዋች ቤንጂ ፍላወርስን ከአሜሪካው ዳላስ ኤፍሲ ለማስፈረም ከመሰረታዊ ስምምነት ላይ ደርሷል።
በተዘጋጀው የዝውውር እቅድ መሠረት ይህ የክንፍ መስመር ተወርዋሪ ዕድሜው 18 ዓመት እንደሞላ በቀጥታ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ በማምራት የቼልሲን አካዳሚ ይቀላቀላል።
በአሜሪካ እግር ኳስ ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ተስፋ ሰጪ ታዳጊዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገሩለትን ፍላወርስን ለማስፈረም በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የረጅም ጊዜ ፍላጎት አሳይተው የነበረ ቢሆንም ቼልሲዎች ፈጣን እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia | የለንደኑ ክለብ ቼልሲ የወደፊት የቡድኑን አቅም ለመገንባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ አሜሪካዊውን ድንቅ ታዳጊ መስመር ተጫዋች ቤንጂ ፍላወርስን ከአሜሪካው ዳላስ ኤፍሲ ለማስፈረም ከመሰረታዊ ስምምነት ላይ ደርሷል።
በተዘጋጀው የዝውውር እቅድ መሠረት ይህ የክንፍ መስመር ተወርዋሪ ዕድሜው 18 ዓመት እንደሞላ በቀጥታ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ በማምራት የቼልሲን አካዳሚ ይቀላቀላል።
በአሜሪካ እግር ኳስ ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ተስፋ ሰጪ ታዳጊዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገሩለትን ፍላወርስን ለማስፈረም በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የረጅም ጊዜ ፍላጎት አሳይተው የነበረ ቢሆንም ቼልሲዎች ፈጣን እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመጪው እሁድ በሚደረገው የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ ለሁለተኛው አጋማሽ እስኪመለሱ የሚኖረው የእረፍት ሰዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ ከ20 እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ተጠቆመ።
ይህ ሊሆን የቻለው በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ እረፍት ወቅት፣ ልክ እንደ አሜሪካው 'ሱፐር ቦውል' አይነት የ11 ደቂቃ ግዙፍ የሙዚቃ ትዕይንት ለማቅረብ በመታቀዱ ነው።
በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ቦርድ የጨዋታ ህግ መሰረት፣ ተጫዋቾች የሚያገኙት የእረፍት ሰዓት "ከ15 ደቂቃ መብለጥ የለበትም" የሚል ደንብ አለ። ይሁን እንጂ የዓለም እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ (FIFA) ውስጥ ያሉ ምንጮች እንደገለጹት፣ በእሁዱ ጨዋታ የእረፍቱ ጊዜ 20 ደቂቃ አካባቢ ይሆናል። አሁን ላይ ባለው አንዱ አማራጭ መደበኛውን የ15 ደቂቃ እረፍት ሰጥቶ፣ የታቀደውን የ11 ደቂቃ የሙዚቃ ትዕይንት ማካሄድ ነው።
ፊፋ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥመው ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባለፈው ዓመት በኒው ጀርሲ በተካሄደው የዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ኮልድፕሌይ፣ ጄ ባልቪን፣ ዶጃ ካት፣ ቴምስ እና ኢማኑኤል ኬሊ ያቀረቡትን ትዕይንት ተከትሎ፣ የእረፍት ሰዓቱ በአጠቃላይ 24 ደቂቃ መፍጀቱ ይታወሳል።
ለእሁዱ ትልቅ የፍጻሜ ጨዋታ እረፍት በሚቀርበው ዝግጅት ላይ ታዋቂዎቹ ድምጻውያን ማዶና፣ ሻኪራ እና የኮሪያው ታዋቂ የሙዚቃ ቡድን ቢቲኤስ በዋና አቅራቢነት የሚሳተፉ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ጃስቲን ቢበርም በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል።
በተጨማሪም በርና ቦይ፣ ጉስታቮ ዱዳሜል እና የፒኤስ22 ቾረስ ከኮልድፕሌይ ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። አጠቃላይ ዝግጅቱን ያቀናበረው ደግሞ የኮልድፕሌይ ድምጻዊ ክሪስ ማርቲን ነው።
የዓለም ዋንጫው የፍጻሜ ጨዋታ በአካባቢው አቆጣጠር ከቀኑ 9:00 ሰዓት (በለንደን አቆጣጠር 8:00 ምሽት) ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድሞ ከቀኑ 7:30 ሰዓት (በለንደን 6:30 ምሽት) ጀምሮ ደማቅ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።
በዚህ ታላቅ የመዝጊያ መርሃ-ግብር ላይ ተዋናይ ቶም ክሩዝ፣ ላውራ ፓውሲኒ፣ ኒኮል ሸርዚንገር፣ ሮቢ ዊሊያምስ እና ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ የሚሳተፉ ሲሆን፣ የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር ደግሞ ጄኒፈር ሁድሰን እንደምትዘምረው ታውቋል።
ስፔን ዛሬ በዳላስ በተደረገው የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜው ማለፏን ያረጋገጠች ሲሆን፤ ረ ነገ በአትላንታ ከሚገናኙት እንግሊዝ ወይም አርጀንቲና መካከል አሸናፊውን በእሁዱ ታላቅ ፍጻሜ የምትገጥም ይሆናል።

ስምረትን ፍለጋ!!!
በዳላስ ቴክሳስ ዛሬ ይመረቃል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ወዳጄነህ ማህረነ (ዶክተር)
የመድረኩ አጋፋሪ ገጣሚ አበባው መላኩ
በዚህ ታላቅ የመጽሐፍ ምረቃ ስነስርአት ላይ የመጽሐፍ ፊርማ መርሐ-ግብር ይካሄዳል ።
ዳላሶስች ስምረትን ፍለጋ መጽሐፍ ምረቃ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል ። #dallastexas

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ኪሊያን ምባፔ በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ያመከነውን የፍጹም ቅጣት ምት በሚያስገርም ግብ ባካካሰበት የሩብ ፍፃሜ ፍልሚያ፣ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ እጅግ ልቆ በመገኘት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል። ምባፔ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ስምንተኛ ግቡን በማስቆጠር ደምቆ አምሽቷል።
በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ በማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ኑሳይር ማዝራዊ በተሰራበት ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ምባፔ ራሱ ቢመታውም፣ ደካማ የነበረውን ምት ግብ ጠባቂው ያሲን ቦኖ በቀላሉ አድኖበታል። የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (ቫር) ጥፋቱን ለማረጋገጥ ከሶስት ደቂቃዎች በላይ በመውሰዱ ምባፔ ኳሷን ለመምታት ረዘም ያለ ጊዜ መጠበቅ ግድ ብሎት ነበር፤ ሲመታውም አቋቋሙን አበላሽቶ ወደ ቀኝ የላካት መሬት ለመሬት ኳስ ለቦኖ ቀላል ኢላማ ሆናለች።
ይሁን እንጂ ፈረንሳይ የማጥቃት ጫናዋን አላቀዘቀዘችም። ዴዚሬ ዱዌ ያደረገው ሙከራ ሲዳንበት፣ የአስቶን ቪላው ተከላካይ ሉካስ ዲኝ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ቦኖ በትንሹ ነክቶት የግብ አግዳሚው መልሶበታል። ዳዮት ኡፓሜካኖ በግንባሩ የገጨውን ኳስም ቦኖ በሚገርም ብቃት አውጥቶበታል።
ሆኖም የሪያል ማድሪዱ አጥቂ በ60ኛው ደቂቃ ስህተቱን በሚገባ አርሟል። ከቅጣት ምት ክልል ጠርዝ አካባቢ አክርሮ የመታው እጅግ ማራኪ እና ተጠምዛዥ ኳስ መረብ ላይ በማረፉ፣ ፈረንሳይ የሚገባትን መሪነት አግኝታለች።
ከስድስት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ የባሎን ዶር አሸናፊው ኡስማን ዴምቤሌ፣ የሞሮኮን ተከላካዮች ሰርስሮ በመግባት በላከው መሬት ለመሬት ኳስ የፈረንሳይን መሪነት ወደ ሁለት አሳድጓል። ቦኖ ኳሷን በእጁ ቢነካትም ከመግባት ሊያድናት ግን አልቻለም።
ይህች የምባፔ ግብ፣ በዘንድሮው ውድድር ካስቆጠራቸው ግቦች ብዛት አንጻር ከአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ጋር በ8 ግቦች እኩል እንዲቀመጥ አስችሎታል። ነገር ግን ፈረንሳዊው ኮከብ ከቀድሞ የፒኤስጂ የቡድን አጋሩ የተሻለ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበሉ (አሲስት) የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩን እየመራ ይገኛል።
በተጨማሪም ሁለቱ ኮከቦች የምንግዜም የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን አስገራሚ ፉክክር እያደረጉ ሲሆን፣ የ39 ዓመቱ ሜሲ በ21 ግቦች ክብረወሰኑን ሲይዝ፣ የ27 ዓመቱ ምባፔ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት 20 ግቦች ላይ ደርሷል።
በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜው ሞሮኮን 2-0 ያሸነፈችው ፈረንሳይ፣ በድጋሚ በተገናኙበት በዚህ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታም ፍጹም የበላይነቷን አሳይታለች። በዓለም ደረጃ 7ኛ ላይ የምትገኘው ሞሮኮ በጨዋታው ሙሉ ለሙሉ ተዳፍና የዋለች ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ያደረገችው 2 ለ 0 እየተመራች በ83ኛው ደቂቃ ላይ ነበር።
የፈረንሳይ ብቸኛ ስጋት የነበረው በ77ኛው ደቂቃ በክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ዣን ፊሊፕ ማቴታ ተቀይሮ የወጣው ምባፔ፣ በቀኝ ቁርጭምጭሚቱ ላይ በረዶ አስሮ መታየቱ ነበር። ሆኖም ከጨዋታው በኋላ ከቡድን አጋሮቹ ጋር እየዘለለ 6ኛ ተከታታይ ድላቸውን ሲያከብር መታየቱ፣ ጉዳቱ ያን ያህል ከባድ አለመሆኑን አመላካች ሆኗል።
በ1998 እና በ2018 የዓለም ዋንጫን ያነሳችው እና በ2022ቱ የፍፃሜ ጨዋታ በአርጀንቲና የተረታችው ፈረንሳይ፣ የፊታችን ማክሰኞ በዳላስ በሚደረገው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ከስፔን ወይም ቤልጂየም ጋር የምትፋለም ይሆናል። እስካሁን ባደረገቻቸው 6 ጨዋታዎች 16 ግቦችን በማስቆጠር በውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ቡድን የሆነችው ፈረንሳይ፣ ዋንጫውን ለማንሳት ቀዳሚ ግምት የሚሰጣት ቡድን መሆኗን በድጋሚ በተግባር አስመስክራለች።

ዶ/ር ወዳጄነህ በ ዳላስ ቴክሳስ፣ አሜሪካ ቅዳሜ ጁላይ 11, 2026.
* የጥበብ ምሽት
* በስምረት ቢውቲ የተፃፈው
" ስምረትን ፍለጋ " መጽሃፍ ምርቃት
* የማግኖኒሚቲ ሌክቸር
Saturday 11th of July, 2026
4:30 PM. Address: 9560 Skillman St. #126 , Dallas TX 75243.

