7 hours ago
በ2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዟል
#ethiopia | በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የ2019 በጀት ዓመት የበጀት መግለጫ ማብራሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጥቅሉ አንድ ነጥብ 817 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡
ይህ የገቢ ዕቅድ በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት እንዳለው ጠቁመው፤ የ2019 በጀት ዓመት በጀትን 88 ነጥብ 7 በመቶውን ከታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ መታቀዱንም ጠቁመዋል።
የታክስ ገቢ ዕቅዱን ለማሳካትም በታክስ ፖሊሲና በታክስ አስተዳደር ረገድ የተያዙ ማሻሻያዎችን፣ የታክስ ዲጂታላይዜሽንና የኤክሳይዝ ስታምፕ አሠራርን በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
ለ2019 በጀት ዓመት የተቀመጠው የተጣራ የበጀት ጉድለት መንግሥት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ከተቀመጠው ግብ ጋር የተጣጣመ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡
ከብሔራዊ ባንክ በጀት ጉድለት መሸፈኛ የሚወሰደው ብድር ሙሉ በሙሉ ቆሟል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የዋጋ ንረትን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ማገዙን ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ ተግባራዊ በመደረጉ ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲውን የሚያጠናክሩ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ ሲሆን፤ ብሔራዊ ባንክ የዘረጋውን ዘመናዊ የገንዘብ ፖሊሲ ለማስጠበቅ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በምግብ ዘይትና በመሠረታዊ ሸቀጦች እንዲሁም መድኃኒቶችን በተመሳሳይ የድጎማ በጀት በመመደብ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የ10 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ግምት የተቀመጠ ሲሆን፤ በኢኮኖሚ እድገቱ ኢንደስትሪ፤ አገልግሎት ዘርፍና ግብርና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት #ጋዜጣፕላስ #በጀት2019 #ታክስ #የልማትእቅድ #አፍሪካ #gazette_plus

1 month ago
የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ሰፊ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነውበታል ተባለ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ እንደገለጹት የሀገሪቱ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸውና ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው መስኮች መካከል አንዱ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ እንደተጠቆመው የሪፎርሙ ቀዳሚ ተግባር በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ የነበሩ ተቋማዊ ችግሮችን በመለየት ተገቢውን መፍትሄ መስጠት ነበር፡፡
በተለይም የይዘት ጥራትን ማሻሻልና ብዝሀነትን ማረጋገጥ፣ ተቋሙን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የህትመት ውጤቶችን ተደራሽነትና ስርጭት ማሳደግ እንዲሁም ዘመናዊ አደረጃጀትና መዋቅር መፍጠር የሪፎርሙ ዋና ዋና ግቦች ነበሩ፡፡
እነዚህ በመንግስት የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት ከዘርፉ እድገት ባለፈ የሀገሪቱን የጋራ ትርክት በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተመላክቷል፡፡
#የኢትዮጵያፕሬስድርጅት #ሚዲያ #ህትመት #ሪፎርም #የሚዲያእመርታ #መረጃ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ምክር ቤቱ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል
*****************
6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱን 18ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በአንጎላ ሪፐብሊክ፣ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ረፐብሊክ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግሥት እና በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥታት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረቡ አራት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በመጨረሻ ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል የአገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ እንደሚያፀድቅም የሚጠበቅ መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ebc #ethiopia #hopr

