ከታረዱ በሬዎች ወርቅ ተገኘ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ዞን ሺንሺቾ እና ዱራሜ ከተማዎች በትናትናው ዕለት ለመሳላ በዓል ከታረዱት ሰንጋ በሬዎች ሆድ ዕቃ ውስጥ ወርቅ ተገኘ፡፡
የከንባታ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንደገለፁት፤ ለበዓል ከታረዱ 2 በሬዎች ውስጥ የተገኘው ማዕድን ወርቅ መሆኑ ተረጋግጧል።
በከንባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ በአካባቢው ባህል ሼማታ ተብለው የሚጠሩ ማህበሮች 8 ሆነው በመደራጀት ሰንጋ በሬ ገዝተው እንደነበር አስታውሰዋል።
የእርድ ሥነ ሥርዓት በሚያከናውኑበት ወቅት ከበሬው ሆድዕቃ ውስጥ ለጊዜው ግራሙ በውል ያልታወቀ ወርቅ መገኘቱን አስረድተዋል።
የተገኘውን ወርቅ ከ80 ሺህ ብር የገመቱት ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመው፤ ባለቤቶቹ ግን ከዚህ በላይ ያወጣል ማለታቸውን አንስተዋል።
በተመሳሳይ በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ለመሳላ በዓል ከተገዛው ሰንጋ በሬ 12.5 ግራም የሚያወጣ ወርቅ መገኘቱን አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ተናግረዋል፡፡
seledadotio

10 months ago