4 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሊዮኔል ሜሲ ትላንት እጅግ ትልቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡ የአርጀንቲናው አምበል በአለም ዋንጫ ላይ 18 ጎሎችን በማስቆጠር አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ በዳላስ ስታዲየም ተገኝተው ይህን ታሪክ በአይናቸው ከተመለከቱት ውስጥ ድምፃዊት ሻኪራ አንዷ ናት፡፡ ሜሲ ሁለቱንም ጎሎች ሲያስቆጥር በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ሆና ስሜቷን ስትገልፅ ታይታለች፡፡
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም በኢንስታግራም ገፃ ላይ ‹‹እጅግ ኮርቼብሀለሁ ሊዮ፡፡ ለአገርህ፣ ለቤተሰብህና ለመላው የላቲን ማህበረሰብ የምታደርገው ሁሉ የሚያኮራ ነው፡፡ ቁርጠኝነትህና ብርታትህ ብዙዎችን ያነሳሳም፡፡ በዚሁ ቀጥልበት›› በማለት ፅፋለች፡፡ ሻኪራ በአለም ዋንጫው የተለያዩ ጨዋታዎችን እየተመለከተች ሲሆን ትላንትም በዳላስ ስታዲየም ክብር ትሪቢዩን ታድማለች፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ከፊፋ ጋር ያላትን 20 አመታት የዘለቀ ቁርኝት ተከትሎ ነው፡፡
በ2010 የአለም ዋንጫ ‹‹ዋካ ዋካ›› የተሰኘውን ሙዚቃ ከሰራች ጀምሮ ከፊፋ ጋር ግንኙነት የመሰረተችው ሻኪራ በ2014ቱ አለም ዋንጫም ‹‹ላ ላ ላ›› በሚለው ሙዚቃ ውስጥ ተሳትፎ አድርጋ ነበር፡፡ በዘንድሮው ውድድር ደግሞ ከበርና ቦይ ጋር በመሆን ‹‹ዳይ ዳይ›› የተሰኘውን የፊፋ ይፋዊ ሙዚቃ መስራቷ ይታወቃል፡፡ በዘንድሮው የአለም ዋንጫ መዝጊያ እረፍት ሰአት ላይ በሚከናወነው የፊፋ ‹‹ሀፍ ታይም ሾው›› ላይ ስራዋን እንደምታቀርብም ይጠበቃል፡፡

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በቴክሳስ ዳላስ የስታዲየሙ መብራቶች ደምቀዋል። ሜዳው ላይ ያለው ሰው ግን ከማንኛውም ደማቅ መብራት በላይ በክህሎቱ አለምን እያበራ ነው። ሰኔ 2026፤ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ለሚቀጥለው ረቡዕ 39ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ሲጠባበቅ፣ አስቀድሞ ለራሱ እና ለአርጀንቲና ሕዝብ ታላቅ የልደት ስጦታን አበርክቷል።
የጨዋታው ሰዓት 38ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ፣ ፋኩንዶ ሜዲና ያሻማትን ኳስ ቲያጎ አልማዳ በእግሮቹ መካከል አሾልኮ ለሜሲ ሲያመቻችላት፣ የዳላስ ተመልካች ምን ሊፈጠር እንደሆነ ጠረጠረ። "አንት" (የአልማዳ ቅጽል ስም) ኳሷን ሳይነካ ለሜሲ መፍቀዱ የቡድኑን ፍቅርና መተማመን በጉልህ የሚያሳይ ነበር። ሜሲም አልቸኮለም፤ በቅጽበት የተመታች ድንቅ ኳስ የአውስትራሊያን መረብ አርገፈገፈች። ይህ ጎል የአርጀንቲናውን ጌታ በዓለም ዋንጫ ታሪክ 17ኛ ጎል አስቆጣሪ በማድረግ ከጀርመናዊው ሚሮስላቭ ክሎዝ ጋር አቻ አደረገው።
ግን ሜሲ እዚህ አያቆምም!
ጨዋታው ተገባዶ በተጨመረው ሽርፍራፊ ደቂቃ፣ አውስትራሊያውያን ተከላካዮች ተስፋ ቆርጠው የከበቡት ሜሲን ነበር። ከመጠነኛ አንግል ላይ ሆኖ፣ በሁለት ተከላካዮች መሃል ያሰለፋት ኳስ መረቡን ስትገጭ፣ ሜሲ የዓለም ዋንጫ ታሪክ ብቸኛ እና ከፍተኛው የ18 ጎል ባለቤት ሆኖ ታሪክ ተጻፈ።
የምሽቱ ጀግና ግን መጀመሪያ ላይ ፈተና ገጥሞት ነበር። በ8ኛው ደቂቃ ላይ አርጀንቲና ያገኘችውን የፍጹም ቅጣት ምት ሜሲ ወደ ውጪ ሲመታው፣ በስታዲየሙ የነበሩ ደጋፊዎች በድንጋጤ ጸጥ ብለው ነበር። ሆኖም ሜሲ "ተስፋ መቁረጥ" የሚባል ቃል በስሙ መዝገበ-ቃላት ውስጥ እንደሌለ በአራት እጥፍ ጥንካሬ አሳየ።
የስፔኑ ጋዜጠኛ ጊሌም ባላጌ እንደገለጸው "ለሜሲ ሐውልት ለመስራት ጊዜ የለንም፣ ምክንያቱም እሱ በየቀኑ አዲስ ታሪክ እየሰራ ነው።" አሁን በ39 ዓመቱ፣ እንደ ወጣት ልጅ ሜዳውን ሲያካል፣ በእድሜ ሳይሆን በአእምሮ እና በጥበብ ተከላካዮችን ሲያሸንፍ ማየት ለተመልካች ትልቅ ክብር ነው።
የእንግሊዙ ክሪስ ሰተን ደግሞ በዳላስ ሲናገር፣ "ሜሲ የትልቅ አፍታዎች ሰው ነው። አርጀንቲና ለሜሲ የተገነባች ቡድን ናት፤ ሁሉም ለሜሲ ይጫወታሉ፣ ሜሲ ደግሞ ለታሪክ ይጫወታል።"
በምድብ ጄ አርጀንቲና 6 ነጥብ በመሰብሰብ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች። ሜሲ በሁለት ጨዋታዎች 5 ጎል በማስቆጠር የውድድሩ ኮከብ ሆኗል። ዳላስ ላይ የነበረው ምሽት፣ ለሜሲ እና ለተከታዮቹ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ትውልድ የሚነገር፣ የማይረሳ የግርግዳ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል።
ሊዮኔል ሜሲ፤ የማይጠግብ የግብ አዳኝ፣ የታሪክ ጸሐፊ!