3 months ago
ጣሊያንን ጨምሮ አዳዲስ ሀገራት የኢትዮጵያውያን የሥራ መዳረሻ ሆኑ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባወጣው የሰባት ወራት የሥራ ክንውን ሪፖርት መሠረት፣ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዘርፍ አዳዲስና ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን አስታውቋል።
ዕቅድን ያለፈ አፈጻጸም፦ ባለፉት ሰባት ወራት 435 ሺህ ዜጎችን ለማሰማራት ታቅዶ፣ ዕቅዱን በማለፍ ከ447 ሺህ በላይ ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል።
አዳዲስ መዳረሻ ሀገራት፦ መንግሥት ከነባር አምስት ሀገራት በተጨማሪ ጣሊያንን ጨምሮ አራት አዳዲስ ሀገራትን የሥራ መዳረሻ በማድረግ የስምሪት አማራጮችን አስፍቷል።
የባለሙያዎች ስምሪት፦ ስምሪቱ ከቤት ውስጥ ሥራ ባለፈ፣ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው። ይህም በሁለትዮሽ ድርድር የተገኘ ትልቅ ድል መሆኑ ተገልጿል።
ቀጣይ ድርድሮች፦ ከዩናይትድ ኪንግደም (UK)፣ ከኢራቅ እና ከኦማን ጋር የሚደረጉ የሥራ ስምሪት ድርድሮች ከጫፍ መድረሳቸው ተጠቁሟል።
በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባለፉት ሰባት ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የዓለም የቡና ገበያ መናወጥ፦ የኢትዮጵያ ላኪዎች 'ምርታችሁን ቶሎ ሽጡ' ተባሉ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተከትሎ፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች ምርታቸውን በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ አሳሰበ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንደገለጹት፣ ባለፉት ሁለት ወራት የቡና ዋጋ ከ4 ዶላር ወደ 2.8 ዶላር ዝቅ ብሏል።
ዋጋው በቀጣይም እስከ 2.5 ዶላር ሊወርድ ስለሚችል፣ ባለድርሻ አካላት ምርቱን አከማችተው ለከፍተኛ ኪሳራ እንዳይዳረጉ ጥሪ ቀርቧል።
በበጀት ዓመቱ 600 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ ውጤታማ ለመሆንም ላኪዎች በስፔሻሊቲ ቡና ጥራት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠይቋል።
በተጨማሪም ቡናን ከአንድ ዓመት በላይ ማከማቸት ወይም በኮንትሮባንድ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው

4 months ago
ዚምባብዌ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚወሰድ አዲስ የኤች አይቪ መከላከያ መድኃኒት በይፋ አስጀመረች
ዚምባብዌ በዓመት ሁለት ጊዜ በመርፌ የሚሰጥና ውጤታማነቱ አስተማማኝ የሆነውን "ሌናካፓቪር" (Lenacapavir) የተሰኘ የኤች አይቪ መከላከያ መድኃኒት በብሔራዊ ደረጃ በይፋ በማስጀመር ከአለም ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች።
የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዳግላስ ሞምቤሾራ (ዶ/ር) መድኃኒቱ ኤድስን እንደ የህዝብ ጤና ስጋት ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
በጊልያድ ሳይንስ (Gilead Sciences) የበለጸገውና ባለፈው ህዳር ወር በሀገሪቱ የፈቃድ ማረጋገጫ ያገኘው ይህ መድኃኒት፣ በየቀኑ የሚወሰዱ የቅድመ ተጋላጭነት መከላከያ (PrEP) መድኃኒቶችን አስፈላጊነት የሚያስቀር ነው።
በመጀመሪያው ምዕራፍ በ24 ማዕከላት ውስጥ ለሚገኙ 46 ሽህ ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ይሰጣል የተባለ ሲሆን፤ ቅድሚያ ለወጣት ሴቶች፣ ለታዳጊዎች እና ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጥም ይሆናል፡፡
ፕሮጀክቱ በአሜሪካ መንግስት እና በግሎባል ፈንድ ድጋፍ የሚከናወን ነው። መድኃኒቱ በዓመት ሁለት ጊዜ በመርፌ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከሞላ ጎደል መቶ በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተረጋግጧል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህንን አዲስ መድኃኒት "ከክትባት ቀጥሎ ያለ ምርጥ አማራጭ" ሲሉ ማወደሳቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በዚምባብዌ በአሁኑ ወቅት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከኤች አይቪ ጋር የሚኖሩ ቢሆንም፣ ሀገሪቱ የተያዘውን የሶስቱን 95 የህክምና ግቦች ማሳካት የቻለችና የበሽታውን ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰች ሀገር መሆኗ ይነገራል።
@የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት
የኢቢሲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ማንነት?
#ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ የስነዳ ሥራ ታሪካቸው መዝገበ አእምሮ ላይ የሚሰነድላቸው ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ይጠቀሳሉ።ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክና ባህል ዙሪያ በርካታ መፅሐፍትን በመድረስ ትልቅ አሻራ አኑረዋል።ከ30 በላይ መፅሀፍትን የደረሱት እኒህ ሰው የሀይማኖት ሰባኪ፣ ፀሀፊ እና ዲስኩር አቅራቢ በመሆን ለአገራቸው አገልግሎት ሰጥተዋል። የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን የመሠረቱት ዲያቆን ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ናቸው። በዛሬው ዕለት ደግሞ፣ የኢቢሲ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ተሹመዋል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ታሪክ ሰንደውታል።
#ቅድመ ነገር
በነገረ ሀይማኖት፣ በሥነጽሑፍ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በጥናትና ምርምሮች ከምልዓት በተጠጋ መሰጠት ያገለገሉ ሰው ናቸው፣ ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት።
የተወለዱት ደሴ ከተማ ነው። በወላጅ አባታቸው የንግድ ሥራና እንቅስቃሴ ምክንያት፣ ነፍስ በማያውቁበት እድሜ የመላ ቤተሰቡ ቋሚ መኖሪያ ወደ ባህርዳር ከተማ ተዛወረ። በመሆኑም አብዛኛውን ለሕይወት ስንቅ ሆኖ የቆያቸውን የእውቀት መሠረት ያገኙት በዚሁ በባህርዳር ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጼ ሰርጸ ድንግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መለስተኛ ደረጃን በፋሲል መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጣና ሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚህ መደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ወላጅ እናታቸው ለትምህርትና ንባብ የሰጡት ትኩረት የንባብ ልምዳቸውን በእጅጉ እንደቃኘው በተለያየ ጊዜ በሰጧቸው ቃለመጠይቆች ደጋግመው ያወሳሉ።
#የሥነጽሑፍ ፍቅር
በልጅነት እድሜ ከዘመናዊ ትምህርት ጎን ለጎን፣ ባደጉበት ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርትን በሚገባ ቀስመዋል። ይህም አገልግሎታቸው ከፍ ብሎ ቤተክርስትያንን በዲቁና እንዲያገለግሉ የክህነት መዓረግ አስገኝቷቸዋል። ከዚያም ባሻገር ወደ አካባቢው ከሚያቀኑ በእውቀትና በመንፈሳዊ ጽናት የታወቁ አባቶች መምህራን ብዙ ትምህርትን የመቅሰም እድል ነበራቸው፣ ተጠቅመዉበታልም።
ይህ ሁሉ ተዳምሮ በልጅነት እድሜ የተለያዩ ሥነጽሑፋዊ ሥራዎችን እንዲጽፉ፣ አልፎም በትምህርት ቤት በጠዋት የተማሪዎች ሰልፍ ሰዓት መድረክ ላይ ወጥተው እንዲያቀርቡ አስችሏቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳሉም በሰልፍ ሰዓት ለተማሪዎች ዜና ያቀርቡ ነበር። በንባብ የተገነባ መሠረት ላይ የተጣለ ማንነታቸውም ለሥነጽሑፍ በተለየ እንዲሳቡ አድርጓቸዋል።
#ከአዲስ አበባ እስከ ኬንያ
ከባህር ዳር አዲስ አበባ ያቀኑት በ1982 ዓ.ም ነው። አዲስ አበባ እንደገቡም ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ። በዚያም ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአቅራቢያ በሚገኘው በኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጡ ነበር።
የአንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ታድያ በፖለቲካ እንቅስቃሴ የተናጠችው ኢትዮጵያ፣ ወጣት ተማሪዎቿ ወደ ብላቴ እንዲሄዱ ተወሰነባት። ዲያቆን ዳንኤልም በዚህ መሠረት ወደብላቴ የውትድርና ማሠልጠኛ ከሄዱ ተማሪዎች መካከል ሆኑ። ይህ ከተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ወጣቶችን በአንድ እንዲሰባሰቡ እድል የፈጠረው አጋጣሚ፣ ለዳንኤል የተለያዩ ባህሎችን፣ የሀገር መልኮችን እንዲያዩ እድል የፈጠረላቸው ነበር።
የብላቴ ሥልጠና ተጠናቅቆ ምረቃ ሳይደርስ ግን ደርግ ወርዶ ኢሕአዴግ ገባ። በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶችም አብዛኞቹ ወደ ኬንያ ሄዱ። ዳንኤልም በኬንያ የተወሰኑ ወራት ቆይተው፣ ኢሕአዴግ መንበረ ሥልጣኑን አደላድሎ ከያዘ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ወጣቶች ሁሉ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተባለና ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ። በአንድ ዓመት ውስጥም የሦስት መንፈቅ ትምህርት ተከታትለው ዲፕሎማቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ተቀብለው አጠናቀቁ።
#መምህርነት
ከዚህ በኋላ በተመረቁ ተማሪዎች ምደባ መሠረት ሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር (በቀድሞ አጠራር) ደረሳቸው። ምንም እንኳ አዲስ አበባ ላይ ሥራ ያገኙና ምደባውን መተው የሚችሉ ቢሆንም፥ “እንዲሁ በነጻ የተማርኹትን ያህልም ቢሆን ማገልገል አለብኝ” በማለት ምድባውን ተቀብለው፣ እንደውም ‘ቢቻል ሰው ሊሄድ የማይመርጥበት ራቅ ያለ ስፍራ መድቡኝ’ አሉ። በጊዜው ግን አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት የደረሳቸው በሰሜን ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅሩ ነበርና በዚያ የአማርኛ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ።
በዚያም የመምህራን እጥረት ስለነበር፣ ከአማርኛ ባለፈ ታሪክ እና አካባቢ ሳይንስ (ጂኦግራፊ) ያስተምሩ ነበር። ከዚያ ጎን ለጎን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠትና በማስተማር የአካባቢውን ማኅበረሰብ አገልግለዋል።
የማገልገል ጽኑ ፍላጎት እና ባመኑበት ‘ለብቻም ቢሆን የመቆም’ ጽናት ውስጥ ሆነው፣ የመምህርነት አገልግሎታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባ ተመለሱ።
ቀጥለውም ዲፕሎማ በተመረቁበት ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል። ትምህርታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊትም ሆነ በኋላ፥ በማኅበረ ቅዱሳን በመደበኛ አገልግሎት ሠርተዋል። ሐሳብ አመንጭቶ መጽሐፍ ከመጻፍ በላይ የማሳተምና ማሰራጨት ክብደቱን በመረዳት የመጽሐፍ ህትመት ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ‘አግዮስ’ የተባለውን የራሳቸውን የመጽሐፍ ማሳተሚያና ማሰራጫ ከፍተው በዘርፉ ሠርተዋል።
ከዚህም ባሻገር የምክር አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም በ2010 ዓ.ም የመጣውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ፥ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።
#የመጽሐፍ ሥራዎች
መሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከሠላሳ ሦስት በላይ መጻሕፍትን ለአንባብያን አድርሰዋል። እነዚህም እንደ ‘ብቻዬን እቆማለሁ’፣ ‘ጠጠሮቹ እና ሌሎችም’፣ ‘የሰርቆ አደሮች ስብሰባ’ ከሚሉና ከመሳሰሉ ከተወሰኑ የወግ ስብስብ መጽሐፎች ባለፈ፣ ዳጎስ ያሉ በጥናትና ጥልቅ ንባብ ላይ የተመሠረቱ፣ ሃይማኖታዊ ብሎም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ናቸው።
ዳንኤል እስከ 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መሥራች ናቸው። ከዚህም ባሻገር የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን መሥራቾች መካከል ይገኙበታል። በዚህ ማኅበር ውስጥ የሚታተሙ መጽሔት፣ ጋዜጣና መጻሕፍት ዝግጅት ክፍል ላይም ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። ስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና ሐመር መጽሔትም ላይ በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቻቸው ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ በቅርብ በፋና ሚድያ ኮርፖሬት የቦርድ አባል ብሎም ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ለሀገር ይጠቅማል ብለው ባመኑበት መስክ እና ተቋም የቦርድ አባልና ሊቀመንበር ሆነዋል፣ ሠርተዋል።
‘የዳንኤል ክብረት ዕይታዎች’ የሚለው መጦመሪያ ድረገጻቸው ላይ የሚያሰፍሯቸው ጽሑፎች ብሎም በተለያዩ መድረኮች በመገኘት የሚያቀርቧቸውና የሚሰጧቸው ማኅበራዊ ኂሶች ብዙ ትኩረት የሚስቡና ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ፣ ናቸው። በቃል ብቻ ሳይሆን በመጽሐፎችም መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል። ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚሆኑ የሆኑ ሥራዎቻቸውም ጥቂት አይደሉም።
ብዙ የደከምኩባቸው የሚሏቸው ሁለት መጻሕፍት አሉ። አንደኛው ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘው በአቡነ ተክለሃይማኖት የሕይወት ታሪክ ዙሪያ የሠሩት ሲሆን ሌላው ‘አራቱ ኃያላን’ የተሰኘ መጽሐፍ ነው። በቅርብና መጨረሻ ላይ ለንባብ ካቀረቡት ዳጎስ ያለ መጠን ያለው ‘የትርክት እዳና በረከት’ መጽሐፋቸው በፊትም፣ ‘እጨጌ እንባቆም ከየመን እስከ ደብረሊባኖስ’፣ ‘ራዕየ ዮሐንስ’፣ ‘ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ’ የተሰኙ የመጽሐፍ ሥራዎቻቸው ከብዙ በጥቂት የሚጠቀሱ ናቸው።
#ቤተሰብ
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ከትዳር አጋራቸው ወይዘሮ ጽላት ጌታቸው ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በትዳር ቆይተዋል። በዚያም ሦስት ወንዶች (አቤሜሌክ ዳንኤል፣ ባሮክ ዳንኤል እና ባህራን ዳንኤል) እና አንዲት ሴት ልጅ (አንኪዮን ዳንኤል) አባት ለመሆን በቅተዋል።
ሙሓዘ ጥበባት የሚለውን ማዕረግ፣ ‘ኢትዮጵያዊው ሱራፊ’ የተሰኘውን መጽሐፍ ባስመረቁበት ወቅት ‘ስም ከግብር አብሮ ይሄዳልና...’ ሲሉ፣ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ የሰጧቸው ስያሜ ነው። ሙሓዘ ጥበባት ማለት ‘የጥበብ መፍሰሻ’ ማለት ነው።
#ምስክርነት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመገናኛ ብዙኃን አመራርና አሠራር ጥሩ እውቀትና ልምድ አለው፡፡ አዳዲስ አሠራሮች እንዲጎለብቱ ሃሳብ በማፍለቅና እንዲሳካ ጥረት የማድረግ ብቃት አለው፡፡ አሁንም የጋዜጠኞች ሙያዊ ነጻነትና የሚዲያው ኤዲቶሪያል አቅም እንዲጎለብት እንዲሁም ተቋማዊ አቅሙ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነፃነት ተስፋዬ የሚድያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ
##########
ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በይዘት ደረጃ ካየነው በባህል ኪነጥበበ እና በታሪክ ዙሪያ የኢትዮጵያን መልክ በፅሑፎቹ እና በንግግሮቹ ለማሳየት ከፍተኛ አበርክቶ ሰጥቷል። ፅሑፎቹ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ጥናቶች የተሠሩባቸው አሁንም ይበልጥ ሊጠኑ የሚገባቸው ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው። ዲያቆን ዳንኤል በፅሑፎቹ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፍልስፍናዎችን፣ ጥበባትን፣ ታሪክን፣ ሀይማኖትን፣ ባህልን፣ ሥነ ጽሁፍን ፍንትው አድርጎ በማሳየት የራሱን አሻራ ያኖረ ነው። አበርክቶውም ትልቅ ነው።
እርሱ በፅሑፍ ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ሰው በመሆኑ ትውልድ በማነፅ፣ ሥነ-ምግባርን በማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያን በመመርመርና በመግለጥ፣ ማኅበራዊ ኂስ በጥበብ በመስጠት፣ ያነበባቸውን መፅሀፎች ወይም ያካበተውን ዕውቀት ጥበባዊ ስልት በተላበሰ ምጡቅ መንገድ በማቅረብ ይታወቃል።
