Logo
Getu Temesgen
ሚስ ከምባታ 2018
ወ/ሪት ሜሮን ታዲዎስ ሆና ተመርጣለች
#ethiopia | የ2018 የሚስ ከምባታ አጓጓጊ ውድድር በስተመጨራሻ ሚስ 2018 ወ/ሪት ሜሮን ታዲዎስ ሆና አሸናፊ ሆናለች።

ተመራጯ ሚስ በቀጣይ የከምባታ ዞን አምባሳደር በመሆን የከምባታን ባህል ፣ የቱሪዝም ስፍራ ፣ እሴት እና ገፅታ ለኢትዮጵያና ለተቀሪው ዓለም የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቃታል።

የዞኑ ባህል ታሪክና የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ቪዚት ከምባታ አስጎብኚ ድርጅት አስታወቀ ።

ድርጅቱ ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ/ም 3ኛውን የመሳላ አዋርድ ውድድር በዱራሜ ከተማ አካሂዷል ።

ወይዘሪት ሜሮን ታደሰ የ3ኛው የሚስ መሳላ አዋርድ አሸናፊ ሆናለች ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሀይሉ ሀደሮ እንደተናገሩት ቪዚት ከምባታ ድርጅት የዞኑን የሪዝሙን አቅም ለማሳደግ ለማሳደግና የዞኑን ፀጋዎች በማስተዋወቅ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ነው ብለዋል ።

የዞኑን የቱሪዝም አቅም ለማስተዋወቅ የኘስጎብኚ ቁጥር እንዲጨምር ይበረታታል ያሉት አቶ ሀይሉ ድርጅቱ የመሳላ አዋርድ የመሳላ ታላቁ ሩጫና ሌሎች ሁነቶችን በማዘጋጀት የሚሠራቸው ሥራር ለዞኑ ተጨማሪ የቱሪስት አቅም የሚሆኑ ናቸው ሲሉም አክለዋል ።

በመርሃግብሩ ላይ የቪዚት የከምባታ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ቶማስ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የዞኑን ህዝብ ባህል ታሪክ ቅርስና የተፈጥሮ መስህቦችን በማስተዋወቅ ረገድ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል ።

ድርጅቱ እየሠራ ባለው ሥራ አካባቢያቸውን የሚወዱ ስለአካባቢያቸው ለማወቅ የሚጓጉና ታታሪ ወጣቶች እየተፈጠሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሳምሶን ይህ ድርጅት እዚህ እንዲደርስ የድርሻቸውን እየተወጡ ያሉ አጋሮችን አመስግነዋል ።

ለከምባታ ብሔር ባህል ዕድገት ታሪካዊ የድርሻቸውን የተወጡና አሻራቸውን ያኖሩ የብሔሩ አባላት በያሉበት ማስታወስና ዕውቅና መስጠት ከድርጅቱ ዓላማዎች አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ሥራአስኪያጁ ድርጅቱ ከዚህ በበለጠ በሥራው እንዲያድግ ሁሉም አካላት ከድርጅቱ ጎን ከመሆኑም ጠይቀዋል ።

ሶስተኛው የመሳላ አዋርድ ለመምረጥ በተደረገው ውድድር ወይዘሪት ሜሮን ታደሰ ማሸነፏን የገለፁት አቶ ሳምሶን የውድድሩ አሸናፊ ሚስ ሜሮንም ለሚቀጥለው አንድ ዓመት በአገር ውስጥና ለመላው ዓለም የከምባታን ባህል ታሪክና የተፈጥሮ ፀጋዎችን የማስተዋወቅ ሀላፊነት ተቀብላለች ብለዋል ።

የ2018 ዓ/ም 3ኛው የመሳላ አዋርድ አሽናፊዋ ሚስ ሜሮን ታደሰ በሰጠችው አስተያየት ድርጅቱ ለሰጣት ዕድል በማመስገን ባገኘችው ዕድል የብሔሩን ታሪክ ባህልና የተፈጥሮ መስህቦችን በማስተዋወቅ ሀላፊነቷን እንደሚትወጣ ተናግራለች።

በ3ኛው የመሳላ አዋርድ በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎች የተሸለሙ ሲሆን በዚህም መሠረት :-

የ2018 የ777 ዳግም ደረጃ መንገድ ህብረተሠቡን በማስተባበርና በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ በዞኑ ህዝብ ላይ ለፈጠሩት ህዝባዊ አንድነት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ

የ2018 ምርጥ መስህብ አጆራ መንትያ ፏፏቴ
የ2018 አርኤል በጎ አድራጎት ማህበር
የ2018 ተጽዕኖ ፈጣሪ ማህበራዊ ሚዲያ ሄኖክ ታደሰ
የ2018 የህይወት ዘመን አገልግሎት ዶክተር ፍቅሩ ገለሶ
የ2018 አለምአቀፍ አስጎብኚ ሴና ቱር
የ2018 በጤና ዘርፍ ዶክተር ዳኛቸው ዮሐንስ
የ2018 ለከምባታ ልማት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዶክተር ግዛቸው ከበደ

የ2018 ማህበራዊ ሚዳዲያን ለበጎ ዓላማ ይድነቃቸው ያሬድ እና ቢኒያም ዓለሙ

የ2018 ምርጥ ዶክመንተሪ ረታ ዓለሙ

የ2018 የከምባታ የባህል ሙዚቃ ዘርፍ አሸናፊ አርቲስት ዙሪያሽወርቅ አበራ

የ2018 በወንዶች የሙዚቃ ዘርፍ ድምጻዊ ከተማ ገብረመድህን

የ2018 ባህላዊ ምግብ አዘገጃጀት ትሁት አየለ

የ2018 በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ልዩ ተሸላሚ ለመጣው ለውጥ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ደረበ ዮሐንስ

የ2018 ልዩ ተሸላሚ ታላቅ መሪ ዘርፍ መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ

የ2018 ልየ ተሸላሚ በደቡብ አፍሪካ የከምባታ ልማት ማህበር

የ2018 ሞዴል አርሶ አደር በአካባቢው ላመጣው የሥራ ባህል ለውጥ ልዩ ተሸላሚ ወጣት አብነት ዴላሞ

የ2018 በዞኑ ልማት ላይ ላበረከቱት አበርክቶ ልዩ ተሸላሚ የተከበሩ ወይዘሮ ማርታ ልውጂ

የ2018 የሥራ ፈጠራና የልማት ተሳትፎ አርበኝነት ልዩ ተሸላሚ አቶ አበበ አበሞ ሆነዋል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊና የዋና አስተዳዳሪውን ተወካይ አቶ ሀይሉ ሀደሮና የከምባታ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችና ዓለም አገራት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.