3 months ago
ስኳር ፋብሪካው ያሉበት ውስብስበ ችግሮች ካልተፈቱለት ለግንባታ የፈጀውን የ341.1 ሚሊዮን በብድርን ለመከፍል እንደሚቸገር ፓርላማው አሳሰበ
#ethiopia | የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ያሉበት ውስብስበ ችግሮች ካልተፈቱለት ለግንባታ የፈጀውን የ341.1 ሚሊዮን ዶላር ብድርን ለመከፍል እንደሚቸገር ፓርላማው አሳሰበ፡፡
በህዝብ ተወካይዎች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ 2 እና 3 የስኳር ፋብሪካዎች እና የኦሞ ኩራዝ 5 ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክትን ተመልክቶ የግብረ መልስ ሪፖርት አሰናድቷል፡፡
በሪፖርቱ መሰረት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የተገነባው በብድር በተወሰደ የ341.1ሚልዮን ዶላር ሲሆን በቀን ፋብሪካው የሚፈጨው የአገዳ መጠን 12 ሺህ ቶን ነው፡፡
ይሁንና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤት፣ በውሃ፣ በባንክና በኢንተርኔት አገልግሎት እጥረት እና በጥቅማጥቅምና በደመወዝ ማነስ ምክንያት ፋብሪካውን ለቀው እየሄዱ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ያህል እያመረተ እንዳልሆነ ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም የፋይናንስ አቅርቦት እና የግብዓት አቅርቦትን የመሳሰሉ ከፍተት ችግሮች አሉበት ተብሏል፡፡
በመሆኑም ፋብሪካው ያለበትን የእዳ ጫና ተወጥቶ ትርፋማ እንዲሆን፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተጀመሩ የመስኖና የመብራት ኃይል የሰብስቴሽን ግንባታዎችን በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሳስቧል፡፡
የባለሙያዎችን ፍልሰት ለመግታት የበረሃ አበል፣ የደመወዝ ማሻሻያና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ውሃ፣ ባንክ፣ ኔትወርክ አገልግቶቶችን ማሟላትም ወሳኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ ባደረገው የመስክ ምልከታም ከፍተኛ የሃበት ብክነት መመልከቱን አረጋግጧል፡፡
በዚህም ለፋብሪካው ተብለው የተገዙ 75% የሚሆኑ ውድ ማሽነሪዎች ያለምንም መጠለያ በሜዳ ላይ ተበትነው እንደሚገኙ ቋሚ ኮሚቴው ተመልክቻለው ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተጋዙ ማሽነሪዎች የዝገትና የብልሽት አደጋ እንደተጋረጠባቸው በሪፖርቱ መረጋገጡን ተመልክተናል፡፡
ፕሮጀክቱ ተገቢ የሆነ የቴክኒክና የኢኮኖሚ የአዋጭነት ጥናት ሳይከተል መጀመሩን የጠቀሰው ሪፖርቱ አሁን ላይ የግንባታው ሂደት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲል አስረድቷል፡፡
የፕሮጀክቱን የቀጣይ እጣ ፈንታ ለመወሰን ደግሞ ተገቢውን የቴክኒክ ምርመራ ለማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሉበት ቡድን በማቋቋም በሜዳ ላይ የሚገኙ ማሽነሪዎች አሁን ላይ ያላቸውን የቴክኒክ ብቃትና የጉዳት መጠን በዝርዝር እንዲጠና አሳስቧል፡፡
የፋብሪካውን የአዋጭነት ክለሳ (Feasibility Review) በማካሄድ ፕሮጀክቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ማስቀጠል ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ እንዲጠናም አክሏል፡፡
#ሸገር ኤፍ ኤም
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #amn

