9 months ago
ዶ/ር አብተው ለጂቦ ድልበቶ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
#ethiopia | ዶክተር አብተው ለጂቦ ድልበቶ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ሲመሰረት ከነበሩ ከመጀመሪያዎቹ አንጋፋ ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው። ዶ/ር አብተው በዩኒቨርሲቲው ከ1999 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆንም በቅንነት እና ታማኝነት አገልግለዋል።
በተቋሙ በነበራቸው ቆይታ በግብርና ኮሌጅ ሆርቲካልቸር ት/ት ክፍል በመማር ማስተማር እና በችግር ፈቺ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር መስክ በተለይ በእንሰት ተክል ባካሄዱት ጥልቅ ምርምር እንደ ሀገር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ሲካሄድ በነበረ ጥረት ጉልህ አሻራ አሳርፈዋል። በሙያቸው የማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን በማማከር እና አቅጣጫ በማሳየትም ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል።
ዶ/ር አብተው በሙያቸው መስክ በዋና እንዲሁም ተባባሪ ተመራማሪነት ከ40 የሚበልጡ ሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ስራዎች በዓለም አቀፍ ጆርናል ላይ በማሳተም ለአካዳሚው ዓለም የጥናትና ምርምር እድገት የማይተካ ሚና ነበራቸው።
ዶክተር አብተው በሀገረ ስዊድን ኡፕሳላ ከተማ በሚገኘው ❝የስዊድን ግብርና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ❞ በመምህርነት እና ተመራማሪነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፤በሚኖሩበት ስውዲን ሀገር ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ዶ/ር አብተው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መስራች በመሆን በተቋም ደረጃ በምክትል ኘሬዝዳንትነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ታሪካዊ አሻራቸውን ከማሳረፋቸውም ባሻገር
በቀድሞ የደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት በአመራርነት እንዳገለገሉ የግለ ታሪክ ማህደራቸው ያመላክታል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር በቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ባልደረባ እና አንጋፋ ምሁር በሆኑት ዶ/ር አብተው ለጅቦ ድልበቶ ህልፈት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን በመግለጽ ለመላ ቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለአካዳሚው ማህበረሰብ መጽናናትን ይመኛል!!
ነፍስ ይማር
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር!!
Condolence Message for Abitew Lagibo Dalbato (Dr.)
We are deeply saddened by the passing of Dr. Abitew Lagibo Dalbato, a brilliant researcher, dedicated educator, and compassionate soul whose work touched lives far beyond the academic sphere. His pioneering research on Ensete ventricosum and sustainable agriculture has left an enduring legacy that will continue to inspire future generations.
Dr. Dalbato was not only a scholar of great intellect but also a person of humility, kindness, and unwavering commitment to improving food security and environmental resilience. His contributions to science and society will be remembered with profound respect and admiration.
Our thoughts and prayers are with his family, friends, and colleagues during this difficult time. May his memory be a blessing, and may his work continue to flourish in the hands of those he inspired.
Rest in peace, Dr. Abitew. Your work lives on. 🌿
#rip #abitewdalbato #agriculturalscience #ensetresearch #wsu #sustainableagriculture #legacyoflearning #ethiopia #slu #plantpropagation
***
በመማሩ ማይታበየው ትሁቱና ቀናው ሰው !
በሽግግር መንግስቱ ሁሉም አከባቢውን እንዲያለማ ጥሪ ይተላለፋል።ዶ/ር አብተው ለጂቦ ደሞ በጊዜው ልእለ ሀያል ደረጃ ባለችው በሀገረ ጀርመን 2ኛ ዲግሪውን ያጠናቀቀበት ጊዜ ነበር። በትምህርት ዝግጅቱ በተማረበት ሀገርም ሆነ በሀገራችን አሉ በሚባሉ የሙያም ሆነ በስልጣን ደረጃ ማገልገል የሚያስችል አቅሙ ብቻ ሳይሆን እድሉም ነበረው። ቅድሚያ ለምቾቱ ሳይሆን ለህዝቡ በመስጠት ጥሪውን ተቀብሎ የዞኑን የግብርና ዘርፍ በዱራሜ ለመምራት በሰው ሀይልም ፣በግብአትም ሆነ በበጀት ያልተደራጀ ተቋም ለማደራጀት ምቹ እድሉን ሰውቶ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ቆራጥ ሰው ነበረ።
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ ክልሉን በአመራርነት ፤የወላይታ ዩኒቨርሲቲ መስራችና በምክትል ኘረዝደንትነት ታሪካዊ አሻራውን ያሳረፈ ፤ በሀገረ ሲውዲን ስመጥር ተመራማሪው ዶ/ር አብተው ዛሬ ከዚህ ዓለም መለየቱን ስሰማ ልቤ ተሰበረ።
ሩቅ አላሚው ለሀገሩም ለህዝቡም ብዙ ራእይ እንደነበረው ያጫወተኝ ነገር ትልቅ ሸክም ፈጥሮብኛል።የማይቀርበት ቢሄድም በማይሞተው ራእይውና ሌጋሲው ሁሌም ከትውልዱ ጋር ይኖራል።
ነፍስህን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን!
ለቅሶ ሥነ ስርዓቱ የሚከናወነዉ በትዉልድ ስፍራዉ አሽራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቤቄራ አከባቢ በቀን 21-12-2017 ከ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።