በአሜሪካ ቨርጂኒያ ስቴት የAlexandria city Nov 30 የወንድወሰን ከበደ ቀን ተብሎ ተሰይሟል
ጋዜጠኛና መድረክ መሪ ወንድወሰን ከበደ በአሜሪካ ዕውቅና ተቀብሏል
ከዕዝራ እጅጉ(ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | በአሜሪካ ቨርጂኒያ ስቴት የAlexandria city Nov 30 የወንድወሰን ከበደ ቀን ተብሎ ተሰይሟል ። ወንድወሰን ከበደ በሚድያ ሥራ ላበረከተው አስተዋፅኦ ነው ክፍለ ግዛቱ ይህን ትልቅ ክብር የሰጠው። ወንድወሰን ከበደ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከተወዳጅ ሚድያ ጋር ባደረገው ቆይታ ይህ ትልቅ ዕውቅና መሆኑን ተናግሯል። የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ መዝገበ አእምሮ ቅፅ ሁለት( ከ6ወር በፊት የታተመው) የወንድወሰንን ታሪክ የሰነደ ሲሆን እኛም ዕውቅናውን አስመልክቶ የሙያ ታሪኩን እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን ።
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ ወንዴ!!!!
ትውልድ ልጅነትና ትምህርት
ወንድወሰን ከበደ በ1964 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ሩፋኤል ነው የተወለደው ከአንድ ዓመቱ ጀምሮ እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ ቀጨኔ መድኃኔዓለም መዳረሻ በችሎት ሰፈር ነው ያደገው፡፡
ከጀማሪ ክፍል እስከ አራተኛ ክፍል በቤተልሔም ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ ከዚያም ቤተሰቡ ወደ አዲሱ ቄራ ከገቡ በኋላ ከ5ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ፊት አውራሪ ላቀ አድገህ /ጎፋ/ ትምህርት ቤት ሲማር 8ኛ ክፍል ነፃነት ጮራ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡
የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱ በቴክኒክ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከአዲስ ቴክኒክ ኮሌጅ በጄኔራል መካኒክስ በዲፕሎማ ተመርቋል፣ ከኦ፡አይ፡ሲ፡ኢ ኢንተርናሽናል በከተማ ማስተር ፕላንና በፕላቢንግ ኢንስታሌሽን በሠርተፍኬት ሲመረቅ፣ በአውቶ መካኒክስ ርቀት ትምህርት ቤት ሠርተፍኬት አግኝቷል፡፡
ወደ ሥራ ዓለም
መደበኛ የሥራ ሕይወቱን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚዘጋጁ የንግድ ትርዒቶች፣ ባዛሮችና ፌስቲቫሎች መድረክ በመምራት፣ በማዘጋጀት፣ በማማከርና በማስተባበር፣ የጀመረ ሲሆን፣ ከዚያም ጎን ለጎን በሬዲዮ ፋና በስፖርት ጋዜጠኝነትና በዜና አንባቢነት ተቀጥሮ ለሰባት ዓመታት አገልግሏል፡፡
በስፖርት ጋዜጠኝነት ከዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ /IOC/ ያዘጋጀውን ሥልጠና ወስዶ ሠርተፍኬት ተቀብሏል፡፡
በርካታ የጋዜጠኝነትና የኮሙዩኒኬሽን ሥልጠናዎችን በሚገባ ተከታትሎ ሠርተፍኬቶችን አግኝቷል፡፡
"ጉራማይሌ" የተሰኘ አጫጭር ድራማዎችና የባህል ሙዚቃዎችን የያዘ ቪዲዮ ፕሮዲዩስ አድርጓል፡፡
WBK የተሰኘ የማስታወቂያ ድርጅት አቋቁሞ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ማስታወቂያዎችንና የድርጅቶች ዶክመንተሪ ሠርቷል፡፡
እጅግ በርካታ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በኤግዚቢሽን ማዕከል፣ በመስቀል አደባባይና በሐዋሳ ከተማና በተለያዩ ሥፍራዎች መርቷል፡፡
የፀጋዬ እሸቱ የሙዚቃ ወዳጆች ማኅበር በሚል ለትርፍ ያልተቋቋመ ማኅበር መሥርቶ ከሁለት ሺሕ መነሻ አድርጎ እስከ አሥር ሺሕ በሚጠጉ ወላጅ አልባ ሕፃናትንና ደካማ ወገኖችን አሰባስቦ ለበዓላት በመመገብ፣ የተማሪዎችን የትምህርት ወጪና ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ አመቻችቷል፡፡
የኪነ ጥበብ ዝንባሌ
በልጅነቱ ዓለም አቀፍ ሬዲዮ (ብሥራተ ወንጌል) ለገዳዲ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ፕሮግራሞችንና ዜናዎችን ይከታተል የነበረ ሲሆን የሃይስኩል ተማሪ ሳለ በሚኒሚዲያ ውስጥ አገልግሏል፣ ከዚያም ለሬዲዮኖች መጣጥፎችን በመላክ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡
ወንድወሰን ከበደ ባለትዳርና ሁለት የሃይስኩል ተማሪ ልጆች ያለው ሲሆን ነዋሪነቱ በሰሜን አሜሪካ በሜሪላንድ ግዛት ነው፡፡
ወንድወሰን ከበደ ኑሮውን በአሜካን አገር ካደረገ ሃያ ዓመት ሆኖታል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በቨርጂኒያ፣ በሜሪላንድ፣ በሲያትል፣ በሎስአንጀለስ፣ በአትላንታ፣ በዳላስ፣ በዴንቨር፣ በተካሄዱ ትልልቅ መድረኮችን በመምራት፣ በማዘጋጀትና በማስተባበር ሠርቷል፡፡ አሁንም በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
በሰሜን አሜሪካ ብቸኛ የስፖርት ሬዲዮ በመክፈት ልዩ ሬዲዮ በሚል ለአምስት ዓመታት አገልግሏል፡፡
ኢትዮጵያ ናሽናል ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ /ENBS/ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከሌሎች ባልደረቦች ጋር በማቋቋም በአሜሪካን የቴሌቪዥን ቻናል WHUT ያስተላልፍ ነበር፡፡
ሰንደቅ ሚዲያ የተሰኘ ከአንድ ባልደረባው በማቋቋም ለሁለት ዓመታትም ሠርቷል፡፡ በENT ሚዲያ ላይም ለተወሰኑ ወራቶች አገልግሏል፡፡
ከ ስድስት ወር በፊትም መድረክ ሲመራ ያሰባሰባቸውን ምስሎች በመፅሀፍ ፅፎ አስመርቋል ።
መጽሐፍ
- በቅርቡ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ከ1980ዎቹ እስከ 1990ዎቹ የሚል በበርካታ ምስሎችና ታሪኮች የተዘጋጀ መጽሐፍ ለአንባቢ ያበረክታል፡፡
- ግለ ታሪኩ በተመለከተ ቀጣይ የሚኖረው መጽሐፍ ነው፡፡
በቅርቡ
- ትዳር በአሜሪካ የተሰኘ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ
- ከባልደረቦቹ ጋር እየተቋቋም ባለ አዲስ ሚዲያ በልዩ አቀራረብ ይመጣል፡፡
- 1980ዎቹ/1990ዎቹ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በተመለከተ ልዩ ተከታታይ የቪዲዮ ቅንብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡

10 months ago