4 months ago
የወልቂጤ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭት ተቋረጠ
#ethiopia | በደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስር የሚገኘው የወልቂጤ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች፣ ከመስከረም 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የነበረበት የደመወዝ ማሻሻያ አልተደረገልንም በሚል መጋቢት 16 ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን አስታወቁ።
ሠራተኞቹ በጻፉት ደብዳቤ፤ "ሌሎች አቻ ቅርንጫፎች ጥቅማጥቅሙ ተከብሮላቸው እኛ ጋር ግን ምላሽ የሚሰጥ አካል ጠፋ" ብለዋል።
በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት እስከማስወጣት መገደዳቸውንና ማህበራዊ ሕይወታቸው መቃወሱን በምሬት ገልጸዋል።
በአማርኛ፣ በቀቤንሲኛ፣ በየሚኛ፣ በጉራግኛና በማረቂኛ ቋንቋዎች የሚተላለፈው ስርጭት ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ተቋርጦ እንደሚቆይ ሠራተኞቹ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
#ኢትዮጵያ #ወልቂጤ #ደቡብ_ሬድዮና_ቴሌቪዥን #የደመወዝ_ማሻሻያ #የሠራተኞች_መብት #getu_temesgen #ዜና #gurage #wolkite

8 months ago
ከፌደራል መንግሥት ለትግራይ ክልል የሚላከው በጀት ተቋርጧል?
#ethiopia | ከፌደራል መንግሥቱ ለትግራይ ክልል የሚላከው በጀት ለሁለት ወራት ያህል አልተለቀቀም ሲሉ የትግራይ ፕላን ኮሚሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃንሳ ተኽላይ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናገሩ።
ይህ የተሰማው ባለፉት ወራት በፌደራል መንግሥት እና ሕጋዊ ዕውቅናው በተሰረዘበት በህወሓት መካከል ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል ተብሎ በሚሰጋበት ወቅት ነው።
ወደ ክልሉ የሚገባው ነዳጅም በቂ ባለመሆኑ በአጠቃላዩ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ላይ ችግር ተፈጥሯል ሲሉ ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው የክልሉ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
ከተቋረጡ በጀት መካከል 844 ሚሊዮን ብር የካፒታል በጀት መሆኑን የተናገሩት የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኃላፊ፣ በተጨማሪም ከፌደራል መንግሥት በድጓማ የሚሰጥ እንዲሁም ከትግራይ ጦርነት በኋላ በየወሩ ይከፈል የነበረ ገንዘብ ይገኝበታል።
በአጠቃላይ ለ2018 ዓ.ም. ለትግራይ የተመደበው 18.8 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት፣ ለአስራ ሁለት ወራት ተካፍሎ፣ በየወሩ የሚላክ ሲሆን ነገር ግን ይህ ገንዘብ ከጥቅምት ወር ጀምሮ መቆሙን ኃላፊዋ ጨምረው ገልጸዋል።
ወደ ትግራይ ክልል የሚላከው በጀት መቋረጡን በተመለከተ እስካሁን ከፌዴራል መንግሥት የተሰጠ ይፋዊ ማብራርያ የለም።
ቢቢሲ ከገንዘብ ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ መሠረት ለመስከረም ወር 481 ሚሊዮን ብር ወደ ክልሉ የተላከ ቢሆንም ሰፊ ክፍተት በመኖሩ አዲሱ ጭማሪ ለመንግሥት ሠራተኞች ሊከፈል አለመቻሉን ወይዘሮ ሃንሳ አስታውሰዋል።
#bbc