የኔዘርላንድ እና የጃፓን ብሄራዊ ቡድኖች በአቻ ውጤት ተለያዩ
#ethiopia | በአለም ዋንጫ የምድብ ስድስት መክፈቻ ጨዋታ የኔዘርላንድ እና የጃፓን ብሄራዊ ቡድኖች ተገናኝተው የሁለት ለሁለት አቻ ውጤት አስመዝግበዋል።
በዳላስ በተካሄደው ጨዋታ ቨርጂል ቫን ዳይክ እና ክሪሰንሲዮ ሱመርቪል የኔዘርላንድን የግብ መረቦች ማናጋት የቻሉ ሲሆን የጃፓንን የአቻነት ግቦች ደግሞ ናካሙራ እና ዲያቺ ካማዳ በጨዋታው ማጠናቀቂያ የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥረዋል።
#worldcup #football #netherlands #japan #matchday #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
ቀኝ አዝማች በኩረ ምዕመናን ትዛዙ ኮሬ የኢትዮጵያን ባህል፣ ቱሪዝምና በጎ አድራጎት በማስፋፋት የሚታወቁ ታዋቂ ኢንተርፕረነር፣ የባህል አምባሳደር እና ሀገር በቀል ሽማግሌ ናቸው። በተለይም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን እና ግዙፍ የባህል ምግብ ቤቶች አንዱ የሆነውን ዮድ አቢሲኒያ (Yod Abyssinia) ባህላዊ ምግብ ቤት በመመስረታቸው በሰፊው ይታወቃሉ።
ስለ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ዋና ዋና መረጃዎች
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና ባለቤት በ1996 ዓ.ም.
(እ.ኤ.አ. በ2003) ዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ ምግብ ቤትን መስርተዋል።
ምግብ ቤቱ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች፣ ሙዚቃዎች እና ውዝዋዜዎች ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ዜጎች በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
እንደ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ያሉ በርካታ የዓለም መሪዎችን እና የውጭ አገር ዲፕሎማቶችን በምግብ ቤታቸው አስተናግደዋል።
❸ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
ማኅበራዊ አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች
ለተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት እና ችግረኛ ወገኖች ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃሉ።
በበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸው ምክንያት በ2016 ዓ.ም የፊላንትሮፒ (የበጎ አድራጎት) ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።
በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰላምን ለማስፈንና እርቅ ለማውረድ እንደ ትልቅ የሀገር ሽማግሌ ሆነው ያገለግላሉ።
በጎ ተግባራት እና ማህበራዊ ሀላፊነት በመወጣት አርዓያነት ያለዉን ተግባራት በመስራት ይታወቃል።
የዓመቱን 360 ቀናት ለኢትዮጵያ ሀገራቸዉ እንዲሁም 4 ቀናት ለበጎ አድራጎት ተግባራት ሲውል ፤ 365 ኛውን ቀን ደግሞ ዕድገት እንደሚያስተዋዉቅ የሚያምኑት የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ ናቸዉ።
የዮድ አቢሲኒያ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ቀኝ አዝማች ትዛዙ ኮሬ እንዲሁም ድርጅታቸዉ 'ዮድ አቢሲኒያ'ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር፣ ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ፣ ለቶራ የህፃናት ማሳደጊያ ፣ ለሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ፣ ለየወደቁትን እናንሳ የአረጋውያን መርጃ ማህበር ለሌሎችም በማገዝና በመርዳት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በጎ ስምና አርዓያነትን በተግባር ለማሳየት ችሏል።ወደፊትም ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
❹እዉቅናና ሽልማት
➢የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና
ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ለ12ኛ ጊዜ በተካሄደዉ የዓመቱ በጎ ሰዉ ሽልማትና እዉቅና በቅርስ ባህል እና ቱሪዝም ዘርፍ ዮድ አቢሲኒያ፡የባሕል ምግብ አዳራሽ ተሸልሟል።
የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦችን ፤ ውዝዋዜዎችን እና ባህላዊ እሴቶችን ለቱሪስቶች እና ማህበረሰቡ የሚያቀርብ ተቋም ሲሆን የኢትዮጵያን እሴቶችን በማስተዋወቅ ረገድ ያስቀመጠው ደማቅ አሻራ ከፍ ያለ ነዉ።
ዮድ አቢሲኒያ ባህል ባንድ
ለቱሪስቶች የአገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎች ዉዝዋዜን በማሳየት ቱባ ባህላችንን ሳይበረዝና ሳይከለስ ያሳያል።
➢ የቱሪዝም አዋርድ
የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሐምሌ 6/2016ዓ.ም በአድዋ መታሰብያ ሙዚየም ባካሄደው የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ምስረታና 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለከተማችን የቱሪዝም ልማትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቱሪዝም ተቋማትና አካላት የቱሪዝም አዋርድ ከተሰጡት መካከል አንዱ ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ ነዉ።
የቱሪዝም ተቋማቱ በሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት ባላቸው የቱሪዝም ፈጠራ ስራ እንዲሁም የቱሪስት አያያዝና የመሳሰሉት መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ ከዘርፉ 1ኛ በመዉጣት ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ፣የቱሪዝም አዋርድ ተሸልሟል።
➢"የ8ኛዉ የአርአያ ሰው ሽልማት"
ተቀማጭነቱን በሀገረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ያደረገው ዓድዋ የባህልና የታሪክ ኅብረት ለትርፍ ያልተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በዋናነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን አርአያ የሚሆን ሥራ ለሚሠሩ ግለሰቦችና ተቋማት"የአርአያ ሰው ሽልማት" በሚል ዕውቅና ይሰጣል፡፡
ለ8ኛ ግዜ በአዲስ አበባ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ለሀገር ባለውለታዎች በተለይም በባህል ልማት፣ በተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቱሪዝም እና ቅርስ እንዲሁም በታሪክ መስኮች ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማት ከተሰጣቸው መካከል ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ አንዱ ነዉ።
ዓለም አቀፍ እውቅና
የኢትዮጵያን ባህልና ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቃቸው “የባህልና ቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ክብር ተሰጥቷቸዋል።
በቅርቡ (እ.ኤ.አ በ2025) በአሜሪካ ሲያትል በተካሄደው የ42ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል (ESFNA) ላይ ለሀገራቸው ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ልዩ የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
❺ዋና ዋና ቅርንጫፎችና አድራሻዎች
ዮድ አቢሲኒያ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቁልፍ ቦታዎች ቅርንጫፎችን ከፍቶ ይገኛል፦
ቦሌ ቅርንጫፍ (ዋናው)፦ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ፣ ከብራስ ሆስፒታል ከፍ ብሎ የሚገኝ የነበረ ሲሆን አሁን ቀድሞ ከነበረበት በ100 ሜትር ገባ ብሎ ኬኬር ህንፃ አጠገብ ይገኛል።ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርብ በመሆኑ ለቱሪስቶች ተመራጭ ነው።
ፒያሳ (ቴዎድሮስ አደባባይ) ቅርንጫፍ፦ በቅርቡ በዲል ፕላዛ ፊት ለፊት የተከፈተ አዲስና ዘመናዊ የባህል አዳራሽ፣ የስፖርት ባር (Sport Bar) እና የባዛር ማዕከል ነው።
ዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል፦ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ማዕድን ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል ነው።
❻የ"ዮድ" መሪ ቃል በተግባር
የድርጅቱ መሪ ቃል የሃገራችን ኢትዮጵያን ”ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ” የሚል ነው ባለፉት 22 ዓመታት የኢትዮጵያን ባህልና መስተንግዶን ጨምሮ ሲያስተዋውቅ ኖሯል ፡፡ ለዚህም አስተዋፅኦው ”የኢትዮጵያ የባህልና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል ዕውቅና ከመንግስት ተሰጥቶታል ፡፡
“ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ” በሚል መርህ ከመላው ዓለም ወደ ሃገራችን ለመጡ እንግዶች የባህል ምግብና መጠጦች መስተንግዶ በመስጠት ፣ የብሔር ብሄረሰቦችን ሙዚቃዎችና ውዝዋዜዎች በማቅረብ ፣ የሀገራችንን የታሪክ የባህልና የቱሪዝም ሃብቶችና ቅርሶቻችንን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በመገንባት ብዙ በመስራት ”የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም አምባሳደር” የሚል እውቅናን ለማግኘት ችሏል፡፡
"ዮድ"
ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ
በእግዚአብሔር ቀኝ ያለ እሱ ኃያልና
ጽኑዕ የሆነ ነው ማለት በሌላ መልኩ"ዮድ" ማለት በጉራጌ ቋንቋ "መመስከር ወይም መናገር" ማለት ነዉ።
ከ1996ዓ.ምማለትምላለፉት 22 ዓመታት በተለያዩ ወቅቶች ወደ ሀገራችን የመጡ በርካታ የሀገራት መሪዎችን ፣ ዲፕሎማቶችን ፣ የዓለም ታላላቅ ሰዎችን፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ አትሌቶች ፣ አርቲስቶች የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎችም በሺዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶችንና ኢትዮጵያዊያን እንግዶችን ተቀብሎ በፍቅርና በአክብሮት ሲያስተናግድ የቆየው ዮድ አቢሲኒያ በቀጣይም በሀገራችን ለሚከናወኑ ታላላቅ ሁነቶች ሙሉ አገልግሎት ለመስጠት ከወትሮው በተለዬ አኳኋን መዘጋጀቱ ተስተዉሏል።በ500 ብር ካፒታል እና በአነስተኛ የስራ ጅምር በጥረት የተገነባ ካምፓኒ በበርካታ ፈተናዎች ዉስጥ አልፎ ዛሬ በርካታ ቁጥር ላላቸዉ ወገኖቻችን የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ኩባንያ ለመሆን በቅቷል።
"የሃገራችን ኢትዮጵያን ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቅርሶች እንጠብቅ፤ እናክብር ፤ ቋንቋችንን እናሳድግ ”ዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ
ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጩ የቪዲዮ ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ አንድ የቴክሳስ ሮቦቲክስ ኩባንያ "ስቱዊ" (Stewie) የተሰኘውን የሰው ቅርጽ ያለው ሮቦት ከዳላስ ወደ ላስ ቬጋስ ባደረገው መደበኛ በረራ ላይ አሳፍሮት ተጉዟል። ሮቦቱ በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲራመድ እና አውሮፕላን ላይ ሲሳፈር፣ ሌሎች መንገደኞች እና የበረራ አስተናጋጆች በከፍተኛ አግራሞት እና ድንጋጤ ሲመለከቱት ታይተዋል።
ይህንን አስገራሚ ክስተት ተከትሎ በማግስቱ፣ ሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሻንጣ አያያዝ እና የጉዞ ፖሊሲውን በአስቸኳይ በማሻሻል ጥብቅ እገዳ ጥሏል። አየር መንገዱ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት፣ የሰውም ሆነ የእንስሳት ቅርጽ ያላቸው ሮቦቶች መጠናቸውም ሆነ የሚሰጡት አገልግሎት ምንም ይሁን ምን በበረራዎቹ ላይ እንዳይሳፈሩ ሙሉ በሙሉ አግዷል። ይህ ክልከላ ከመንገደኛ ጋር ወደ ውስጥ የሚገቡትንም ሆነ ከሻንጣ ጋር በርቀት የሚጫኑትን ሮቦቶች በሙሉ የሚያጠቃልል ነው።
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጠው አምራቹ የቴክሳስ ሮቦቲክስ ኩባንያ በበኩሉ፣ ሮቦቱ "ስቱዊ" የራሱ የሆነ ሙሉ የመሳፈሪያ ትኬት ተቆርጦለት እንደተጓዘ ገልጿል። በተጨማሪም የሮቦቱ ባትሪ የአሜሪካ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደርን (FAA) የደህንነት መስፈርት ያሟላ መሆኑን እና ኩባንያው ጉዞውን ሲያደርግ በወቅቱ የነበሩትን የአየር መንገዱን ህጎች በሙሉ ያከበረ ህጋዊ አሰራርን የተከተለ መሆኑን አስረድቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሮቦት ተሳፋሪ ቢያጋጥመው ምን ይወስን ይሆን? በሮቦት ላይ ያለው ፖሊሲስ ምንድን ነው?

