Logo
SeledaPost
የገቢዎች ሚኒስቴር የደመወዝ ስኬል ይፋ ሆነ‼️
መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን ለማስፈጸም ለመንግሥት ሠራተኞች እና አመራሮች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥናቱ ለመንግሥት ቀርቦ ተወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሰመንግሥት ሠራተኞች፣ ተሿሚዎች እና
የህዝብ ተመራጮች ተግባራዊ እንዲደረግ የገንዘብ ሚኒስቴር መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በቁጥር በበ18/6/134 በተጻፈ ደብዳቤ ገልጾልናል፡፡

ውሳኔውን ለማስፈጸም የተዘጋጀው የደመወዝ ማስተካከያ መመሪያ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጉባኤ ታይቶ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ሲሆን፣ በፍትህ ሚኒስቴርም መመሪያ ቁጥር 1110/2018 ተብሎ የተመዘገበና በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽ መጫኑን አስታውቆናል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞችን የደመወዝ ማስተካከያ መጠን መሠረት በማድረግ የልዩ የደመወዝ ስኬል ተጠቃሚዎችን የደመወዝ ማሻሻያ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዘጋጅቶ ለየተቋማቱ እንዲያስተላልፍ በመንግሥት በተወሰነው መሠረት-

1. የተሻሻለውን የተቋሙ የደመወዝ ስኬል ሠንጠረዥ፣
2. የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ሠንጠረዥ እና
3. የደመወዝ ስኬል ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር
1110/2018፣

ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን እየላክን፣ በጀቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር በመጠየቅ ክፍያውን መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም ውሳኔውን በፍጥነት በማስፈጸም ውጤቱን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንድታስታውቁን እናሳስባለን፡፡
ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.