Logo
Getu Temesgen
ለበዓል ከታረዱት በሬዎች ወርቅ ተገኘ
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ዞን ሺንሺቾ እና ዱራሜ ከተማዎች በትናትናው ዕለት ለመሳላ በዓል ከታረዱት ሰንጋ በሬዎች ሆድ ዕቃ ውስጥ ወርቅ ተገኘ፡፡

የከንባታ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንደገለጹት፤ ለበዓል ከታረዱ 2 በሬዎች ውስጥ የተገኘው ማዕድን ወርቅ መሆኑ ተረጋግጧል።

በከንባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ ሼማታ በሚል ስያሜ የተደራጀው ማኅበር ለቅርጫ የገዛው ሰንጋ በሬ ሲታረድ ሆድ ዕቃው ውስጥ ለጊዜው ግራሙ በውል ያልታወቀ ወርቅ መገኘቱን አስረድተዋል።

የተገኘውን ወርቅ ከ80 ሺህ ብር በላይ የገመቱ ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመው፤ ባለቤቶቹ ግን ከዚህ በላይ ያወጣል ማለታቸውን አንሥተዋል።

በተመሳሳይ በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ለመሳላ በዓል ከታረደው ሰንጋ በሬ 12.5 ግራም የሚያወጣ ወርቅ መገኘቱን አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ተናግረዋል፡፡#ebc

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.