ለመንግሥት ሠራተኛው የቤት አቅርቦት ታስቧል
የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድኅን ሽፋንን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎች እንደሚወሰዱ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መረጃ እንዳመለከተው፤ መንግሥት ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።
ሆኖም የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድኅን ሽፋንን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎች ይወሰዳሉ ብሏል።
መንግሥት ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን የመንግሥት ሠራተኛ ዝቅተኛ የክፍያ ሁኔታ እና ተያይዞ የመጣውን የኑሮ ጫና በአንድ ጊዜ በሚደረግ የደመወዝ ማሻሻያ ሊቀርፈው እንደማይችል ይገነዘባል ያለው የኮሚሽኑ መግለጫ፤ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብልፅግና ምዕራፍ ሁሉም ዜጋ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብሎ ደግሞ ያምናል።
ስለሆነም ከሚወሰዱ ሌሎች ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን ገልጿል።
Seledadotio

11 months ago