መድፉ ምስጋና ለጠንቃቃ አለቃው አርቴታ ይግባና እንደተጨነቀ ለናፈቀው ዋንጫ ከመቼውም ግዜ በላይ ቀርቧል !!!
በኤፍሬም የማነ
#ethiopia | አርሰናል በሆነው ባልሆነው ይጨነቃል ። አርሰናል በልጦ በተቆጣጠረው ጨዋታም ይጨነቃል ። ለወረደውም ለረባው ላልረባውም ያምጣል ይጨነቃል ። በጊዜ ጨዋታ ማጠናቀቅ በመድፉ ቤት ብርቅና ድንቅ ነው ። አርሰናል ለአደጋ እራሱን እንደጋበዘ ለዛሬ የከፍታ ደረጃው በርካታ ውድ ሶስት ነጥቦችን ከያዘባቸው ጨዋታዎች መሃከል አንዱ የበርንሌይ ፍልሚያ ሆኗል ። ማይክ አርቴታ ዛሬም የአርሰናል ዋና አሰልጣኝም ዋና ተጋጣሚም መስሎ የወረደው በርንሌይን በቆመ ኳስ ጎሉ 1ለ0 ረቷል ። የመድፉ የዛሬ ከፍታ ዋና ተዋናይ አርቴታ በምሽቱ ጨዋታ ዋና አጥቂው ዮኬሬስን ከካይ ሃርቫርትዝ ለምን በቋሚነት እንዳላስጀመረ አይታወቅም ። አርቴታ ኦዴጋርድ እና ኤዜን በጋራ ሲጠቀም ዮኬሬስን ተጠባባቂ ያደርጋል ። ኦዴጋርድ እና ኤዜን ቤንች ያደረገ ዕለት በአንፃሩ ዋና አጥቂው ዮኬሬስን በቋሚነት ያለ አቅራቢዎቹ ያሰልፋል ። ይህ የማይክ አርቴታ አባዜ ለሁለም መነጋጋሪያ ሆኗል ።
በጨዋታው የተሻለው ቡድን በጊዜ ጨዋታውን መግደል እንደልማዱ እንደተሳነው በድል ፈፅሟል ። የቆመ ኳስ ዛሬም መድፉን አድኗል ። የጎሉ ባለቤት ካይ ሃርቫርትዝ 68 ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ያልተባረረው በዳኛው ችሮታ ሆኗል ። በልጦም ተበልጦም በሜዳውም ከሜዳው ውጭም ከተረፈውም ከወረደውም በሆነውም ባልሆነውም ጨዋታ ሁሉ በጊዜ ጨዋታን ማጠናቀቅ ለመድፈኛው ብርቅና ድንቅ እንደሆነ የሰሜን ለንደኑ ገናና ለሚመጥነው የሻምፒዮንነት ንግስናው ተቃርቧል ። አርሰናል በብዙ የአንድ ሻምፒዮን ቡድን የጥንካሬ መልኮች መዋቅር ከየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ጠንካራው የተከላካይ መስመር ቅኝቱ ጋር በታላቁ ፔፕ ጋርዲዮላ የስንብት ዋዜማ ወደ መጨረሻው ክብር ከመቼውም ግዜ በላይም ተጠግቷል ። የመድፉ የፀና የድል አሸናፊነት ጉዞ ዋና የውድድር ዓመቱ የጥንካሬ መለያ ቢሆንም አርሰናል ከአናት እየመራው በዘለቀው ገናና ሊግ ከህልሙ ጫፍ ለመድረስ የተሟላ የቡድን ጥልቀት የተጨዋቾች አማራጭ ይዞ በሁሉም የጨዋታ ቅርፆች ለወራጁ ሁሉ እላፊ መጨነቁ የበለጠውን ጨዋታ በጊዜ ለመግደል መቸገሩ ግን አጠያያቂ ነው ።
በሊጉ ብቻ በ22 ጨዋታዎች ለ18ኛ ጊዜ ከቆመ ኳስ የተቆጠረችው የካይ ሃርቫርትዝ ብቸኛ ጎል መድፈኛውን ለ22 ዓመት ከራቀው ታላቅ የዋንጫ ክብር ለማገናኘት የመጨረሻው መጨረሻ ቀጠሮው ይጠበቃል ። ምናልባትም የመድፉ የውድድር ዓመቱ በጭንቅ የቀጠለ ልፋት ነገም ከቫይታሊቲ ስቴዲየም የሲቲ በርንማውዝ ፍጥጫ ጋር ሊጠናቀቅ ሊፈፀም ይችላል ። ካልሆነ ግን ለተናፈቀው ዋንጫ ልጅን ከመድፉ መንደር ለማንሳት ምጡ መጨነቅ መንቆራጠጡ እስከ 38ኛው ሳምንት የሲዝኑ ፍፃሜ አሰልጣኝ ማይክ አርቴታ አንዴ አሸንፎ እስካልተገላገለ ድረስ መቀጠሉ ለመድፉ ወዳጆች ሁሉ ዕርግጥ ነው ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የደቡብ ጎንደር ዴራ ወረዳ አድያመ ዮርዳኖስ የወንቅሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መስራች እና አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም፣ በአሜሪካ ሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርኒያ ታላቅ ገዳም መመስረታቸው ተሰማ። በአሁኑ ወቅት በዳላስ የገዳመ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አስተዳዳሪ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አባ ዮሐንስ፣ ይህ አዲሱ የካሊፎርኒያ ገዳም ምረቃ መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን በሰሜን አሜሪካ ይበልጥ ለማስፋት የወሰዱት ትልቅ ሐዋርያዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ አገልግሎት መስፋፋት ድንገተኛ ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በተሰጠ ይፋዊ ቡራኬ እና የሥራ ኃላፊነት ላይ የተመሰረተ ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በጻፉት እና ዘ-ሐበሻ እጅ የገባው ይፋዊ ደብዳቤ (ቁጥር ል/ጵ/452/420/2012)፣ አባ ዮሐንስ የወንቅሸት ገዳሙን ከመመስረት እና ከማቋቋም ደረጃ ጀምሮ ለማኅበረ ካህናት እና ለምዕመናን እያበረከቱ ያለውን የላቀ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት አድንቀዋል።
በደብዳቤው ላይ በግልጽ እንደሰፈረው፣ አባ ዮሐንስ ያላቸውን ሐዋርያዊ ተልእኮ ይበልጥ አጠናክረው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር እየተዘዋወሩ ማስተማር ይችሉ ዘንድ ከገዳሙ ጽ/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተቀብለውታል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓትን ሳይለቁ፣ በመላው ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን አገልግሎት እንዲሰጡ ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ፈቃድ እንደሰጧቸው ይፋዊ ሰነዱ ያስረዳል።
አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ሃይማኖትን ከምግባር፣ ዕውቀትን ከትሕትና፣ እንዲሁም ምስጢርን ከታሪክ ጋር በማዋሃድ እንዲያስተምሩ በቅዱስ ፓትርያርኩ አደራ የተሰጣቸው ሲሆን፤ አሁን በሳክራሜንቶ፣ ካሊፎርኒያ የመሰረቱት አዲስ ገዳም (9249 Folsom Blvd, Sacramento, CA 95826) በውጭው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የቤተ ክርስቲያኒቱ እምነት ተከታዮች ትልቅ መንፈሳዊ መጠለያ፣ የስነ-ልቦና ማዕከል እና የበረከት ምንጭ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ ክንውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሐዋርያዊ ተልእኮ በቆራጥ አባቶች አማካኝነት ድንበር ተሻግሮ ፍሬ እያፈራ ለመሆኑ ማሳያ ሆኗል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአዲሱ የኢራን እቅድ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ጦርነቱን ለመቋጨት ያቀረበችው አዲስ የሰላም እቅድ እንዳላስደሰታቸው ገለጹ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው አሜሪካ አካሄዷን የምትቀይር ከሆነ ኢራን ለዲፕሎማሲ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
የኢራን ዜና ወኪል ‘ኢርና’ ቴህራን በፓኪስታን በኩል አዲስ የድርድር እቅድ ለአሜሪካ ማቅረቧን ትናንት አስታውቆ ነበር። እቅዱ ስለያዛቸው ዝርዝር ጉዳዮች ግን በዘገባው አልተጠቀሰም።
የፓኪስታን ባለሥልጣናት በበኩላቸው የኢራንን አዲስ እቅድ ለአሜሪካ ማድረሳቸውን ገልጸዋል።
አዲስ እቅድ መቅረቡ በተሰማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለጋዜጠኞች አስተያየት የሰጡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ “ስምምነት ላይ መድረስ ይፈልጋሉ። እኔ አልረካሁበትም፤ ስለዚህ የሚፈጠረውን እናያለን” ማለታቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ትራምፕ ትናንት አርብ በዋይት ሐውስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በእቅዱ ውስጥ ያላስተደሰታቸው ጉዳይ ምን እንደሆነ አላብራሩም።
የኢራን አመራር “እጅጉን ተከፋፍሏል” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “ልስማማበት የማልችለውን ነገር እየጠየቁ ነው” ማለታቸውን ሮይተርስ አስነብቧል።
ትራምፕ ከቆይታ በኋላ በፍሎሪዳ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅትም የኢራንን ጉዳይ አንስተዋል። አሜሪካ ከኢራን ጋር የገባችበትን ግጭት በቶሎ ቋጭታ “በተጨማሪ ሦስት ዓመታት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር” እንደማትፈቅድ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈቅዱ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ኢራን ባለፈው ሳምንት ያቀረበችው የሰላም እቅድ የኒውክሌር ጉዳይ ወደ ጎን ተደርጎ የመጀመሪያው ደረጃ ድርድር ጦርነቱን መቋጨት እና ሆርሙዝን መክፈት ላይ እንዲያተኩር የሚጠይቅ ነበር።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው አሜሪካ የያዘችውን “የተለጠጠ አካሄድ፣ የዛቻ ንግግር እና ተንኳሽ ድርጊቶች” የምታቆም ከሆነ አገራቸው ለዲፕሎማሲ ዝግጁ መሆኗን እንደተናገሩ ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህም ቢሆን ግን “የኢራን ጦር ኃይሎች አገሪቱን ከማንኛውም ስጋት ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውን” በቴሌግራም ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል።
BBC

6 months ago
በአሜሪካ "ንጉሥ አንፈልግም" ያሉ ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ
#fastmereja I በአሜሪካ ዋና ዋና ከተሞችና በውጭ አገራት በሚኖሩ አሜሪካውያን ዘንድ "ንጉሥ አንፈልግም" በሚል መሪ ቃል በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ላይ ያነጣጠሩ ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ። ሰልፈኞቹ የትራምፕን የኢራን ፖሊሲ፣ የስደተኞች አያያዝ እና የኑሮ ውድነትን በመቃወም ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተረጋግጧል።
ቅዳሜ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒውዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ሚኒሶታ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል። በተለይም በሚኒሶታ በፌዴራል ወኪሎች የተገደሉ ሁለት ዜጎችን መታሰቢያ በማድረግ የተካሄደው ሰልፍ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። በኒውዮርክ ታይምስ አደባባይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች መገኘታቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።
በሎስ አንጀለስ ሰልፈኞች የፌዴራል ሕንጻን በመክበብ ድንጋይ በመወርወራቸውና ፖሊስን በመተናኮላቸው "ገዳይ ያልሆኑ እርምጃዎች" መወሰዳቸውንና በርካቶች መታሰራቸውን የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ (DHS) ገልጿል። በዳላስም በተቃራኒ ሰልፈኞችና በ"ንጉሥ አንፈልግም" ደጋፊዎች መካከል መጠነኛ ግጭቶች ተከስተዋል።
የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ሰልፎቹን "ከትራምፕ ጋር ችግር ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን የሚያክሙበት መድረክ" ሲሉ አጣጥለውታል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው "ንጉሥ አይደለሁም" በማለት የሚሰነዘርባቸውን የአምባገነንነት ክስ ቀደም ብለው ማስተባበላቸው ይታወሳል።
ተቃውሞው ከአሜሪካ አልፎ በፓሪስ፣ ለንደን እና ሊዝበን በሚኖሩ አሜሪካውያን ዘንድ የቀጠለ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱን "ፋሺስት" እና "የጦር ወንጀለኛ" የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል።

7 months ago
ብዕርና ባሩድ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮፓ ገበያ ላይ ዋለ
#ethiopia | በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አያሌ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት የተመረቀው የአንዱዓለም አራጌ አዲስ መጽሐፍ ብዕርና ባሩድ በአሜሪካ ታትሞ በተለያዩ ከተሞች ለገበያ ቀርቧል።
"ብዕርና ባሩድ" በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሲልቨር ስፕሪንግ፣ በቨርጂኒያ፣ በሂውስተን፣ በዴንቨር፣ በዳላስ፣ በኦክላንድና ሳንሆዜ በሽያጭ ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም በካናዳ ቶሮንቶ ለአንባቢዎች ደርሷል።
በአውሮፓ ደግሞ በጀርመን ፍራንክፈርትና በርሊን፣ በስዊዘርላንድ፣ በሆላንድ አምስተርዳም እንዲሁም በስዊድን ስቶክሆልም ለአንባቢዎች መቅረቡ ታውቋል።
ይህ አዲስ መጽሐፍ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሰንሰለት በጥልቀት የሚፈትሽና ብዙ የሚያወያዩ ቁምነገሮችን የያዘ ሲሆን፣ ለሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄዎችን የሚያመለክት ድንቅ ሥራ መሆኑ ተገልጿል።
መጽሐፉን በኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የአንላይን ተጠቃሚዎችም በቅርቡ በአማዞን ላይ እንደሚጫን ተጠቁሟል።
#ብዕርናባሩድ #አንዱዓለምአራጌ #አዲስመጽሐፍ #ኢትዮጵያ #ፖለቲካ #ሥነጽሑፍ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

8 months ago
‹ተወዳጅ ሚድያ› 22ኛ ዓመቱን ሌሎችን በማመስገን እያከበረ ይገኛል!
በታሪክ ስነዳ፣ በመጽሐፎችና በኹነት ዝግጅት በጋዜጣ ሥራና በሌሎችም የሚታወቀው ‹ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን › 22ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን፣ በየወቅቱ ዐብረው የነበሩ ባለሙያዎችንና ተቋማትን በማመስገን ሊያሳልፍ ነው።
‹ማክበር መሠልጠን ነው› በሚል መሪ አርእስት ከፊት፣ ከጐንና ከጀርባ የነበሩትን የሥራውን ዋና አንቀሳቃሾች ማመስገን ግድና ተገቢ ነው›› ሲል የድርጅቱ መሥራች ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ተናግሯል።
ሰው ሕልም ቢኖረውም፣ እግዚአብሔር ግን ትክክለኛ ዐቅም ያላቸውን ሰዎች ለባለሕልመኛ እንደሚሰጠው የሚያምነው ዕዝራ እጅጉ፣ በእነዚህ ሰዎች ምክንያት ‹ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን › ለዚህ ደረጃ መብቃቱን ይናገራል። ‹ተወዳጅ ሚድያ›፣ በተለይ ባለፉት 9 ዓመታት፣ ለ25 ሰዎች ወቅታዊ የሥራ ዕድሎች የፈጠረ ሲኾን፣ ብዙዎችም ዐቅማቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲጠቀሙና እንዲያውቁ አድርጓል።
የካቲት 2፣ 1996 ዓ.ም በይፋ ሕጋዊ ሰውነቱን አግኝቶ ሥራውን የጀመረው ‹ተወዳጅ ሚድያ›፣ ‹‹ተወዳጅ›› የተሠኘ በነፃ የሚሠራጭ የማስታወቂያ ጋዜጣ በማሳተም ወደ ሚድያው ሥራ ዘልቋል፡፡ ‹‹በጊዜው ሥራው ሲጀምር፣ በየሱቁ እየዞሩ የማስታወቂያ ደንበኞች መፈለጉ ፈታኝ ነበር›› የምትለው የ‹ተወዳጅ› የመጀመሪያዋ ደሞዝ ተከፋይ የሽያጭ ባለሙያ ቅድስት ደበበ ናት። ቅድስት በጊዜው በ500 ብር ደሞዝ ሥራ መጀመሯን የምትናገር ሲኾን፣ ‹‹ከ22 ዓመታት በኋላ ‹ተወዳጅ› ሚድያ ዐዲስ ዐሳብ፣ ብቃትና ዐቅም ያላቸውን ባለሙያዎች አፍርቶ በማየቴ ርካታ ይሰማኛል›› ብላለች።
በአኹኑ ሰዓት ‹ተወዳጅ› ሚድያ ታሪክ በመሰነድ ሥራ ላይ ትኵረት ሰጥቶ ከ23 በላይ መጻሕፍትን ለአንባቢ ማቅረብ ችሏል። በዚህ ብቻ ሳይወሰን፣ 45 ታሪኮችን በሲዲና በዲቪዲ ያቀረበ ሲኾን፣ ልዩ-ልዩ ኹነቶችንም በማዘጋጀት አሻራ ማኖር ችሏል።
‹ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን›፣ በተለይ የሰዎች የሕይወት ታሪክ ከጉግል ላይ በቀላሉ ተፈልጎ እንዲገኝ ሲያደርግ፣ ለዚህ ጥረቱም ዳላስ ከሚገኘው ‹የአርኣያ ሰው› ሽልማት ለማግኘት በቅቷል። እንደ ‹ቻት ጂፒቲ› ያሉ ዘመኑ የወለዳቸው የመረጃ ምንጮችም የ‹ተወዳጅ› ሚድያን ታሪኮች እንደ ተአማኒ የመረጃ ምንጭ አድርገው ይወስዷቸዋል።
‹ተወዳጅ› ሚድያ ለባለሙያ ዕድል በመስጠት የሚያምን ድርጅት መኾኑን መሥራቹ ዕዝራ ያስረዳል፣ ‹‹ልዩ-ልዩ ተቋማትና ግለሰቦች የሚያግዙት፣ ትብብር ለማሳየት ኹሌም ዐብረውት የሚኾኑ ተቋም ነው›› ሲልም ሀሣቡን ገልጿል።
በተለይ ተወዳጅ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ባለፉት 9 ዓመታት ትኵረቱን ሙሉ በሙሉ ታሪክ ላይ በማድረግ ዐዲስ አካኼድና ስልት በመንደፍ የበኩሉን የአገር አሻራ እያኖረ የሚገኝ ድርጅት ነው።
‹ተወዳጅ›፣ ኅትመቶችን ወደ ድምፅ በመቀየር ‹‹የኤርትራ ጕዳይ››ን (አምባሳደር ዘውዴ) የመሰሉ ከ30 በላይ መጽሐፎችንም በትረካ መልክ በማቅረብ በቀላሉ ሰዎች ሥራ እየሠሩና መንገድ ላይ እየኼዱ ማዳመጥ የሚችሉበትን ስልት ነድፏል።
ሚድያው የኢንሳይክሎፒዲያ ፕሮጀክት በመቅረፅ ከሚያዝያ 13፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ‹‹መዝገበ አእምሮ›› የተሠኘውን መጽሐፍ በ2 ቅጽ ያሳተመ ሲኾን፣ በአጠቃላይ የ400 የሚድያና የጥበብ ሰዎችን ታሪክ ይዘዋል፡፡
የአባት የእናቶቻቸው ታሪክ እንዲጻፍ የሚፈልጉ በአገር ውስጥና በባሕር ማዶ የሚገኙ ደንበኞችም ‹ተወዳጅ›ን መርጠው የቤተሰቦቻቸው ታሪክ እንዲሰነድ ያደረጉ ሲኾን፣ እስከ ዛሬም 23 መጽሐፎች ለኅትመት በቅተዋል።መፅሀፍ ከመፃፍ ባሻገርም ደረጃውን የጠበቀ የአርትኦት ተግባር እያከናወነ ይገኛል።
አንድ የቈየ ምስል፣ ሰነድ ወይም ታሪክ አመላካች ወረቀት የቤት ሥርቻ ስር ከሚቀመጥ፣ በ‹ተወዳጅ› ዲጂታይዝ እየተደረገ ሲኾን፣ እስከ ዛሬም ከ10,000 በላይ ፋይሎች በቀላሉ ለትውልድ ተደራሽ እንዲኾኑ ተደርጓል።
‹‹ማክበር መሠልጠን ነው›› በሚል መሪ ዐሳብ ‹ተወዳጅ› ሚድያ እዚህ ለመድረሱ ምስጋና የሚቸራቸው ከ140 በላይ የሚኾኑ ባለሙያዎች፣ ግለሰቦችና ተቋማት በtewedajewikipedia.com ድረ ገጽ በtewedajemedia የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ስማቸው በዝርዝር የተቀመጠ ሲኾን፣ የ22ኛ ዓመት ክብረ በዓሉም ያለምንም ድግስ በማኅበራዊ ድረ ገጾችና በተመረጡ ሬድዮ ጣቢያዎች መረጃዎችን መጥኖና ከፍ አድርጎ በማስተላለፍ እንደሚከበር ታውቋል።
የተመሰገኑ ሰዎችንና ተቋማትን ብሎም 22 የተወዳጅ ሚድያ እውነታዎችን ለማግኘት ሊንኩን ከፍተው ይመልከቱ።https://tewedajewikipedia....

9 months ago
ያልተሰማው ጩኸት፡ የታሚ ሊ ዎከር የመጨረሻ ጉዞ።
👉ባላጠፋው ጥፋት ሞት ተፈርዶበት የተሰቀለው ሰው
የግንቦት ወር 1956 ዓ.ም.። በቴክሳስ የሞት እስር ቤት ውስጥ ያለው አየር በጭንቀት ከብዷል። የአሥራ ዘጠኝ ዓመቱ ወጣት ታሚ ሊ ዎከር በብረት አልጋው ላይ ተቀምጦ ወደ ግድግዳው ያያል። ልቡ እንደ ከበሮ ይመታል፤ ነገር ግን አይኖቹ በእንባ ደርቀዋል። ጥፋቱ ምን እንደሆነ እንኳ በውል በማያውቅበት ሁኔታ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል። ጥፋቱ ጥቁር ሆኖ መፈጠሩ እና በዚያ ክፉ ዘመን በዳላስ ምድር መኖሩ ብቻ ነበር።
የጭለማው ሌሊት ስህተት
ታሪኩ የሚጀምረው መስከረም 30 ቀን 1953 ዓ.ም. ነው። የ31 ዓመቷ ቬኒስ ፓርከር ከስራ ወደ ቤቷ እየተመለሰች በነበረበት ወቅት በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ደረሰባት። በወቅቱ ዳላስ በ"ሰላይ" (Peeping Tom) ፍርሃት ተውጣ ነበር። ፖሊሶች ጥቁር ሰው ፍለጋ ከተማዋን አበጠሯት። በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ጥቁር አሜሪካውያን ያለ ጥፋታቸው ታሰሩ። ከእነዚህም አንዱ ታሚ ሊ ዎከር ነበር።
የ19 ዓመቱ ታሚ በወቅቱ ከሚወደው የሴት ጓደኛው ጋር በሆስፒታል ውስጥ ነበር። ልጃቸው ኤድዋርድ ሊ ስሚዝ ሊወለድ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውት ነበር። የታሚ እጆች የልጁን እጅ ለመጨበጥ እየተዘጋጁ እንጂ በደም ለመጨቅየትስ አልነበረም። ነገር ግን "ፍትህ" የዓይነ ስውርነት ካባዋን አውልቃ የዘረኝነትን መነጽር አጥልቃ ነበር።
የተቀነባበረው ምስክርነት
መርማሪው ዊል ፍሪትዝ የኩ ክሉክስ ክላን (KKK) አባል መሆኑ ዛሬ በግልጽ ታውቋል። ታሚን ለሰዓታት ሲያሰቃየው፣ "ካልተናዘዝክ ትገደላለህ" እያለ ሲያስፈራራው፣ ወጣቱ ታሚ ህይወቱን ለማዳን ሲል ያልፈጸመውን ወንጀል "ፈጽሜያለሁ" ብሎ ፈረመ።
በችሎቱ ላይ የታሚ ጠበቆች 10 ምስክሮችን አቀረቡ። "ታሚ በዚያ ሰዓት ሆስፒታል ነበር" ብለው ምለዉ ተናገሩ። ነገር ግን በዚያ ዘመን፣ በዳላስ ችሎት ውስጥ፣ የአሥር ጥቁር ምስክሮች ቃል ከአንድ ነጭ ፖሊስ የፈጠራ ወሬ በታች ነበር። በሙሉ ነጭ ዳኞች የተዋቀረው ችሎት በደቂቃዎች ውስጥ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።
የመጨረሻው የኤሌክትሪክ ወንበር
ግንቦት 1956። ታሚ ወደ ኤሌክትሪክ ወንበሩ ሲወሰድ እግሮቹ ይንቀጠቀጡ ነበር። ልጁ ገና የሁለት ዓመት ህጻን ነበር። "አላደረግኩትም" የሚለው ጩኸቱ በክፍሉ ግድግዳዎች ላይ ተስተጋብቶ ቀረ። መብራቱ ጠፋ፣ ብልጭታው መጣ... የታሚ ንፁህ ነፍስ ተለየች።
ለ70 ዓመታት የታሚ ስም በ"ነፍሰ ገዳይ" እና "አስገድዶ ደፋሪ" መዝገብ ላይ ሰፍሮ ኖረ። ባለቤቱ ለልጇ ኤድዋርድ ሁልጊዜ የምትነግረው አንድ ነገር ነበር፦ "ልጄ፣ አባትህ ባላደረገው ወንጀል ነው የኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ያስቀመጡት።"
ከ70 ዓመት በኋላ የወጣው እውነት
የፍትህ መዝገብ አቧራውን አራግፎ ሲመረመር፣ ቬኒስ ፓርከር በወቅቱ መናገር እንኳ እንደማትችል፣ ፖሊስ "ጥቁር ሰው ነው" አለች ያለው ምስክርነት የፈጠራ መሆኑ ተረጋገጠ።
የታሚ ልጅ ኤድዋርድ አሁን የ72 ዓመት አዛውንት ነው። ዕድሜውን ሙሉ የአባቱን ስም ለማጥራት ሲታገል ኖሯል።
ባለፈው ረቡዕ በዳላስ ፍርድ ቤት ውስጥ የታየው ትዕይንት ግን የድንጋይን ልብ የሚያቀልጥ ነበር። የታሚ ልጅ ኤድዋርድ እና የተገደለችው የቬኒስ ፓርከር ልጅ ጆሴፍ ፓርከር ፊት ለፊት ተገናኙ።
ጆሴፍ የኤድዋርድን እጅ ይዞ፣ አይን አይኑን እያየ እንዲህ አለው፦
"ስለሆነው ነገር ሁሉ በጣም አዝናለሁ።"
ኤድዋርድም በእንባ ታጥቦ መለሰ፦
"እኔም እናትህን በማጣትህ አዝናለሁ።"
ሁለቱ አዛውንቶች ተቃቀፉ። የ70 ዓመት ቂም፣ ስቃይ እና የፍትህ ጥማት በዚያ እቅፍ ውስጥ የፈሰሰ መሰለ። ፍርድ ቤቱ ታሚ ሊ ዎከር ንፁህ መሆኑን በይፋ አወጀ።
መደምደሚያ
ታሚ ዛሬ የለም። አጥንቱ በምድር ውስጥ ከፈረሰ ቆይቷል። ነገር ግን ዛሬ ስሙ ከጭቃ ወጥቷል። ይህ ታሪክ የሚያስተምረን ፍትህ ቢዘገይም፣ እውነት መቃብር ቆፍራ መውጣቷ እንደማይቀር ነው።
ኤድዋርድ ፍርድ ቤቱን ለቆ ሲወጣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየ። ምናልባትም አባቱ በአንድ ወቅት በግፍ የተነጠቀውን ሰላም ዛሬ አግኝቶ ይሆን? "አባዬ፣ አሁን በሰላም ተኛ" የሚል ይመስላል።

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው
* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል
* የአእላፋት ዝማሬ ቀን የአእላፋት ቅዳሴ ቀን ይሆናል::
* የቅዳሴ ተሰጥዎ ትምህርት ዐቢይ ጾም ላይ ይጀምራል
#ethiopia | 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተካሔደ:: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ የአዲስ አበባ የሐዲያና ሥልጤ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት በዚህ ዝማሬ ላይ የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የጉባኤ መምህራን ፣ ሰባኪያንና ዘማርያን እንዲሁም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ታድመዋል::
የአእላፋት ዝማሬው በጃን እስጢፋኖስ በመሐረነ አብ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን ጸሎተ ወንጌል ደርሶ የዕለቱ ወንጌል በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ ተነብቦ የሰርክ ኪዳን ደርሶአል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዶ/ር አካለ ወልድ ተሰማ የተመራው ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ቃለ ምዕዳን ተከፍቶአል::
ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው "ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ በቅዱስ ያሬድ ዜማ በሊቃውንት ድርሰት በዓለ ልደትን ከዋዜማው በመነሣት ሌሊቱን በቅኔ ማኅሌትና በሥርዓተ ቅዳሴ ሐዋርያዊ ትውፊትን ጠብቃ በዝማሬ ስታከብር ኖራለች ዛሬም እያከበረች ትገኛለች፡፡ ይኽንኑ ፍጹም መንፈሳዊ የሆነ የተቀደሰ ትውፊት መሠረት በማድረግ፣ በጌታችን ልደት በዓልምእመናን በተለይም ወጣቶች ከመንፈሳዊ ሥርዓት ውጭ በአልባሌ ቦታዎች ቀኑንና ሌሊቱን እንዳያሳልፉ፣ መዝሙራትን አጥንተው፣ ከዋክብት ብሩሃንን ሆነው የጌታችንን ልደት በምስጋና ለመቀበል መሰባሰባቸው የሚያስመሰግንና በረከትን የሚያሰጥ የተቀደሰ ተግባር ነው" ብለዋል::
የአእላፋት ዝማሬ መድረክ በጥንታዊው የክብ ቤተ ክርስቲያን ቅርፅ የተሠራ ሲሆን በደመራ ቦታው ላይ ደግሞ የቤተልሔም ግርግምን የልደት የብራና ሥዕል በማድረግ ምእመናን ወደ ተወለደበት ሥፍራ ሕሊናቸውን እንዲመልሱ የሚያደርግ ሆኖአል::
ሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ አብሣሪነት በይፋ የተከፈተ ሲሆን በጃን እስጢፋኖስ ዲያቆናት ወረብ ተከፍቶ ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረዋል:: በሁለተኛ ዙር ከዲያቆናት "መድኃኒነ ተወልደ ነዋ" የሚል ወረብ በማስከተል ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረው በበኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ "እንደ ቸርነትህ" ጸሎት ተደርጎ በሰላም ተጠናቅቆአል:: የአእላፋት ዝማሬው ላይ የታደሙት ምእመናን ቁጥራቸው ከተጠበቀው በላይ ቢሆንም የጸጥታ አካላትን ባስደነቀ ፍጹም ሰላማዊ መንፈስና በእርጋታ ወደየ በአታቸው ሔደዋል:: በዕለቱ የታደሙ ምእመናን የጧፍ መባቸውን ለታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ሠጥተዋል::
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ዘንድሮ በመስቀል አደባባይ ያካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በድኅረ ሁነት ውይይቱ በጥንቃቄ የገመገመ ሲሆን እግዚአብሔር ቢፈቅድ የአእላፋት ዝማሬን ወደ አእላፋት ማሕሌትና የአእላፋት ቅዳሴ ለማሳደግ ሲያወርግ የነበረውን ጥረት በ2019 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ላይ ዕውን ለማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዓን አባቶችን በማማከር ድምዳሜ ላይ ደርሶአል::
የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ መካሔዱ የታየው አዲስ ነገር የአደባባዩ ጠባይ ፣ የተሳታፊው ብዛት ፣ ሰልፍና ፍተሻው የሚወስደው ታሳቢ ሆኖ ጸሎትና ዝማሬው ብቻ አምስት ሰዓታትን የሚወስድ መሆኑ ፣ ሕዝቡ ከአደባባዩ ለመውጣት የሚፈጅበት ጊዜ ከአክፍሎትና ወደየአጥቢያው ለመድረስ ከሚደረግ ጉዞ ጋር አዳጋች እንደሚሆን ተስተውሎአል::
በዚህ ምክንያት ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬ አንድ ቀን ቀድሞ በዋዜማው ዋዜማ እንዲደረግና በዋዜማው ዕለት ደግሞ የአእላፋት ቅዳሴ ዘመቻ እንዲጀመር ተወስኖአል:: ይህ መደረጉም ማሕሌት የሚቆሙ ምእመናን ከአእላፋት ማግሥት ዕረፍት አድርገው እንዲቆሙ ፣ ወደ ቅዱስ ላሊበላና ወደ ሌሎች ቅዱሳት መካናት ጉዞ የሚያደርጉም ተሳትፈው በማግሥቱ በረራዎች እንዲሔዱ እንዲሁም ልደትን በቅዳሴ አሳልፈው የማያውቁም በዋዜማው ዝማሬ መንፈሳቸው ለቅዳሴ እንዲዘጋጅና በየአጥቢያው ሔዶ እንዲያስቀድስ ያበረታታል::
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ቅዳሴ በተሰኘው ፕሮጀክቱ አማካኝነት ቅዳሴ ለማስተማር ትምህርታዊ ቪድዮ ከመማሪያ ሞጁል ጋር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን የአእላፋት ሳምንት ዐውደ ርእይ ላይ በ3D Model የቅዳሴ ትዕይንት ለብዙኃን ማስጎብኘቱም ይታወቃል:: ከመጪው ዐቢይ ጾም ጀምሮ ይህንን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት ለምእመናን በይፋ የሚጀምር ሲሆን በ2019 ዓ.ም. በአእላፋት ዝማሬ ላይ የታደመውን ሕዝብ ያህል በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ ተገኝቶ የዝማሬውን ድምፅ በተሰጥዎ ድምፅ እንዲደግም ለማድረግ ዕቅድ ተይዞአል:: ጃን ቅዳሴ ከ፳፬ቱ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሦስት ዙር የቅዳሴ ተሰጥዎ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቆአል:: በተቋማት ደረጃ የቅዳሴ ተሰጥዎ ለመማር ጥያቄ ላቀረቡ የሙያ ማኅበራትም እንዲሁ ከሥራ ሰዓታቸው ጋር የተስማማ የመማሪያ መርሐ ግብር ነድፎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ ዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ተሻለ ገልጸዋል::
በመስቀል አደባባይ የተካሔደውን ሦስተኛውን የአእላፋት ዝማሬ ከቀደሙት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች እጅግ የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ምእመናን የታደሙበት ሲሆን በኦንላይን ደግሞ ሚልዮኖች ተመልክተውታል:: የEOTC TV ፣ ሀገሬ ቲቪ ፣ አርትስ ቲቪ ፣ ቃና ቲቪ ፣ ፋና ቲቪ ፣ ኢቢሲ ፣ አሶሽየትድ ፕሬስ ፣ BBC ፣ ሮይተርስ ፣ ዶቼቬሌ ፣ ቪዮሪ ቲቪ ፣ ስፖትኔክ ሬድዮ ለሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ ሽፋን የሠጡ ሚድያዎች ናቸው::
የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ
#እንዳላስቀድስ_የሚከለክለኝ_ምንድነው #የአእላፋት_ዝማሬ #ሠረገላው_እንዲቆም_አዘዘ

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው::
ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል
* የአእላፋት ዝማሬ ቀን የአእላፋት ቅዳሴ ቀን ይሆናል::
* የቅዳሴ ተሰጥዎ ትምህርት ዐቢይ ጾም ላይ ይጀምራል
3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተካሔደ:: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ የአዲስ አበባ የሐዲያና ሥልጤ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት በዚህ ዝማሬ ላይ የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የጉባኤ መምህራን ፣ ሰባኪያንና ዘማርያን እንዲሁም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ታድመዋል::

በዚህ ምክንያት ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬ አንድ ቀን ቀድሞ በዋዜማው ዋዜማ እንዲደረግና በዋዜማው ዕለት ደግሞ የአእላፋት ቅዳሴ ዘመቻ እንዲጀመር ተወስኖአል:: ይህ መደረጉም ማሕሌት የሚቆሙ ምእመናን ከአእላፋት ማግሥት ዕረፍት አድርገው እንዲቆሙ ፣ ወደ ቅዱስ ላሊበላና ወደ ሌሎች ቅዱሳት መካናት ጉዞ የሚያደርጉም ተሳትፈው በማግሥቱ በረራዎች እንዲሔዱ እንዲሁም ልደትን በቅዳሴ አሳልፈው የማያውቁም በዋዜማው ዝማሬ መንፈሳቸው ለቅዳሴ እንዲዘጋጅ ያበረታታል::

10 months ago
የሜሲ ዝግጅት በህንድ ምን ገጠመው ?
#ethiopia | አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ሊዮኔል ሜሲ በዛሬው ዕለት ወደ ህንድ በማምራት ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
ሊዮኔል ሜሲ ከደቂቃዎች በፊት በርካታ አድናቂዎቹ በተገኙበት ስታዲየም ተገኝቶ ንግግርም አድርጓል።
ይሁን እንጂ ደጋፊዎቹ ሊዮኔል ሜሲ በፍጥነት እንዲሄድ በመደረጉ እና በቅርበት ሊያዩት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስተዋል።
ደጋፊዎቹ ስታዲየም ለመግባት 130 ዶላር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ሲሆን ሜሲን በ 100 ሜትር ርቀት ላይ እንዲመለከቱ መገደዳቸው እንዳላስደሰታቸው ተነግሯል።
ይህንንም ተከትሎ ደጋፊዎቹ የስታዲየሙን ወንበሮች እና የዝግጅቱን እቃዎች አውድመዋቸዋል።
#ts #sport #gtmc

በአሜሪካ ቨርጂኒያ ስቴት የAlexandria city Nov 30 የወንድወሰን ከበደ ቀን ተብሎ ተሰይሟል
ጋዜጠኛና መድረክ መሪ ወንድወሰን ከበደ በአሜሪካ ዕውቅና ተቀብሏል
ከዕዝራ እጅጉ(ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | በአሜሪካ ቨርጂኒያ ስቴት የAlexandria city Nov 30 የወንድወሰን ከበደ ቀን ተብሎ ተሰይሟል ። ወንድወሰን ከበደ በሚድያ ሥራ ላበረከተው አስተዋፅኦ ነው ክፍለ ግዛቱ ይህን ትልቅ ክብር የሰጠው። ወንድወሰን ከበደ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከተወዳጅ ሚድያ ጋር ባደረገው ቆይታ ይህ ትልቅ ዕውቅና መሆኑን ተናግሯል። የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ መዝገበ አእምሮ ቅፅ ሁለት( ከ6ወር በፊት የታተመው) የወንድወሰንን ታሪክ የሰነደ ሲሆን እኛም ዕውቅናውን አስመልክቶ የሙያ ታሪኩን እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን ።
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ ወንዴ!!!!
ትውልድ ልጅነትና ትምህርት
ወንድወሰን ከበደ በ1964 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሩፋኤል ነው የተወለደው ከአንድ ዓመቱ ጀምሮ እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ ቀጨኔ መድኃኔዓለም መዳረሻ በችሎት ሰፈር ነው ያደገው፡፡
ከጀማሪ ክፍል እስከ አራተኛ ክፍል በቤተልሔም ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ ከዚያም ቤተሰቡ ወደ አዲሱ ቄራ ከገቡ በኋላ ከ5ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ፊት አውራሪ ላቀ አድገህ /ጎፋ/ ትምህርት ቤት ሲማር 8ኛ ክፍል ነፃነት ጮራ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡
የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱ በቴክኒክ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከአዲስ ቴክኒክ ኮሌጅ በጄኔራል መካኒክስ በዲፕሎማ ተመርቋል፣ ከኦ፡አይ፡ሲ፡ኢ ኢንተርናሽናል በከተማ ማስተር ፕላንና በፕላቢንግ ኢንስታሌሽን በሠርተፍኬት ሲመረቅ፣ በአውቶ መካኒክስ ርቀት ትምህርት ቤት ሠርተፍኬት አግኝቷል፡፡
ወደ ሥራ ዓለም
መደበኛ የሥራ ሕይወቱን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚዘጋጁ የንግድ ትርዒቶች፣ ባዛሮችና ፌስቲቫሎች መድረክ በመምራት፣ በማዘጋጀት፣ በማማከርና በማስተባበር፣ የጀመረ ሲሆን፣ ከዚያም ጎን ለጎን በሬዲዮ ፋና በስፖርት ጋዜጠኝነትና በዜና አንባቢነት ተቀጥሮ ለሰባት ዓመታት አገልግሏል፡፡
በስፖርት ጋዜጠኝነት ከዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ /IOC/ ያዘጋጀውን ሥልጠና ወስዶ ሠርተፍኬት ተቀብሏል፡፡
በርካታ የጋዜጠኝነትና የኮሙዩኒኬሽን ሥልጠናዎችን በሚገባ ተከታትሎ ሠርተፍኬቶችን አግኝቷል፡፡
"ጉራማይሌ" የተሰኘ አጫጭር ድራማዎችና የባህል ሙዚቃዎችን የያዘ ቪዲዮ ፕሮዲዩስ አድርጓል፡፡
WBK የተሰኘ የማስታወቂያ ድርጅት አቋቁሞ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያዎችንና የድርጅቶች ዶክመንተሪ ሠርቷል፡፡
እጅግ በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በኤግዚቢሽን ማዕከል፣ በመስቀል አደባባይና በሐዋሳ ከተማና በተለያዩ ሥፍራዎች መርቷል፡፡
የፀጋዬ እሸቱ የሙዚቃ ወዳጆች ማኅበር በሚል ለትርፍ ያልተቋቋመ ማኅበር መሥርቶ ከሁለት ሺሕ መነሻ አድርጎ እስከ አሥር ሺሕ በሚጠጉ ወላጅ አልባ ሕፃናትንና ደካማ ወገኖችን አሰባስቦ ለበዓላት በመመገብ፣ የተማሪዎችን የትምህርት ወጪና ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡
የኪነ ጥበብ ዝንባሌ
በልጅነቱ ዓለም አቀፍ ሬዲዮ (ብሥራተ ወንጌል) ለገዳዲ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ፕሮግራሞችንና ዜናዎችን ይከታተል የነበረ ሲሆን የሃይስኩል ተማሪ ሳለ በሚኒሚዲያ ውስጥ አገልግሏል፣ ከዚያም ለሬዲዮኖች መጣጥፎችን በመላክ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡
ወንድወሰን ከበደ ባለትዳርና ሁለት የሃይስኩል ተማሪ ልጆች ያለው ሲሆን ነዋሪነቱ በሰሜን አሜሪካ በሜሪላንድ ግዛት ነው፡፡
ወንድወሰን ከበደ ኑሮውን በአሜካን አገር ካደረገ ሃያ ዓመት ሆኖታል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በቨርጂኒያ፣ በሜሪላንድ፣ በሲያትል፣ በሎስአንጀለስ፣ በአትላንታ፣ በዳላስ፣ በዴንቨር፣ በተካሄዱ ትልልቅ መድረኮችን በመምራት፣ በማዘጋጀትና በማስተባበር ሠርቷል፡፡ አሁንም በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
በሰሜን አሜሪካ ብቸኛ የስፖርት ሬዲዮ በመክፈት ልዩ ሬዲዮ በሚል ለአምስት ዓመታት አገልግሏል፡፡
ኢትዮጵያ ናሽናል ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ /ENBS/ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሌሎች ባልደረቦች ጋር በማቋቋም በአሜሪካን የቴሌቪዥን ቻናል WHUT ያስተላልፍ ነበር፡፡
ሰንደቅ ሚዲያ የተሰኘ ከአንድ ባልደረባው በማቋቋም ለሁለት ዓመታትም ሠርቷል፡፡ በENT ሚዲያ ላይም ለተወሰኑ ወራቶች አገልግሏል፡፡
ከ ስድስት ወር በፊትም መድረክ ሲመራ ያሰባሰባቸውን ምስሎች በመፅሀፍ ፅፎ አስመርቋል ።
መጽሐፍ
- በቅርቡ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ከ1980ዎቹ እስከ 1990ዎቹ የሚል በበርካታ ምስሎችና ታሪኮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ለአንባቢ ያበረክታል፡፡
- ግለ ታሪኩ በተመለከተ ቀጣይ የሚኖረው መጽሐፍ ነው፡፡
በቅርቡ
- ትዳር በአሜሪካ የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ
- ከባልደረቦቹ ጋር እየተቋቋም ባለ አዲስ ሚዲያ በልዩ አቀራረብ ይመጣል፡፡
- 1980ዎቹ/1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በተመለከተ ልዩ ተከታታይ የቪዲዮ ቅንብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