9 months ago
" አሁን ያለባቸውን ችግር በራስ አቅም ይፍቱ " - የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
#ethiopia | የደመወዝ ማሻሻያው በወቅቱ በሁሉም አካባቢዎች ለምን ተፈጻሚ መሆን እንዳልቻለ ማብራሪያ እንዲሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተጠይቋል።
ኮሚሽኑ ጥያቄውን የተጠየቀው ዛሬ የሶስት ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለህዘብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት ስራ ሰምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄ ያቀረቡት ወ/ሮ ጀማነሽ ወ/ሚካኤል ፤ የደመወዝ ማሻሻያው መልካም መሆኑን ጠቅሰው " ክፍያው እስከ ጥቅምት አጋማሽ እንዲከፈል ቢታዘዝም እስካሁን የደመወዝ ማሻሻያ ያልደረሳቸው አካባቢዎች አሉ " ብለዋል።
ስራ እንዳይስተጓገል በሁሉም ደረጃ ለምን በወቅቱ የደመወዝ ማሻሻያው ተፈጻሚ መሆን አልቻለም ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎቹ መልስ የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) በደመወዝ ክፍያው ላይ ለተስተዋለው ችግር ክልሎችን ተጠያቂ አድርገዋል።
አስቀድሞ የፌዴራል መንግስት ደመወዝ ማሻሻያ ሊሰራ ሲል የሰራው በቀድሞ መረጃ መሰረት መሆኑን ተናግረው ማሻሻያ የተሰራው ክልሎች በሰጡት መረጃ መሰረት ነው ብለዋል።
አንዳንድ ክልሎች ማሻሻያው ከተሰራ በኋላ " ያንሰናል " የሚል ቅሬት በደብዳቤ እና በአካል ማቅረባቸውን ያስረዱት ምክትል ኮሚሽነሩ " ከአንዳንድ የክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር በጉዳዩ ላይ ተነጋግናል ችግሩም የእኛ ሳይሆን የእነሱ መሆኑን ተማምነናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ችግሩ በስፋት የተፈጠረው በቀድሞ ደቡብ ክልል ስር በነበሩ ክልሎች መሆኑን አስታውሰው " እኛ ማሻሻያ የሰራነው ከሰኔ 2016 ዓ.ም በፊት በቅጥር ላይ ላሉ ሰራተኞች ነው " ብለዋል።
ከዚያ ወዲያ ለነበሩ ሰራተኞች ቅጥር ኮሚሽኑ እንደማይመለከተው ተናግሮ አሁን ያለባቸውንም ችግር " በራስ አቅም ይፍቱ " ሲሉ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ችግሩ ከክልሎች እንጂ ከኮሚሽኑ እንዳልሆነ ቢገልጽም ሰራተኞች ደመወዙ እንዲከፈላቸው የክትትል ስራ እንደሚሰራ መግለጹን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰን የሚያስችል ቦርድ መቋቋሙ ተገለጸ
#ethiopia | ዝቅተኛ የሰራተኞች ደመወዝ ወለል እንዲወስን የሚያስችል ቦርድ መቋቋሙን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በተያዘው በጀት አመት ቦርዱ በሚያቀርበው ጥናት መሰረት የሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ይወሰናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮንፌድሬሽኑ የውጭና የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ አቶ አያሌው አህመድ ተናግረዋል፡፡
ቦርዱ ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮን በመውሰድ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ የሰራተኞችን ገቢና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች በማጥናት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የሚያጠና እንደሆነ የተናገሩት ሃላፊው፤ ከመንግስት፤ ከአሰሪዎችና ከኮንፌድሬሽኑ የተውጣጡ አባላት እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሃላፊው አያይዘውም ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ መደረጉን በማስታወስ፤ ደመወዝ ያልተጨመረላቸውና የዝቅተኛ ተከፋይ የሆኑት በአንድ ገበያ እኩል ሊገበያዩ የማይችሉ በመሆኑ ዝቅተኛው የደሞዝ ወለል በተያዘው በጀት አመት ሊወሰን ይገባል ብለዋል፡፡
በኢንዱስትሪዎችና በግል የልማት ተቋማት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች አነስተኛ ደመወዝ የሚያገኙ በመሆኑ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌድሬሽን ተደጋጋሚ ጥሪን ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህም የተቋቋመው ቦርዱ በሚያሳየው የጥናት ውጤት በበጀት አመቱ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ይወሰናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሃላፊው አመላክተዋል ያለው መናኸሪ ኤፍ ኤም ነው፡፡

10 months ago
የገቢዎች ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል ይፋ ሆነ‼️
መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን ለማስፈጸም ለመንግሥት ሠራተኞች እና አመራሮች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥናቱ ለመንግሥት ቀርቦ ተወስኗል፡፡
በዚሁ መሠረት ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሰመንግሥት ሠራተኞች፣ ተሿሚዎች እና
የህዝብ ተመራጮች ተግባራዊ እንዲደረግ የገንዘብ ሚኒስቴር መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በቁጥር በበ18/6/134 በተጻፈ ደብዳቤ ገልጾልናል፡፡
ውሳኔውን ለማስፈጸም የተዘጋጀው የደመወዝ ማስተካከያ መመሪያ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጉባኤ ታይቶ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ሲሆን፣ በፍትህ ሚኒስቴርም መመሪያ ቁጥር 1110/2018 ተብሎ የተመዘገበና በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ መጫኑን አስታውቆናል፡፡
የመንግሥት ሠራተኞችን የደመወዝ ማስተካከያ መጠን መሠረት በማድረግ የልዩ የደመወዝ ስኬል ተጠቃሚዎችን የደመወዝ ማሻሻያ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዘጋጅቶ ለየተቋማቱ እንዲያስተላልፍ በመንግሥት በተወሰነው መሠረት-
1. የተሻሻለውን የተቋሙ የደመወዝ ስኬል ሠንጠረዥ፣
2. የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ሠንጠረዥ እና
3. የደመወዝ ስኬል ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር
1110/2018፣
ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን እየላክን፣ በጀቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር በመጠየቅ ክፍያውን መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም ውሳኔውን በፍጥነት በማስፈጸም ውጤቱን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንድታስታውቁን እናሳስባለን፡፡
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
seledadotio

Sponsored by
Surafel
10 months ago
አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆነ
#ethiopia | አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆኗል።ለመንግሥት ሰራተኞች የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ከዚህ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው አዲሱ የደመወዝ እርከን እንደሚከተለው ቀርቧል።

11 months ago
ለመንግሥት ሠራተኛው የቤት አቅርቦት ታስቧል
የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድኅን ሽፋንን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎች እንደሚወሰዱ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መረጃ እንዳመለከተው፤ መንግሥት ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።
ሆኖም የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድኅን ሽፋንን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎች ይወሰዳሉ ብሏል።
መንግሥት ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን የመንግሥት ሠራተኛ ዝቅተኛ የክፍያ ሁኔታ እና ተያይዞ የመጣውን የኑሮ ጫና በአንድ ጊዜ በሚደረግ የደመወዝ ማሻሻያ ሊቀርፈው እንደማይችል ይገነዘባል ያለው የኮሚሽኑ መግለጫ፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብልፅግና ምዕራፍ ሁሉም ዜጋ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብሎ ደግሞ ያምናል።
ስለሆነም ከሚወሰዱ ሌሎች ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን ገልጿል።
Seledadotio

12 months ago
የፋብሪካ ሰራተኞች ደመወዝስ?
በፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች ወርሃዊ ገቢ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ጥሪ አቀረቡ።
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በፋብሪካዎች የሚሰሩ ሠራተኞች እጅግ በጣም አነስተኛ ደመወዝ የሚያገኙ በመሆኑ መንግሥት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን ጠየቁ።
አቶ ካሳሁን ፎሎ መንግሥት በቅርቡ የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ እንደሚጨምር ማስታወቁን በአዎንታ እንደተቀበሉት ገልጸው፥ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚሰሩ ሠራተኞች ከ1,000 ብር (7 ዶላር) እስከ 3,000ብር (22 ዶላር) የሚደርስ ወርሃዊ ደሞዝ እንደሚያገኙ ገልፀዋል።
ይህም ዝቅተኝእ ክፍያ ለመኖር ከሚያስፈልገው ደመወዝ እጅግ በጣም ያነሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት በመስጠት መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ካሳሁን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ለመወሰን ሕጋዊ መሠረት እንዳለ ተናግረዋል። "በ2011 የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን" መቀመጡን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ አዋጁ በተግባር ላይ እንዲውል ጠይቀዋል።
ከመጪው መስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል።
በዚህ ማሻሻያ መሰረት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ ማደጉም ታውቋል።
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከ21 ሺህ 492 ብር ወደ 39 ሺህ ብር እንዲያድግ መደሩኩም ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።via :ayu

የደመወዝ ማሻሻያው ሰራተኛውን ለበለጠ ምርታማነት ያነሳሳል - አቶ ካሳሁን ፎሎ
መንግስት የሰራተኛውን ደመወዝ ለማሻሻል ያሳለፈው ውሳኔ ሰራተኛው ለበለጠ ምርታማነት እንዲነሳሳ ያደርጋል አሉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ካሳሁን ፎሎ።
ፕሬዚዳንቱ ከፋና የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኞች የሚያቀርቡት ጥያቄ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ምላሽ እንደሚያገኝ ማሳያ ነው ብለዋል።
ይህም በመንግስት እና በሰራተኛው መካከል የበለጠ መቀራረብንን እና መተማመንን እንደሚያሳድግ ተናግረው፤ ማሻሻያው በመንግስት እና በሰራተኛው መካከል ያለውን መተማመን ይበልጥ ያሳድጋል ነው ያሉት።
ማሻሻያው ሰራተኛው የበለጠ ለምርታማነትና ለጥራት እንዲነሳሳ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ክስተቶች ጫና ውስጥ ሆና የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ትኩረት መስጠቷንም ነው የጠቆሙት።
መንግስት ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰራተኛው የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል።
ለሰራተኛው የደመወዝ ማሻሻያም ተጨማሪ 160 ቢሊየን ብር በጀት የመደበ ሲሆን፤ ሰራተኛው ሥራውን በውጤታማነት በመፈፀም ለሀገራዊ ዕድገት የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል።
FBC

"የተፈቀደው አዲሱ የደምወዝ ስኬል ይህ ነው" በሚል የሚዘዋወረው ምስል ሀሰተኛ ነው የፌዴራል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
#ethiopia | ከሰሞኑ የኢፌዴሪ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተከትሎ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህንን መረጃ ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች “የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ ስኬል ይህ ይመስላል” የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተዘዋወሩ እና በርካቶችን እያሳሳቱ መሆኑን ተመልክተናል።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) እነዚህን “የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል” በሚል በአንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚናፈሱ አሳሳች መረጃዎች እንድትተዋቸው በሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንግስት ደምወዝን አስመልክቶ ትክክኛውን መረጃ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካይነት ብቻ የሚወጣ መሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚዘዋወሩ እና ምንጫቸው ያልታወቀ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት መረጃዎችን በጥንቃቄ መከታተል እና ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ በማጣራት ማረጋገጥ የሁልግዜ ተግባራችን ሊሆን እይገባል።

የደመወዝ ማሻሻያውን ተከትሎ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች…
መንግስት ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የደመወዝ ማሻሻያውን ምክንያት በማድረግ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል፡፡
የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፥ የደመወዝ ማሻሻያው መንግስት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የወሰደው ርምጃ ነው፡፡
የደመወዝ ማሻሻያ ውሳኔው ከንግድ ስርዓቱ ጋር ምንም የሚያገናኘው ጉዳይ እንደሌለ ገልጸው፥ ምርትና አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ማሻሻያውን በማሳበብ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
መንግስት ዋጋ እስከሚጨምር በሚል ምርት በመደበቅ በገበያ ላይ እጥረት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ነጋዴዎች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥
ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ምርት የሚደብቁና ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል ህብረተሰቡ ለሚመለከታቸው ተቋማት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መንግስት ለሰራተኛው የደመወዝ ማሻሻያ ተጨማሪ 160 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡን መግለጹ ይታወቃል፡፡

