በመኰንን ሸገኔ ስም ሽልማት ተሰየመ
(ከዕዝራ እጅጉ)
#ethiopia | በርካታ ተማሪዎችን ባፈሩት ፣ ከ 50 አመት በፊት ሕይወታቸው ባለፈው በመምህር መኮንን ሸገኔ ስም ሽልማት ተሰየመ።
የአርአያ ሰው ሽልማት ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ዲያቆን ፍሬው ሰይፉ ለተወዳጅ ሚድያ እንደተናገሩት በየዓመቱ በሚሰጠው የአርአያ ሰው ሽልማት ላይ ዘንድሮ ነሐሴ 16 2018 ዓ.ም በተደረገው ሥነ ሥርዓት ሽልማቱ መታሰቢያ የተደረገው ለመምህር መኮንን ሸገኔ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በየአመቱ 'የመኮንን ሸገኔ ሽልማት' በሚል ዘርፍ ለተለያዩ ሰዎች እውቅና እንደሚሰጥ ታውቋል።
የሽልማት ሥነሥርዓቱ ቅዳሜ ነሐሴ 16 2018 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ የተደረገ ሲሆን የመኮንን ሸገኔ ቤተሰቦችም በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
የአባቷን ታሪክ በማፃፍና ለቁምነገር እንዲበቃ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣችው ልጃቸው ካቢው መኮንን ሸገኔ ስትሆን የዛሬ አመት በሰኔ 2017 ዓ.ም መኮንን ሸገኔ የሀገር ባለውለታ" የሚል መጽሐፍ በዕዝራ እጅጉ ተፅፎ መመረቁ ይታወቃል።
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ጨምሮ በርካታ ምሁራንን ለወግ ማዕረግ ያበቁት መምህር መኮንን በአገር ውስጥ እና በባህር ማዶ በሚገኙ ተማሪዎቻቸው ዘንድ የሚወደዱ እና የሚከበሩ እንደሆኑ ይታወቃል።ተማሪዎቻቸውም በዕለቱ የማስታወሻ ስጦታ ለቤተሰቡ እንዳበረከቱ ታውቋል።
መኰንን ሸገኔ፣ የዛሬ 49 ዓመት ሕይወታቸው ያለፈ የዳግማዊ ምኒሊክ፣የድሬደዋ ልዑል መኰንን ፣እና የአዲስ አበባ ልዑል መኰንን ትምህርት ቤቶች ርዕሰ- መምህር የነበሩ ሲሆን በሥራ ላይ ሳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።
ህይወታቸው ሲያልፍ ገና የ5 ዓመት ልጅ የነበረችው ካቢው መኮንንም አባቴ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያዊያን አባት ነው ብላ በማመን ስለ አባቷ ለትውልዱ አንድ አሻራ ለማኖር መነሳቷን ትናገራለች። የአርአያ ሰው ሽልማትም ለመኮንን ሸገኔ ለሰጠው ዕውቅናም ምስጋናዋን አቅርባለች።
በዳላስ በተደረገው የእውቅና ሥነ -ሥርዓት የመኮንን ሸገኔ ቤተሰቦችን ጨምሮ ከተለያዩ ክፍለ -ግዛቶች የመጡ የቀድሞ ተማሪዎች ታድመዋል።
በዳላስ የተሰጠው የአርአያ ሰው ሽልማት ከተመሠረተ 10 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን' እናቀዳድማለን እንጂ አናወዳድርም' የሚለውን መርህ አንግቦ ዘንድሮ ለአገር ባለውለታዎች እውቅና ሰጥቷል። በዕለቱ ሌሎች 9 ባለውለታዎችም በአርአያ ሰው የሽልማት ፋውንዴሽን ዕውቅናው የተበረከተላቸው ሲሆን መርሀ ግብሩም በልዩ ድምቀት እንደተሰናዳ በዳላስ የሚገኘው የተወዳጅ ሚድያ ዘጋቢ አስታውቋል።
ዘጠኙ ዕውቅና የተበረከተላቸው ሰዎች ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ (ላገር በሰሩት ሥራ የኮሎኔል ካሣ ገብረማሪያምን ሽልማት አገኙ)፣ ሐጂ ራህመቶ ሙክታር (የክብር ተሸላሚ፣አርቲስት የትናየት ታምሩ በኪነጥበብ ዘርፍ ፣አቶ ተስፋልደት በላይ ተክሉ የአባታቸውን ሌጋሲ በማስቀጠል፣የቲ እሳቱ፣አኒሳ አደም፣ቶማስ አበበ፣በማህበራዊ ኃላፊነት መወጣት ሲሸለሙ ማህደር ገብረሥላሴ የአመቱ ምርጥ ሬስቶራንት ዘርፍ አሸንፋለች። በተጨማሪም ሊያ ስዩም የህይወት ዘመን ሽልማት ስታገኝ ህፃን ካሳ ሀይሉ ደግሞ ተስፋ የተጣለበት ዘርፍ ላይ ዕውቅናው እንደተበረከተለት ታውቋል።ከተቋማት ደግሞ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ስትሪም ኦፍ ሆፕ በዕለቱ ተመስግኗል።
#የአርአያሰውሽልማት #መምህርመኮንንሸገኔ #ዳላስ #ትምህርት #ዕውቅና #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago