1 month ago
ዱራሜ ዝግጁ ነው?
የ"ኮከቡ ሰው" ትያትር በዱራሜ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | በታዋቂ የመድረክ ሥራው "ኮከቡ ሰው" ትያትር በዱራሜ ከተማ ለተመልካቾች ሊቀርብ መሆኑ ተገለጸ።
ዝግጅቱ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በከምባታ ዞን ባህል አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፣ የትያትር አፍቃሪዎች በስፍራው ተገኝተው እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።
የመግቢያ ትኬት ዋጋ
ለመደበኛ 300 ብር እና
ለVIP 500 ብር ሲሆን፣ ትኬቶችን በመሳላ ሆቴል እንግዳ መቀበያ ቢሮ ማግኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃና ትኬት ቅድመ ቦታ ማስያዝ
በ +251902917692 ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል።
ዝግጅቱን ያዘጋጀችው ቤቲ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ስትሆን፣ በከተማዋ የባህልና የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ዝግጅት መሆኑ ተጠቁሟል።

4 months ago
የሀምበሪቾ 777 ደረጃ የተራራ ላይ ውድድር! 🏃♂️💨
ሀምበሪቾ 777 ተራራ ብቻ አይደለም፤ የታታሪነታችንና የጥንካሬያችን አርማ ነው!" በሚል መሪ ቃል፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የሚገኘው ድንቁ የሀምበሪቾ ተራራ፣ ታላቅና ታሪካዊ የተራራ ላይ የደረጃ ውድድር ሊያስተናግድ ቀጠሮ ተይዟል።
ይህ ውድድር የሰው ልጅ ጽናትና የተፈጥሮ ውበት የሚገናኙበት፣ የከምባታ ህዝብ ኩራት ለዓለም የሚታይበት ልዩ መድረክ ነው!
ፈታኙ የ777 ደረጃዎች ጉዞ፦
ተወዳዳሪዎች ከተራራው ግርጌ ካለው ለምለሙ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ ተነስተው፣ የ 777ቱን አስደናቂ ደረጃዎች በመርገጥ የተራራውን አናት ቀድመው ለመርገጥ ብቃታቸውን ይፈትናሉ። ይህ በአፍሪካ ደረጃ ለየት ያለ የከፍታ ሩጫ (Vertical Race) ተሞክሮን ይሰጣል።
ዳጎስ ያለና አበረታች ሽልማት፦
ለጽናታቸው አሸናፊዎች (ለወንድም ለሴትም) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ማራኪ የገንዘብ ሽልማት፣ የክብር ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል።
የኪነ-ጥበብና የባህል ድግስ፦
በተራራው አናት ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የባህል ቡድኖች፣ የከምባታ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ አልባሳትና የጥበብ ስራዎች ለታዳሚው በድምቀት ይቀርባሉ።
የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ስህበት፦
ውድድሩ ሀምበሪቾን በዓለም አቀፍ የስፖርት ቱሪዝም ካርታ ላይ ለማስፈርና አካባቢውን ለኢንቨስትመንት ምቹ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ሰንቋል።
👕 የውድድሩ ቲሸርቶችና ምዝገባ፦
ልዩ ዲዛይን ያላቸው ቲሸርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተዘጋጅተዋል። ቲሸርቶቹን በመግዛት የውድድሩ ተሳታፊ መሆን ይቻላል።
ቲሸርቶቹን ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የዞኑ ከተሞች በሚገኙ መሸጫ ጣቢያዎች ያገኛሉ!
የዕለቱ መርሃ-ግብር መረጃ፦
ቀን፦ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
መነሻ ቦታ፦ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ (ከተራራው ግርጌ)
መድረሻ ቦታ፦ የሀምበሪቾ ተራራ አናት (777ኛው ደረጃ)
አድራሻ፦ ዱራሜ ከተማ፣ ከምባታ ዞን
ኑ!
የታሪክ አካል ይሁኑ! Betty Event Organizer (ቤቲ ፕሮሞሺን) ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ይህንን ዝግጅት በላቀ ጥራት አሰናድተው ይጠብቁዎታል።
📞 ለበለጠ መረጃ፣
ለምዝገባና ለቲሸርት ትዕዛዝ በዚህ ስልክ ይደውሉ፦ 0902917695
ሀምበሪቾ 777 -
ወደ የከፍታ የምንወጣበት፣ ኩራታችንን ለዓለም የምናሳይበት!
#hambericho777 #hamberichostairsrace #777stepchallenge #mounthambericho #durame #kambata #centralethiopia #visitethiopia #mountainrace #bettyevents #athleticsethiopia #ethiopia #ሀምበሪቾ777 #ደረጃሩጫ #ከምባታ #ዱራሜ #ቱሪዝም #ጌጡተመስገን #getutemesgen #getu

8 months ago
" ሕዝቡን ያስቆጣ ተግባር የፈፀሙት ከንቲባ ከስልጣን ወርደዋል" - የሺንሽቾ ከተማ ነዋሪዎች
በባሳለፍነው ሳምንት በከንባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ለሰርግ መልስ በሚል የፌዴራል መንገድ በሁለቱም በኩል በድንኴን ተዘግቶ ነበር።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ሰርግ ደጋሹ ግለሰብ በአከባቢው ባለሃብትና የባለስልጣናት ዘመድ በመሆኑ ከሌሎች ነዋሪዎች የተለየ ሰርግ ለመደገስ በማሰብ ሁለት ግዙፍ ድንኳኖችን በግራና በቀኝ በመተከል ሺሽቾን ከወላይታ ሶዶ ፣ ከዱራሜ ፣ ወራቤና ሆሳዕና ቡታጅራ የሚያገናኘው የፌዴራል መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ መዝጋቱን ገልጸዋል።
በዚህ ምክንያት አንድ ተሽከርካሪ በውስጥ ለውስጥ ልዋጭ መንገድ ሲሄድ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተነካክቶ መቃጠሉን አክለዋል።
ለአንድ ባለሃብት ልጅ ተብሎ መንገዱ እንዲዘጋ የሆነው በከተማዉ ከንቲባ በነበሩት አቶ ታርኩ ተስፋዬ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ሰጪነት ነው ያሉት ነዋሪዎች ይኸው ህዝብን ያስቆጣ ተግባር የፈጸሙት ከንቲባ ከስልጣን መነሳታቸውን ተናግረዋል።
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር አማካሪ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ከከንቲባቅን ከስልጣን እንዳነሳ ነው ያስረዱት።
የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዙር 12 ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የከተማዋ ከንቲባ የነበሩትን አቶ ታሪኩ ተስፋየን ከስልጣን በማንሳት አቶ መለሰ ገብሬን በቦታቸው መሾሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
" በከንቲባውና አስተዳደራቸው ሕዝቡ ደስተኛ አልነበረም " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " በምክር ቤቱ ዉሳኔ ደስተኛ ነን " ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ ሌላች የስልጣን ማሰናበትና ሽግሽግ አድርጓል።
በዚህም መሠረት፦
➡️ አቶ መለሰ ገብሬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ
➡️ ወ/ሮ ባንቺ ማቴዎስ የሺንሽቾ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ
➡️ ኢ/ር ቢኒያም ጴጥሮስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ
➡️ አቶ አድማሱ ወልዴ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግምባታ ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ
➡️ ወ/ሮ አጥናፏ ታዴዎስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ
➡️ አቶ ሽመልስ ተስፋዬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
tikvahethiopia

#ethiopia | በባሳለፍነው ሳምንት በከንባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ለሰርግ መልስ በሚል የፌዴራል መንገድ በሁለቱም በኩል በድንኴን ተዘግቶ ነበር።

➡️ አቶ ሽመልስ ተስፋዬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን ገልጿል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

ኮንትራት ይዘው በመሄድ አሽከርካሪውን ገድለውን ንብረት ዘርፈው የተሰወሩት ግለሰቦች ከዓመታት በኋላ በእስራት ተቀጡ
በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጨለለቃ ክፍለ ከተማ አናታ የረር ወረዳ ዳንኤል መለሰ የተባለ የባጃጅ አሽከርካሪ በድንገት መሰወሩን ከቤተሰብ ጥቆማ ደርሷል።ፖሊስ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መነሻ አካባቢ ባደረገው ማጣራት ኮንትራት ተብሎ ሁለት ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ኤረር ዋልያ ፋብሪካ ወደተባለ አካባቢ መጓዙን ከባጃጅ ተራ አስከባሪዎች መረጃ ይደርሰዋል።
በዚህም ከተወሰኑ ወራት በኋላ በአንድ ማሳ ውስጥ ለእርሻ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አንድ ተገድሎ የተቀበረ አስክሬን አጥንት ያገኙና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ ኮማንደር ግርማ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ፖሊስ ወዲያው በአካባቢው ተገኝቶ የተቀበረውን የሰው አስክሬን በማንሳት አጥንቱን በመለቃቀም በቀጥታ ለጳውሎስ ሆስፒታል ይልካል። የጳውሎስ ሆስፒታል የተላከውን ቅሪት አካል መርምሮ የሰው ቅሪት አካል መሆኑን ያረጋግጣል ።
ከወራት በፊት የጠፋው የባጃጅ አሽከርካሪ ቅሪት አካል ይሆናል ተብሎ በመጠርጠሩ ከቤተሰብ መካከል የሁለት ሰው ደም በፌደራል ፖሊስ የፎረሲክ ምርመራ እንዲጣራ ተደርጎ 99.8 የተገኘው የቅሪት አካል የተሰወረው የባጃጅ አሽከርካሪ የዳንኤል መለሰ መሆኑ ይረጋገጣል ።ፖሊስም ኮንትራት ብለው የባጃጅ አሽከርካሪውን ይዘው የሄዱትን ሁለት ወጣቶች ላይ ክትትል ሲደረግ 2016 ዓ.ም ላይ ኩማ አሰፋ እና ደረጀ ግርማ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በአንድ መጠጥ ቤት ቁጭ ብለው ከዓመታት በፊት የፈፀሙትን የግድያ ወንጀል በማንሳት እንዳልተደረሰባቸው እና ለሌላ የዘረፋ ወንጀል ቁጭ ብለው ሲወያዩ ለፖሊስ ጥቆማ ይደርሰዋል።
በዚህም ፖሊስ ሁለቱንም በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል። ተከሳሾቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1A-06505 ኦ.ሮ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪን የሚያሽከረክረውን ዳንኤል መሰለን ሰዋራ ጫካ ስፍራ ሲደርሱ በማስቆም የተለያዩ ንብረቶችን ዘርፈዋል። በተጨማሪም ባለ ሶስት እግር ባጃጁን ደግሞ ሚሊዮን ግርማ በተባለ ሶስተኛ ግለሰብ አሽከርካሪነት መቂ ከተማ በመውሰድ ታርጋ፣ ሊብሬ እና የሻሲ ቁጥር በሀሰት በማዘጋጀት ደቡብ ክልል ዱራሜ ከተማ ወስደው በመሸጥ የተመለሱ እንደሆነ ለፖሊስ በሰጡት የእምነት ቃል ተረጋግጧል።
ፖሊስ ባለ ሶስት እግር አሽከርካሪውን ሚሊዮን ግርማን በቁጥጥር ስር በማዋል ተሽከርካሪውን ደቡብ ክልል ዱራሜ ከተማ ገጠራማ መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ስትሰጥ በቁጥጥር ስር አውሎ በማስረጃነት ወደ ቢሾፍቱ ማምጣቱን ኮማንደር ግርማ ማሞ ገልጸዋል።ፖሊስም በሶስቱ ግለሰቦች ሰፊ ክትትል እና ምርመራ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ምርመራ እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ይልካል፡፡አቃቤ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 539 በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል።
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 26 ቀን 2018 በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኩማ አሰፋና ደረጀ ግርማ እያንዳዳቸው በ23 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ሲወስን ሶስተኛው ተከሳሽ በወንጀል ድርጊት የተገኘውን ባጃጅ በማሻሻጡ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።ባለ ሶስት እግር ባጃጁ ለተጎጂው ቤተሰብ እንድትመለስ መወሰኑን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አቃቢ ህግ ፅ/ቤት የተለያዪ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ሃላፊ አቃቢ ህግ ሰኚ ነሞምሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

9 months ago
ለቀረበባቸው የአስተዳደራዊ በደል ክስ ምላሽ ባልሰጡ ከ50 በላይ የመንግሥት ተቋማት እና ኃላፊዎች ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ
👉 ከሚቀርቡ አቤቱታዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር ያየዘው በመንግሥት መስሪያ ቤት ላይ የሚቀርብ አቤቱታ ነው ተብሏል
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም 'አስተዳደራዊ በደል አድርሰውብናል' በሚል በሠራተኞቻቸው ለቀረበባቸው ክስ ተገቢውን ምላሽ ባልሰጡ ከ50 በላይ የሥራ ኃላፊዎች እና ተቋማት ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
በተቋሙ የይግባኝ ሰሚና የውሳኔ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደነቀ ሻንቆ፤ ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ክስ ከተመሰረተባቸው ከ50 በላይ ተቋማት መካከል በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠባቸው መዝገቦች ስለመኖራቸው ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል።
መሪ ሥራ አስፈጻሚው እንዳብራሩት፤ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋሙ በ2017 ዓ.ም. ክስ ከመሰረተባቸው 40 የመንግሥት ተቋማት እና ኃላፊዎች መካከል 22 መዝገቦች እልባት ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ 18 መዝገቦች ወደ 2018 በጀት ዓመት ተዘዋውረዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ደግሞ፤ 13 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ በ4 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ተላልፎ መዝገቡ ተዘግቷል።
በአጠቃላይ እልባት በተሰጣቸው መዝገቦች ላይ የተጣለውን ቅጣት በተመለከተ፤ ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር በደል ያደረሱ ኃላፊዎች ከሥራ እንዲታገዱ፣ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ፣ ተቋሙ ለተበዳዮች ካሳ እንዲከፍል እና ሌሎችም መሰል አስተማሪ ቅጣት ማስተላለፉን አብራርተዋል።
ክስ ከተመሰረተባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል፤ በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን የቡሪሳ ማዘጋጃ ቢሮ፣ ምዕራብ ጉራጌ ዞን፣ በካምባታ ዞን የዱራሜ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፣ በቤንሻንጉል ክልል ቡለን ወረዳ፣ በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል የሚገኙ 6 የመንግሥት ተቋማት ይገኙበታል ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ ካሉት መካከል ደግሞ የየካ፣ ጉለሌ፣ ቃሊቲ እና ልደታ ክፍለ ከተሞች ይጠቀሳሉ።
አቶ ደነቀ ዜጎች ለአስተዳደራዊ በደል ያቀረቧቸው አቤቱታዎች በተለይ ከይዞታ ጋር በተያያዘ፣ ከሠራተኞች ጥቅማ ጥቅም እና ደመወዝ አለመክፈል ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከአስተዳደራዊ በደል ጋር ተያይዞ የቀረቡ አቤቱታዎች ከግል መስሪያ ቤቶች ይልቅ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ የቀረቡት ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
አስተዳደራዊ በደል እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በሦስት ወር ውስጥ ለተቋሙ የቀረበለት አቤቱታዎች ከ430 በላይ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በዚህም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ከ350 በላይ አቤቱታዎች የቀረቡ መሆኑን እና በግል መስሪያ ቤት ደግሞ ከ70 በላይ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡
በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ የቀረበው አቤቱታ ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም፤ በግል ተቋማት ላይ የሚደርሱ አስተዳደራ በደሎች ወደ ተቋሙ ስለማይመጡ እንጂ ከፍተኛ እንደደሚሆኑ ይገመታል ብለዋል፡፡
በአጠቃለይ ከቀረቡት አቤቱታች ከ230 በላይ የሚሆኑት ተገቢውን ምርመራ ተደርጎባቸው እልባት ተሰቷቸዋል ሲሉም መሪ ሥራ አስፈጻሚው ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በግል መስሪያ ቤት ላይ የሚደረሱ አስተዳደራዊ በደሎችን በተመለከተ ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ ቅሬታዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ተገለጸ ሲሆን፤ አሁንም በማሕበረሰቡ ላይ ያለው የግንዛቤ እጥረት በሚፈለገው ልክ አቤቱታዎች እየቀረቡ አለመሆኑን ተነግሯል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት እንደ ተቋም የግንዛቤ ማጨበጫ ሥራዎችን በስፋት እየሰሩ እንደሚገኝ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም ዜጋ ትብብር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡
#አሐዱ

Sponsored by
Surafel
10 months ago
ከታረዱ በሬዎች ወርቅ ተገኘ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ዞን ሺንሺቾ እና ዱራሜ ከተማዎች በትናትናው ዕለት ለመሳላ በዓል ከታረዱት ሰንጋ በሬዎች ሆድ ዕቃ ውስጥ ወርቅ ተገኘ፡፡
የከንባታ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንደገለፁት፤ ለበዓል ከታረዱ 2 በሬዎች ውስጥ የተገኘው ማዕድን ወርቅ መሆኑ ተረጋግጧል።
በከንባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ በአካባቢው ባህል ሼማታ ተብለው የሚጠሩ ማህበሮች 8 ሆነው በመደራጀት ሰንጋ በሬ ገዝተው እንደነበር አስታውሰዋል።
የእርድ ሥነ ሥርዓት በሚያከናውኑበት ወቅት ከበሬው ሆድዕቃ ውስጥ ለጊዜው ግራሙ በውል ያልታወቀ ወርቅ መገኘቱን አስረድተዋል።
የተገኘውን ወርቅ ከ80 ሺህ ብር የገመቱት ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመው፤ ባለቤቶቹ ግን ከዚህ በላይ ያወጣል ማለታቸውን አንስተዋል።
በተመሳሳይ በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ለመሳላ በዓል ከተገዛው ሰንጋ በሬ 12.5 ግራም የሚያወጣ ወርቅ መገኘቱን አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ተናግረዋል፡፡
seledadotio

ለበዓል ከታረዱት በሬዎች ወርቅ ተገኘ
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ዞን ሺንሺቾ እና ዱራሜ ከተማዎች በትናትናው ዕለት ለመሳላ በዓል ከታረዱት ሰንጋ በሬዎች ሆድ ዕቃ ውስጥ ወርቅ ተገኘ፡፡
የከንባታ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንደገለጹት፤ ለበዓል ከታረዱ 2 በሬዎች ውስጥ የተገኘው ማዕድን ወርቅ መሆኑ ተረጋግጧል።
በከንባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ ሼማታ በሚል ስያሜ የተደራጀው ማኅበር ለቅርጫ የገዛው ሰንጋ በሬ ሲታረድ ሆድ ዕቃው ውስጥ ለጊዜው ግራሙ በውል ያልታወቀ ወርቅ መገኘቱን አስረድተዋል።
የተገኘውን ወርቅ ከ80 ሺህ ብር በላይ የገመቱ ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመው፤ ባለቤቶቹ ግን ከዚህ በላይ ያወጣል ማለታቸውን አንሥተዋል።
በተመሳሳይ በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ለመሳላ በዓል ከታረደው ሰንጋ በሬ 12.5 ግራም የሚያወጣ ወርቅ መገኘቱን አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ተናግረዋል፡፡#ebc

11 months ago
የአተካና ምሽት በዱራሜ
#ethiopia | በከምባታ የዘመን መለወጫ ‘‘መሳላ’’ በዓል ዋዜማ የሚከበረው የአተካና ስነ-ስርዓት በማህበረሰቡ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የመሳላ በዓል ሌላኛው ድምቀት ነው፡፡
በአካባቢው ባህል መሰረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው የእናቶች መሳላ በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ስነ-ስርዓት በዱራሜ ከተማ በኡቱቢያ ወጋ አደባባይ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
ይህ የአተካና ስነስርዓት የከምባታ እናቶች ለወራት ተጨንቀውና ተጠበው የሚያዘጋጁት የመሳላ በዓል አከባበር አንዱ አካል ነው።
የአዲስ ዓመት መግባትን ማብሰሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ስነ-ስርዓት፤ በቤተሰብ አባላትና ዘመድ ጎረቤት በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
ከአተካና እራት ስነ-ስርዓት ቁጥሎ በጉጉት የሚጠበቀው የመሳላ ወይም የከምባታ ዘመን መለወጫ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል።
በሲሳይ ደበበ
#ebc #ethiopia #kembata #መሳላ

ሚስ ከምባታ 2018
ወ/ሪት ሜሮን ታዲዎስ ሆና ተመርጣለች
#ethiopia | የ2018 የሚስ ከምባታ አጓጓጊ ውድድር በስተመጨራሻ ሚስ 2018 ወ/ሪት ሜሮን ታዲዎስ ሆና አሸናፊ ሆናለች።
ተመራጯ ሚስ በቀጣይ የከምባታ ዞን አምባሳደር በመሆን የከምባታን ባህል ፣ የቱሪዝም ስፍራ ፣ እሴት እና ገፅታ ለኢትዮጵያና ለተቀሪው ዓለም የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቃታል።
የዞኑ ባህል ታሪክና የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ቪዚት ከምባታ አስጎብኚ ድርጅት አስታወቀ ።
ድርጅቱ ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ/ም 3ኛውን የመሳላ አዋርድ ውድድር በዱራሜ ከተማ አካሂዷል ።
ወይዘሪት ሜሮን ታደሰ የ3ኛው የሚስ መሳላ አዋርድ አሸናፊ ሆናለች ።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሀይሉ ሀደሮ እንደተናገሩት ቪዚት ከምባታ ድርጅት የዞኑን የሪዝሙን አቅም ለማሳደግ ለማሳደግና የዞኑን ፀጋዎች በማስተዋወቅ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ነው ብለዋል ።
የዞኑን የቱሪዝም አቅም ለማስተዋወቅ የኘስጎብኚ ቁጥር እንዲጨምር ይበረታታል ያሉት አቶ ሀይሉ ድርጅቱ የመሳላ አዋርድ የመሳላ ታላቁ ሩጫና ሌሎች ሁነቶችን በማዘጋጀት የሚሠራቸው ሥራር ለዞኑ ተጨማሪ የቱሪስት አቅም የሚሆኑ ናቸው ሲሉም አክለዋል ።
በመርሃግብሩ ላይ የቪዚት የከምባታ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ቶማስ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የዞኑን ህዝብ ባህል ታሪክ ቅርስና የተፈጥሮ መስህቦችን በማስተዋወቅ ረገድ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል ።
ድርጅቱ እየሠራ ባለው ሥራ አካባቢያቸውን የሚወዱ ስለአካባቢያቸው ለማወቅ የሚጓጉና ታታሪ ወጣቶች እየተፈጠሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሳምሶን ይህ ድርጅት እዚህ እንዲደርስ የድርሻቸውን እየተወጡ ያሉ አጋሮችን አመስግነዋል ።
ለከምባታ ብሔር ባህል ዕድገት ታሪካዊ የድርሻቸውን የተወጡና አሻራቸውን ያኖሩ የብሔሩ አባላት በያሉበት ማስታወስና ዕውቅና መስጠት ከድርጅቱ ዓላማዎች አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ሥራአስኪያጁ ድርጅቱ ከዚህ በበለጠ በሥራው እንዲያድግ ሁሉም አካላት ከድርጅቱ ጎን ከመሆኑም ጠይቀዋል ።
ሶስተኛው የመሳላ አዋርድ ለመምረጥ በተደረገው ውድድር ወይዘሪት ሜሮን ታደሰ ማሸነፏን የገለፁት አቶ ሳምሶን የውድድሩ አሸናፊ ሚስ ሜሮንም ለሚቀጥለው አንድ ዓመት በአገር ውስጥና ለመላው ዓለም የከምባታን ባህል ታሪክና የተፈጥሮ ፀጋዎችን የማስተዋወቅ ሀላፊነት ተቀብላለች ብለዋል ።
የ2018 ዓ/ም 3ኛው የመሳላ አዋርድ አሽናፊዋ ሚስ ሜሮን ታደሰ በሰጠችው አስተያየት ድርጅቱ ለሰጣት ዕድል በማመስገን ባገኘችው ዕድል የብሔሩን ታሪክ ባህልና የተፈጥሮ መስህቦችን በማስተዋወቅ ሀላፊነቷን እንደሚትወጣ ተናግራለች።
በ3ኛው የመሳላ አዋርድ በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎች የተሸለሙ ሲሆን በዚህም መሠረት :-
የ2018 የ777 ዳግም ደረጃ መንገድ ህብረተሠቡን በማስተባበርና በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ በዞኑ ህዝብ ላይ ለፈጠሩት ህዝባዊ አንድነት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ
የ2018 ምርጥ መስህብ አጆራ መንትያ ፏፏቴ
የ2018 አርኤል በጎ አድራጎት ማህበር
የ2018 ተጽዕኖ ፈጣሪ ማህበራዊ ሚዲያ ሄኖክ ታደሰ
የ2018 የህይወት ዘመን አገልግሎት ዶክተር ፍቅሩ ገለሶ
የ2018 አለምአቀፍ አስጎብኚ ሴና ቱር
የ2018 በጤና ዘርፍ ዶክተር ዳኛቸው ዮሐንስ
የ2018 ለከምባታ ልማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዶክተር ግዛቸው ከበደ
የ2018 ማህበራዊ ሚዳዲያን ለበጎ ዓላማ ይድነቃቸው ያሬድ እና ቢኒያም ዓለሙ
የ2018 ምርጥ ዶክመንተሪ ረታ ዓለሙ
የ2018 የከምባታ የባህል ሙዚቃ ዘርፍ አሸናፊ አርቲስት ዙሪያሽወርቅ አበራ
የ2018 በወንዶች የሙዚቃ ዘርፍ ድምጻዊ ከተማ ገብረመድህን
የ2018 ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ትሁት አየለ
የ2018 በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ልዩ ተሸላሚ ለመጣው ለውጥ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ደረበ ዮሐንስ
የ2018 ልዩ ተሸላሚ ታላቅ መሪ ዘርፍ መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ
የ2018 ልየ ተሸላሚ በደቡብ አፍሪካ የከምባታ ልማት ማህበር
የ2018 ሞዴል አርሶ አደር በአካባቢው ላመጣው የሥራ ባህል ለውጥ ልዩ ተሸላሚ ወጣት አብነት ዴላሞ
የ2018 በዞኑ ልማት ላይ ላበረከቱት አበርክቶ ልዩ ተሸላሚ የተከበሩ ወይዘሮ ማርታ ልውጂ
የ2018 የሥራ ፈጠራና የልማት ተሳትፎ አርበኝነት ልዩ ተሸላሚ አቶ አበበ አበሞ ሆነዋል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊና የዋና አስተዳዳሪውን ተወካይ አቶ ሀይሉ ሀደሮና የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችና ዓለም አገራት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ዶ/ር አብተው ለጂቦ ድልበቶ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
#ethiopia | ዶክተር አብተው ለጂቦ ድልበቶ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ሲመሰረት ከነበሩ ከመጀመሪያዎቹ አንጋፋ ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው። ዶ/ር አብተው በዩኒቨርሲቲው ከ1999 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆንም በቅንነት እና ታማኝነት አገልግለዋል።
በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ በግብርና ኮሌጅ ሆርቲካልቸር ት/ት ክፍል በመማር ማስተማር እና በችግር ፈቺ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር መስክ በተለይ በእንሰት ተክል ባካሄዱት ጥልቅ ምርምር እንደ ሀገር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ሲካሄድ በነበረ ጥረት ጉልህ አሻራ አሳርፈዋል። በሙያቸው የማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን በማማከር እና አቅጣጫ በማሳየትም ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል።
ዶ/ር አብተው በሙያቸው መስክ በዋና እንዲሁም ተባባሪ ተመራማሪነት ከ40 የሚበልጡ ሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ስራዎች በዓለም አቀፍ ጆርናል ላይ በማሳተም ለአካዳሚው ዓለም የጥናትና ምርምር እድገት የማይተካ ሚና ነበራቸው።
ዶክተር አብተው በሀገረ ስዊድን ኡፕሳላ ከተማ በሚገኘው ❝የስዊድን ግብርና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ❞ በመምህርነት እና ተመራማሪነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፤በሚኖሩበት ስውዲን ሀገር ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ዶ/ር አብተው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መስራች በመሆን በተቋም ደረጃ በምክትል ኘሬዝዳንትነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ታሪካዊ አሻራቸውን ከማሳረፋቸውም ባሻገር
በቀድሞ የደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በአመራርነት እንዳገለገሉ የግለ ታሪክ ማህደራቸው ያመላክታል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር በቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ባልደረባ እና አንጋፋ ምሁር በሆኑት ዶ/ር አብተው ለጅቦ ድልበቶ ህልፈት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን በመግለጽ ለመላ ቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለአካዳሚው ማህበረሰብ መጽናናትን ይመኛል!!
ነፍስ ይማር
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር!!
Condolence Message for Abitew Lagibo Dalbato (Dr.)
We are deeply saddened by the passing of Dr. Abitew Lagibo Dalbato, a brilliant researcher, dedicated educator, and compassionate soul whose work touched lives far beyond the academic sphere. His pioneering research on Ensete ventricosum and sustainable agriculture has left an enduring legacy that will continue to inspire future generations.
Dr. Dalbato was not only a scholar of great intellect but also a person of humility, kindness, and unwavering commitment to improving food security and environmental resilience. His contributions to science and society will be remembered with profound respect and admiration.
Our thoughts and prayers are with his family, friends, and colleagues during this difficult time. May his memory be a blessing, and may his work continue to flourish in the hands of those he inspired.
Rest in peace, Dr. Abitew. Your work lives on. 🌿
#rip #abitewdalbato #agriculturalscience #ensetresearch #wsu #sustainableagriculture #legacyoflearning #ethiopia #slu #plantpropagation
***
በመማሩ ማይታበየው ትሁቱና ቀናው ሰው !
በሽግግር መንግስቱ ሁሉም አከባቢውን እንዲያለማ ጥሪ ይተላለፋል።ዶ/ር አብተው ለጂቦ ደሞ በጊዜው ልእለ ሀያል ደረጃ ባለችው በሀገረ ጀርመን 2ኛ ዲግሪውን ያጠናቀቀበት ጊዜ ነበር። በትምህርት ዝግጅቱ በተማረበት ሀገርም ሆነ በሀገራችን አሉ በሚባሉ የሙያም ሆነ በስልጣን ደረጃ ማገልገል የሚያስችል አቅሙ ብቻ ሳይሆን እድሉም ነበረው። ቅድሚያ ለምቾቱ ሳይሆን ለህዝቡ በመስጠት ጥሪውን ተቀብሎ የዞኑን የግብርና ዘርፍ በዱራሜ ለመምራት በሰው ሀይልም ፣በግብአትም ሆነ በበጀት ያልተደራጀ ተቋም ለማደራጀት ምቹ እድሉን ሰውቶ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ቆራጥ ሰው ነበረ።
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ ክልሉን በአመራርነት ፤የወላይታ ዩኒቨርሲቲ መስራችና በምክትል ኘረዝደንትነት ታሪካዊ አሻራውን ያሳረፈ ፤ በሀገረ ሲውዲን ስመጥር ተመራማሪው ዶ/ር አብተው ዛሬ ከዚህ ዓለም መለየቱን ስሰማ ልቤ ተሰበረ።
ሩቅ አላሚው ለሀገሩም ለህዝቡም ብዙ ራእይ እንደነበረው ያጫወተኝ ነገር ትልቅ ሸክም ፈጥሮብኛል።የማይቀርበት ቢሄድም በማይሞተው ራእይውና ሌጋሲው ሁሌም ከትውልዱ ጋር ይኖራል።
ነፍስህን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን!
ለቅሶ ሥነ ስርዓቱ የሚከናወነዉ በትዉልድ ስፍራዉ አሽራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቤቄራ አከባቢ በቀን 21-12-2017 ከ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

1 year ago
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አኩፋዳሽ አይጓደል መንፈሳዊ ማህበር ለጾመ ፍልሰታ የማርያም ቅዳሴ አገልግሎት ይሆን ዘንድ ያሰባሰበውን የጧፍ ፣ የዕጣን እና የዘቢብ ድጋፍ ለከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት አስረከበ።
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛
ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ/ም
"""""""" ዱራሜ/ኢትዮጵያ """""""""
በብፁዕ አባታችን አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጪነትና አሳሳቢነት አኩፋዳሽ አይጓደል መንፈሳዊ ማህበር በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት ስር ለሚገኙ የገጠር አብያተ ቤተክርስቲያናት ይሆን ዘንድ ያሰባሰበውን የጧፍ ፣ ዕጣን እና ዘቢብ ድጋፍ ለሀገረ ስብከታችን ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ በጽህፈት ቤታቸው አስረክቧል።
ይህም ማህበር ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገረ ስብከቶች እየተዘዋወረ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመውን መልካም ነገር የሚያደርግ ማህበር ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ከነሐሴ 1 ጀምሮ የሚጾመውን ጾመ ፍልሰታ የማርያም ቅዳሴ እንዳይታጎል በማሰብ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን በማሰባሰብ ለሀገረ ስብከታችን አበርክቷል።
የሀገረ ስብከታችን ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ ማህበሩ ለሀገረ ስብከታችን ስላደረገው ድጋፍ አመስግነው ሁሌም ለገጠር አብያተክርስቲያናት እያደረጉ ያለው መልካምነት በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ በረከት የሚያስገኝላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የአኩፋዳሽ አይጓደል መንፈሳዊ ማህበር ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ብሩክ ክፍሌ በበኩላቸው በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድና አባታዊ መመሪያ ሰጪነት ማህበራቸው በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ለመስራት በመብቃቱ መደሰታቸውን ገልጸው የገጠሩ አብያተክርስቲያናት ጾመ ፍልሰታን ሳይዘጉ በአገልግሎት ያሳልፉ ዘንድ በማሰብ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህም በኋላ በብፁዕነታቸው መልካም ፈቃድ ማህበሩ ከሀገረ ስብከቱ ጋር ሰፋፊ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ሊቀ ትጉሃን ብሩክ ክፍሌ ተናግረዋል።
በርክክብ መርሐግብሩ የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ ፣ የአኩፋዳሽ አይጓደል መንፈሳዊ ማህበር ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ብሩክ ክፍሌ እና የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የየክፍላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።ተ

Comments