የራሱን አሳታሚ ድርጅትና የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅትን በመመሥረትና በመምራት ለእውቀት እና እውቅና መስፋፋት ዋና ሚና ተጫውቷል።
በመንግሥት ኃላፊነቱም ቀድሞ ሲከውን የነበረውን ተግባር በላቀ ሀገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ እንደመሆኑ መጠንም ተቋማትን በመመሥረትና በማጠናከር ሚናው ትልቅ እንደሆነ እረዳለሁ።
ዲያቆን ዳንኤል ከ30 በላይ መፅሀፍትን እንደማሳተሙ ጊዜ አጠቃቀሙ እንዴት ይሆን? የሚል ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል። እርሱ ግን ምናልባት በሰላሳ አመት የጽሁፍ ታሪኩ ከሰላሳ በላይ መጻሕፍትን እና እጅግ ብዙ መጣጥፎችን በሙበርከት ፕሮሊፊክ እና ዐቢይ ሥፍራ የሚደጠው ደራሲ እና የሃሳብ መሪ መሆኑን አስመስክሯል።ለሁሉም እንደሁኔታው ጊዜ በመመደብ ለሁላችን አርዓያ ነው።
ተመራማሪው ዳንኤል፣ ከመዛግብት ተነስቶ የሚፅፋቸውን ታሪኮች አይቻለሁ። በመካከለኛው ዘመን በአገራችን የተደረጉ ብዙ ክስተቶችን ለታሪክ ጥናት እጅግ ጠቃሚ ግብዓት እንዲሆን አድርጎ ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሰነደ ነው። ይህ ቀላል አይደለም።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሳስታውስ ብላቴን ጌታ ህሩይን ያስታውሰኛል። እርሳቸው በአንድ በኩል የመንግስት የሥራ ኃላፊነት ይዘው በአንድ በኩል ይፅፋሉ። ምርምሮችንም ያደርጉ ነበር። ዲያቆን ዳንኤል ድንቅ የፈጠራ ክህሎቱን በመጠቀም የሚያቀርባቸው ሥራዎች ከንባብ እና ነገሮች በጥልቀት ተረድቶ የሚያቀርባቸው በመሆኑ ኢትዮጵያን የማሳየት አቅም አላቸው ብዬ አምናለሁ። አበርክቶው እና ጽኑ ሰብዕናው በአጭሩ ተተርኮ የሚያበቃ አይደለም።
ረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ባዬ የባህልና ኪነ ጥበብ ሚኒስትር ዴኤታ
######
ሙሓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የማውቀው ከ20 ዓመት በፊት ነው ። የዐውደ ምሕረቱ ፈርጥ ፣የቤተክርስቲያን አጽራር መከታ ከወንድሞች ጋር ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ሲያገለግልና ለብዙዎቻችን መንፈሳዊ መሠረት ጣይ በነበረ ጊዜ አውቀዋለሁ። በሚጽፋቸው መንፈሳዊና ትዝብት አዘል ማኅበረሰባዊ ጽሑፎች ያልተማረ ,ያልተገሰጸ በነፍሱ ሀሴት ያላደረገ በዙሪያው የነበረ ማንም አልነበረም። በተለይ በማኀበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በሚያዘጋጅበት ወቅት የከተባቸው ጽሑፎች ዘመን የተሻገሩ እስካሁን ለብዙዎች መንፈሳዊ ሙላት የኾኑ ጥዑም ዘለላዎች ናቸው።
የጻፋቸው መጽሐፍት እንዲሁም በብሎጉ በዕይታ ያስቀመጣቸው ትዝብቶቹ በቤተክህነቱም በቤተመንግሥቱም ቅቡልነታቸው የበዛ ነበር።
የቀረቡት ኹሉ ግለሰባዊ ማንነቱን ሊገነዘቡለት የማይከብዳቸው ዳንኤል በዐውደ ምሕረትም ሆነ በመድረክ ራሱን ሳያካብድ ለአገርና ለቤተክርስቲያን በጥልቀት በሚያውቀው የታሪክ አረዳዱ እያገለገለ የሚገኝ ምስጉን ወንድም ነው።
ኢዮብ ስዩም

6 months ago
“ግብፆች የዓባይ ልጆች ነን ካሉ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ንጉሦች ነን”
#ethiopia | ግብፆች ከኢትዮጵያ የሚፈሰውን ወንዝ ተጠቅመው "የዓባይ ልጆች ነን" ካሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ "የዓባይ ንጉሦች ነን" ሲሉ ኡስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ።
ኡስታዝ ጀማል በሽር ይህንን ያሉት "ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጉባ ባዘጋጀው የ"ስለ ኢትዮጵያ" መድረክ ላይ ነው።
ግብፆች ስለ ዓባይ ወንዝ የሚያስተላልፉትን መልዕክት "ኪንግስ ኦፍ ዓባይ" በተሰኘ የዩቲዩብ ሚዲያ በመተርጎም የሚታወቁት ኡስታዝ ጀማል፤ ኢትዮጵያ የወንዙ መነሻ ሆና ሳለ ለዘመናት ሳትጠቀምበት መቆየቷ ግብፆች የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው በር ከፍቷል ብለዋል።
ግብፅ የዓባይ ወንዝን በመጠቀም 163 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ መያዟን የጠቀሱት ኡስታዝ ጀማል፤ ይህም በሕዳሴ ግድብ የተፈጠረው የንጋት ሐይቅ የሚይዘውን ውኃ በሦስት እጥፍ እንደሚበልጥ አስረድተዋል።
የሕዳሴ ግድብ ታላቅነቱ በኃይል ማመንጨት ዘርፍ እንጂ በውኃ የመያዝ አቅሙ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንዳልሆነ መገንዘብ እንደሚያስፈልግም አክለዋል።
ግብፆች ድርቅ ቢከሰት እንኳ ለ10 ዓመት የሚበቃ ውኃ መያዛቸውን የገለጹት ኡስታዝ ጀማል፤ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ልትቸገር ስለምትችል ያላትን ሁሉንም የውኃ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል ይኖርባታል ሲሉ አሳስበዋል።
#ጋዜጣ +

9 months ago
"ብርሃን ፈንጣቂው ዓባይ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | "ብርሃን ፈንጣቂው ዓባይ" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡
መጽሐፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በትብብር አዘጋጅቶታል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመላው ኢትዮጵያዊያን አንድነትና ትብብር ተጠናቅቆ መመረቁ ይታወሳል፡፡#fmc

በደራሲና ጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ የተጻፈ “የብሌን አንዳች” የተሰኘ መጽሃፍ ተመረቀ
#ethiopia | ትኩረቱን በኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ማህበራዊ እና ባህል ላይ ያደረገው “የብሌን አንዳች” ልብ ወለድ መጽሃፍ በ240 ገጾች ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
የመጽሃፉ ምረቃ ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት አዳራሽ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ጸሀፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ የዝና ወርቁ፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመጽሃፉ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ በትውልዶች መካከል የእውቀት ቅብብሎሽ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች መካከል አንዱ መጽሃፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የድርሰት ስራዎች ለዲፕሎማሲ ስራዎች ግብዓት መሆናቸውን የተናገሩት አምባሳደር ዲና፤ ወጣቶች ታሪካቸውን መጻፍ አለባቸው ብለዋል፡፡
መጽሀፉን እንዳነበቡት እና የሀገር በቀል እውቀት የመጽሃፉ ትኩረት መሆኑ እንዳስደሰታቸው የገለጹት ደግሞ ጸሀፊ ተውኔት አያልነህ ሙላት ናቸው፡፡
እንደ ጸሃፊ ተውኔት አያልነህ ገለጻ፣ “የኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት ከውጭ የተቀዳ በመሆኑ የሀገር በቀል እውቀታችን ጎልቶ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡
ዛሬ የመረቅነው “የብሌን አንዳች” መጽሃፍ በሀገር በቀል እውቀት እና ትምህርት ስርዓታችን ላይ ማተኮሩ ተስፋ ሰጥቶኛል” ብለዋል፡፡
“የብሌን አንዳች” በተሰኘው በዚህ መጽሃፍ ላይ ሒስ ያቀረበው ጋዜጠኛ ታምሩ ከፈለኝ እንዳለው፤ መጽሀፉ በርካታ ጠንካራ ሀሳቦች እንዳሉት ገልፀው፣ የገጸ ባህሪ አወቃቀሩ፣ ውጥነቱ እና የሀሳብ ብዝህነቱን አወድሰዋል፡፡
መጽሀፉ የሚነገር ጠንካራ ታሪክ ከመያዙ ባለፈ የአጻጻፍ ስልቱ እና የቋንቋ አጠቃቀሙን አድንቋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምክትል ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ከተማ በበኩላቸው፤ ተቋማቸው የኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ ጸሃፊያን ማህጸን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ደራሲ እና ጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ የዚህ አካል መሆኑን የገለጹት አቶ ፍቃዱ፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኢትዮጵያ ደራሲያንን ያፈራ ተቋም መሆኑንም አክለዋል፡፡
“እነ ብርሃኑ ዘሪሁን፣ ስብሀት ገብረ እግዚያብሔር፣ ጳውሎስ ኞኞ፣ በዓሉ ግርማ እና ሌሎችንም አንጋፋ ጸሃፊዎችን ያፈራው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አሁን ደግሞ ጋዜጠኛ ዋለልኝ አየለ ይህን ታሪክ ተቀላቅሏል” ብለዋል፡፡
አቶ ፍቃዱ አክለውም የጋዜጠኛ ዋለልኝ አዲስ መጽሃፍ መጻፍን አድንቀው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዳዲስ ጸሃፊያንን መደገፉን እና ማበርከቱን እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡
በሳሙኤል አባተ

11 months ago
ስፖርት ለአሸናፊ አገር በሚል መሪ ሀሳብ 21ኛው ስለኢትዮጵያ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ስፖርት ለአሸናፊ አገር" በሚል መሪ ሀሳብ 21ኛው ስለኢትዮጵያ መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ።
በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ እንዲሁም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል ና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የስፖርት አመራሮች እና ባለሞያዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የኢትዮጵያን የስፖርት ታሪካዊ ሂደቶች የሚያስቃኝ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን አራት የመወያያ ሀሳቦችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የፓናል ውይይቱም አሸናፊ ብሄራዊ ቡድንን እንዴት እንገንባ፣ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ምን ይመስላል፣ አሸናፊ ቡድን ለሀገረ መንግስት ግንባታና ለህዝቦች አንድነት ያለው ሚና እንዲሁም አሸናፊ ቡድንን በመገንባት ረገድ ያሉ ስብራቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ያተኮረ ነው።
ለሀገራችን ስፖርት ብሎም ለሀገረ መንግስት ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ውይይት የመሩት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ሲሆኑ የመወያያ ሀሳብ የሚያቀርቡት ደግሞ የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የጥናትና ምርምር ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ናቸው።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ
አሸናፊ ቡድን ለሀገረ መንግስት ግንባታና ለህዝቦች አንድነት ያለው ሚና በሚል ርዕስ ጹሁፍ አቅርበዋል።
ስፖርት ለሀገር መንግስት ግንባታ ያለውን መወጣት እንዲችል በስርዓት ሊመራ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ሚዲያው ሞያዊ ስነምግባርን በጠበቀና ለውጤት በሚጋብዝ ሁኔታ ስፖርታዊ ትችቶችን ሊያቀርቡ ይገባል ብለዋል።
ስፖርት ሰላማዊ ሲሆን ባለሀብቶችን የመሳብ ያለው በመሆኑ ፌድሬሽኖች ባለሀብቶችን በዘርፉ ለማሳተፍ መስራት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የጥናትና ምርምር ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ገልጸዋል።
በስፖርት ዘርፉ የሚታዮ ችግሮች የወረስናቸው ችግሮች በመሆናቸው ችግሩን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ ጠቁመዋል።
የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ አሸናፊ ቡድንን በመገንባት ረገድ ያሉ ስብራቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ያተኮረ ጹሁፍ አቅርበዋል።
የመልካም አስተዳደር እጦት በስፖርት ዘርፍ ውጤት እንዳይመጣ ማድረጉን ገልጸዋል።
ለዚህም አሸናፊ ቡድን ለመገንባት ከስፖርቱ ጋር የተገናