Logo
Getu Temesgen
‎" ሕዝቡን ያስቆጣ ተግባር የፈፀሙት ከንቲባ ከስልጣን ወርደዋል" - የሺንሽቾ ከተማ ነዋሪዎች
#ethiopia | ‎በባሳለፍነው ሳምንት በከንባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ለሰርግ መልስ በሚል የፌዴራል መንገድ በሁለቱም በኩል በድንኴን ተዘግቶ ነበር።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ሰርግ ደጋሹ ግለሰብ በአከባቢው ባለሃብትና የባለስልጣናት ዘመድ በመሆኑ ከሌሎች ነዋሪዎች የተለየ ሰርግ ለመደገስ በማሰብ ሁለት ግዙፍ ድንኳኖችን በግራና በቀኝ በመተከል ሺሽቾን ከወላይታ ሶዶ ፣ ከዱራሜ ፣ ወራቤና ሆሳዕና ቡታጅራ የሚያገናኘው የፌዴራል መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ መዝጋቱን ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት አንድ ተሽከርካሪ በውስጥ ለውስጥ ልዋጭ መንገድ ሲሄድ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተነካክቶ መቃጠሉን አክለዋል።

ለአንድ ባለሃብት ልጅ ተብሎ መንገዱ እንዲዘጋ የሆነው በከተማዉ ከንቲባ በነበሩት አቶ ታርኩ ተስፋዬ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ሰጪነት ነው ያሉት ነዋሪዎች ይኸው ህዝብን ያስቆጣ ተግባር የፈጸሙት ከንቲባ ከስልጣን መነሳታቸውን ተናግረዋል።

‎የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር አማካሪ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ከከንቲባቅን ከስልጣን እንዳነሳ ነው ያስረዱት።

‎የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የሽግግር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዙር 12 ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የከተማዋ ከንቲባ የነበሩትን አቶ ታሪኩ ተስፋየን ከስልጣን በማንሳት አቶ መለሰ ገብሬን በቦታቸው መሾሙንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

" ‎በከንቲባውና አስተዳደራቸው ሕዝቡ ደስተኛ አልነበረም " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " በምክር ቤቱ ዉሳኔ ደስተኛ ነን " ሲሉ ተናግረዋል።

‎ከዚህ ባለፈ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ ሌላች የስልጣን ማሰናበትና ሽግሽግ አድርጓል።

‎በዚህም መሠረት፦

‎➡️ አቶ መለሰ ገብሬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ

‎➡️ ወ/ሮ ባንቺ ማቴዎስ የሺንሽቾ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ

‎➡️ ኢ/ር ቢኒያም ጴጥሮስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ

‎➡️ አቶ አድማሱ ወልዴ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግምባታ ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ

‎➡️ ወ/ሮ አጥናፏ ታዴዎስ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ

‎➡️ አቶ ሽመልስ ተስፋዬ የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን ገልጿል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.