11 months ago
«ድል አባቷ ብዙ ነው" - ጆኔፍ ኬኔዲ
🌎 እኔም ሀገር አለኝ የሚታይ በሩቁ ...
የጉዞ ማስታወሻ ✈️
#ethiopia | በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
የቀድሞው ዝነኛና ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቴክሳስ ግዛት፣ ዳላስ ከተማ፣ በክፍት መኪና፤ በጉብኝት ሳሉ ነበር እኤአ በኅዳር 22፣ 1963 ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት። ፕሬዚደንት ኬኔዲ ስልጣን ላይ ከወጡ ሦስተኛ ዓመታቸን ሊይዙ ትንሽ ወራት ይቀራቸው ነበር።
ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ሰውየውን ( ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ) ማን ገደላቸው? ... ለምን ተገደሉ? ... በሚለው ዙርያ ሺህ ምርመራዎች ተደርገዋል።
እነዚህ የምርመራ ሂደቱን የያዙ ዶሴዎችም በምሥጢር ሲከማቹ ነው የኖሩት።
የ1964 የእውነት አፈላላጊው ‘ዋረን ኮሚሽን’ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የተገደሉት ሊ ሐርቬይ ኦስዋልድ በተባለ ግለሰብ ነው ብሎ ነበር።
ሊ ሐርቬይ ቀደም ሲል በሶቭየት ኅብረት ለአጭር ጊዜ የኖረ አሜሪካዊ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመውም በግሉ ነው ተብሎ ነበር።
በቁጥጥር ሥር በዋለ በሁለተኛው ቀን ግን ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ በዳላስ ፖሊስ ምድር ቤት ውስጥ ተገድሏል።
ይሁንና የኬኔዲ አገዳደል፣ ገዳያቸው ነበር የተባለው ሰው በፖሊስ ምድር ቤት መገደል ምሥጢርና ተያያዥ ጉዳዮች ለዐሥርታት ለብዙ መላምቶች ክፍት ሆኖ ቆይቷል።
የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ግድያውንና ግድያውን ተከትሎ የሆነውን ነገር ሁሉ የተለያዩ ትርጉም ሲሰጡት ኖረዋል። ዛሬም ድረስ ...
አንዳንዶች ወጣቱን ፕሬዝዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሴአይኤ ራሱ ነው፤ ለዚያም ነው ገዳያቸው ነው የተባለውን ሰው ፈጥነው የገደሉት ብለው ያምናሉ።
ሲአይኤ ግን "የኔ እጅ የለበትም!" ይላል።
ገዳያቸው ነው የተባለው ኦስዋልድ በሜክሲኮ አገር ከኬጂቢ ሰላይ ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ወደ በኋላ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመጀመርያው የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታይ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጊዜያቸው ገናና የነበሩ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም ባሻገር በንግግር አዋቂነታቸው ይደነቃሉ።
ከንግግራቸው አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እንደ ጥቅስ ይወሳሉ፤ ከነዚህም መሀል ‘አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ’ የሚለው የበዓለ ሲመት ንግግራቸው በይበልጥ ይታወሳል።
***
እንደምታውቁት የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ግድያ የተመለከተ የምርመራ ዶሴ ከ60 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ይህ ዶሴ ለሕዝብ ይፋ እየሆነ ያለው ከ60 ዓመታት ጥብቅ ምሥጢርነት በኋላ ነው።
ብዛቱ ከ10ሺህ በላይ ይሆናል የተባለው ይህ ሰነድ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ናቸው።
ይሁንና አንዳንድ ሰነዶች አሁንም በምሥጢር የሚቆዩ ይኖራሉ። ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ደኀንነት ሲባል ነው።
ምንም እንኳ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ለዐሥርታት እያወዛገበ ቢቆይም በዚህ ሰነድ የሚገለጥ አንዳች ታላቅ ምሥጢር ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ይሁንና ዶሴው በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዙርያ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግን ልዩ ዕድል ነው ተብሏል።
የ1992 የአሜሪካ ሕግ ዶሴዎቹ በጥቅምት 2017 ለሕዝብ ይፋ እንዲደረጉ አስገዳጅ አድርጎ ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የማይደረጉት ሰነዶች ብዛት 515 ነው ብሏል።
ከጠቅላላው ሰነድ 2ሺህ 545 ሰነዶች ደግሞ ይፋ የሚሆኑት በከፊል ናቸው።
***
ታሪክን የኋሊት
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸዉ። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል።
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
«ድል አባቷ ብዙ ነው" እንዲል ጆኔፍ ኬኔዲ ብዙ የታሪክ ምዕራፍ ለመሰነቅ ወደ ሙዚየሙ ገባሁ።
The joy and excitement of John Fitzgerald Kennedy's life belonged to all men.
So did the pain and sorrow of his death.
When he died on November 22, 1963, shock and agony touched human conscience throughout the world. In Dallas, Texas, there was a special sorrow.
The young President died in Dallas. The death bullets were fired 200 yards west of this site.
by Philip Johnson, This memorial, designed by was erected by the people by the people of Dallas. Thousands of citizens contributed support, money and effort.
It is not a memorial to the pain and sorrow of death, but stands as a permanent tribute to the joy and excitement of one man's life.
Pohn Fitzgerald Kennedy's life.
***
የዓይን ነገር በዳላስ
ዓይን በአሜሪካዊው አርቲስት ቶኒ ታሴት የሁለት ቅርፃ ቅርጾች ርዕስ ነው። ትላልቅ ዓይኖች ሰማያዊ አይሪስ ያላቸው እና ከፋይበርግላስ፣ ሙጫ እና ከብረት በዘይት ቀለም የተዘረዘሩ ናቸው። የዓይን ሐውልት የመጀመሪያው በ2007 የተሰራው በ12 ጫማ (3.7 ሜትር) ዲያሜትር ሲሆን በሴንት ሉዊስ፣ ሚዙሪ ውስጥ በላሜየር ቅርፃ ቅርፅ ፓርክ ይገኛል። ሁለተኛው እ.ኤ.አ. በ 2010 በ 30 ጫማ (9.1 ሜትር) ዲያሜትር የተሰራ እና በአሁኑ ጊዜ በዳላስ ፣ ቴክሳስ ውስጥ በThe Joule ሆቴል ባለቤትነት ይተዳደራል።
እኔና መንጌ ( በዳላስ - የክብር ስፖንሰሬ) ጉብኝቱን አቋርጠን የ“ቶክ ዳላስ “(talk Dallas)
***
ጋዜጠኛና ደራሲ መሐመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ መሓሙድ ጋ ጠቢቅኝ›› (2004) "ትዝታዋ የቀረው የፒያሳዋ ዳላስ" ጣፋጭ ሥራው ትዝ አለችኝ።
ፍቅረኛህን "ማሀሙድ ጋር ጠብቂኝ" ስትላት ተሳስታ ማዶ ተሻግራ ከጠበቀችህ እድለኛ ናት፡፡ ካንተ በላይ የሚያስደስቷትን ሙዚቃዎች እየሰማች ነው ማለት ነው፡፡ ከዳላስ ሙዚቃ ቤት፡፡ ይህ ቤት የየመን ዝርያ ባላቸው ሐበሾች የተያዘ ነው፡፡ ከፒያሳ ፍቅር እንዲይዝህ ከሚያስችሉ አዚሞች አንዱ ነው፤ ዳላስ፡፡
በማለዳ ፒያሳ ከመጣህ በነ‹‹ያኒ›› ዜማ ትታደሳለህ፡፡ በሩቅ ምሥራቅ ረቂቅ ሙዚቃዎች ትፈወሳለህ፡፡ ረፋድ ላይ ፒያሳ ከደረስክ በነ መሀመድ ወርዲ፣ በነ አህመድ ሙስጠፋ፣ በነ ከማል ተርባስ በነ ሳይድ ከሊፋ ሱዳንኛ ዜማ ትደንሳለህ፡፡ በሱዳን ዜማ ለመደነስ አትሽኮርመም እንኳን አንተ ጠቅላይሚኒስትርህም ደንሰዋል፡፡
ከቀትር በኋላ ፒያሳን ከረገጥክ ደግሞ ዳላስ በብሉይየእንግሊዝኛ ሙዚቃዎች አቅልህን ያስትሃል፡፡ በነ ሳም ኩክ፣ በነ ሬይ ቻርለስ፣ በነ ኢታ ጀምስ፣ በነ ዶና ሰመር፣ በነ ዳያና ሮዝ፣ በነ ማርቪንጌ፣ በነ ቲና ቻርለስ፣ በነ ሮድ ስቴዋርት ዜማዎች ትሰክራለህ፤ ትሳከራለህ፡፡ ደግሞ ማምሻ ላይ እነ ዶን ዊሊያምስ፣ እነ አለን ጃክሰን፣ እነ ሩኒ ሚልሳፕ፣ እነ ዶሊ ፓርተን፣ እነ ኬኒ ሮጀርስ በአገረ-ሰብ ሙዚቃ አለምህን ያስቀጩኻል፡፡
ዳላስ ብሉይ በኾኑ ነገር ግን በሚጣፍጡ ሙዚቃዎች የፒያሳን ዜጎች የማዝናናት ተግባር ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሳይታክት ጆሮ ገብ ሙዚቃዎችን ያስኮመኩማል፡፡ በነፃ!
ከዚህ ቤት የሚደመጡ ሙዚቃዎች ዘፋኞቹ በሕይወት የሌሉ ወይም ደግሞ ዘፋኞቹ ራሳቸው የረሷቸው ሙዚቃዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ‹‹ኦልዲስ-በት-ጉዲስ››፡፡ ታዲያ በቲቪ የምታውቀው ጥቃቅንና አነስተኛ ጀማሪ ዘፋኝ እዚህ ዳላስ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሲያንዣብብ ካየኽው አንድ ነገር ጠርጥር፡፡ ሊከትፍ ወይ ሊመነትፍ ነው፡፡
ዳላስ በብሉይ ሙዚቃዎች በይበልጥ ይታወቅ እንጂ በዓለም ላይ ዝናው ከፍ ያለ የሮክ፣ የጃዝ፣ የብሉዝ ወዘተ ሙዚቀኛን ሲዲ በመያዝም ይታወቃል፡፡ ዳላስ ገብተህ በትክክል የዘፈን ስም ከጠራህ ሲዲው ያለምንም ጥርጥር ይሰጥኻል፡፡ ድንገት እንኳ ሲዲው አልቆ ቢኾን ስለ አቀንቃኙ አንዳንድ ማብራሪያዎች ተሰጥቶህ ሌላ ጊዜ ብትመለስ ግን ሲዲው ከነልባሱ እንደሚዘጋጅልህ ተነግሮህ ነው የምትሰናበተው፡፡ ዳላስ ከተወለደ ጀምሮ ሙዚቃ አድናቂን አስቀይሞ አያውቅም፡፡ ሙዚቃ በእውቀት የሚነገድበት ቤት ነው፡፡
በነገርህ ላይ እዚያ አካባቢ የሚሠሩ የታክሲ ወያላዎች ዳላስ ሙዚቃ ቤት ተፅዕኖ ስላሳደረባቸው ይመስለኛል ተሳፋሪ ሲጠሩ ራሱ በዜማ ነው፡፡ የወያላዎቹን ድምፅ በደንብ አስተውህ ካዳመጥከው ሙዚቃዊ ቅላፄ አለው፡፡ ይስረቀረቃል፡፡ ‹‹22 ካዛንቺስ…መገናኛ!!!...መገናኛ ካዛንቺስ 22!!፣ አምስት ኪሎ..…ቅድስት ማርያም...አምስት ኪሎ!!!››
ፒያሳ ከመጣህ እንደ ወይን እያደር የሚጣፍጥ ዘፈኖችን ከዳላስ ሙዚቃ ዘወትር ትኮመኩማለህ፡፡ አምስት ሳንቲም ሳትከፍል፡፡ በዚህ ዘመን አንድን ሙዚቃ ሦስት ታክሲ ውስጥ ተከፍቶ ከሰማኸው እጅ እጅ ማለት እንደሚጀመር አንተም ሳትገነዘብ የቀረህ አይመስለኝም፡፡ የድሮ ሙዚቃ ግን ውብ ነው፡፡ ሄዶ ልብህ ላይ ነው የሚቀመጠው፡፡ አይጎረብጥህም፡፡ ካላመንከኝ ፒያሳ ዳላስ ሙዚቃ ቤት ደጅ ላይ ተሰየም፡፡
አንድ ድረ-ገጽ አንባቢዬ ዳላስ ሙዚቃ ቤትን እንዴት ገለጸው
A "The soundtrack of Piassa"
***
የደራሲና ዳይሬክተር ዮሐንስ ፈለቀ ( Yoni Cash ) እና ተገኔ ( እንደስሙ ተገን✈️
በእዝነ ልቦና ሀገር ቤት ገብቼ ነበር።
የተወዳጇ፤ የሶል ንግሥቷ አስቴር አወቀ "ሀገሬ" አልበም ከፍ ብሎ ይሰማኝ ነበር።
"ይሄም ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ....❣️
Sponsored by
Surafel
Comments