በግል ተቋማት ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለሉን ውሳኔ መስጠት ያስፈልጋል ሲል ኢሰማኮ አሳሰበ
በተለያዩ የግል ተቋማት ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤ ዝቅተኛ የደመመዝ ወለሉን ውሳኔ መስጠት ያስፈልጋል ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አሳስቧል።
ኮንፌዴሬሽኑ በትላንትናው ዕለት የመንግሥት ሠራተኞችን የደመወዝ ክፍያ በተመለከተ ይፋ የተደረገው ማሻሻያ የሚበረታታ ስለመሆኑ የገለጸ ሲሆን፤ ነገር ግን በግል መስሪያ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ አጠቃላይ የሀገሪቱን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
የኮንፌዴሬሽኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ሰሎሞን ዜና፤ "መንግሥት ለሠራተኞቹ ያደረገው የደመወዝ ማሻሻያ በተደጋጋሚ ኮፌዴሬሽኑ ሲያነሳቸው ለነበሩ ሀሳቦች በከፊል መልስ የሰጠ ስለመሆኑ ማሳያ ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በመሆኑም ከመንግሥት በተጨማሪ የግል ሠራተኞችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የሚጠበቀው የአጠቃላይ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ አሁንም ድረስ ጥያቄ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች በጣም አነስተኛ የሆነ ክፍያን እንደሚያገኙ አንስተዋል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአውሮፓ ሕብረት ባወጣው ሕግ መሠረት፤ ማንኛውም ምርቶችን ለመቀበል ምርቶቹ ከሚመረቱበት አግባብ በተጨማሪ የሥራ ቦታው ለሠራተኞች ምቹ ካልሆነ፣ እድሜያቸው ለሥራ ያልደረሱ ሠራተኞች ከተቀጠሩ እንዲሁም፤ ክፍያው በጣም ዝቅተኛ ከሆነ ወደ አውሮፓ ሀገራት እንዳይገቡ መከልከሉን አስታውሰዋል።
በመሆኑም የግል ሠራተኞችንም ተጠቃሚ የሚያደርገው የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ውሳኔን በቅርቡ መንግሥት በተገቢው ሁኔታ ሊመለከተው የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የደመወዝ ቦርድ የሚያቋቁመውን አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቀች ስድስት ዓመታትን ብታስቆጥርም፤ እስከ አሁን ግን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አልወሰነችም። በዚህም ምክንያት በግሉ ዘርፍ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጫና እየደረሰ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ይገለጻል።

❗️በኢትዮጵያ የተደረገውን የደመወዝ ማሻሻያን በመጠቀም የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉት አካላት ላይ መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ።
ህጋዊ እርምጃም እንደሚወሰድ ተገልፇል።
ህጋዊ እርምጃም እንደሚወሰድ ተገልፇል።
12 months ago
የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ የሚከሰቱ የዋጋ ንረትን ለመግታት ማስጠንቀቂያ ተሰጠ::
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ሚኒስቴሩ፣ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የደመወዝ ጭማሪ፣ የሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል ያለመ አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ነጋዴዎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የዋጋ ንረት ለመፍጠር እና ሰው ሠራሽ የምርት እጥረት ለማስከተል ሲሞክሩ መታየቱን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ እንዳለው፣ "በገንዘብ ፍቅር የታወሩ" ጥቂት ነጋዴዎች፣ የሠራተኞችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት መሯሯጣቸው ተስተውሏል።
ይህንን ድርጊትም "አሳፋሪ" ሲል አውግዟል።
በመሆኑም፣ ሚኒስቴሩ ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ፣ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ ምርት የሚደብቁ ወይም አላግባብ የሚያከማቹ ነጋዴዎች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
በተጨማሪም፣ የንግድ መዋቅሩ ከፀጥታ እና ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር የገበያ ማረጋጋት ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና በአጥፊዎች ላይም አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ አስተላልፏል።
Via የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ
#fastmereja I ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡
📌 ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 6 ሺህ ብር
📌 ፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 39 ሺህ ብር
📌የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ 11 ሺህ 500 ብር
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡
በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።
የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።
ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።
ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።
ዘገባው የፋና ነው

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ መወሰኑን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ
በዚህ ማሻሻያ፦
1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
2. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
3. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።
4. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ ይደረግበታል ተብሏል።

የደመወዝ ጭማሪ
መንግስት ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ ወሰነ
ከሚወሰዱ ሌሎች ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

3. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11, 500 ይሻሻላል።
4. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ ይደረግበታል ተብሏል፡፡(Via;አዩ)

1 year ago
" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ነው ! " - የምክር ቤት አባል
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተዋል።
የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ይገኛሉ።
እስካሁን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ከኑሮ ውድነት፣ ከመንግሥት ሰራተኞች ፣ ጤና ባለሙያዎች እና መምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይገኝበታል።
ጥያቄው የቀረበው በምክር ቤት አባሉ አቶ ግዛቸው አየለ ነው።
ምን አሉ ?
" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎችን እና መምህራንን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግሥት ሰራተኛን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል አኳያ በመንግሥት ምላሽ ዙሪያ ማብራሪያ ቢሰጥበት።
በተጨማሪ መንግሥት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል ይሁን እንጂ ካለው የቤት ፈላጊ ቁጥር ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። መንግሥት በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በከተሞች የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
የምክር ቤቱ ስብሰባ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

Comments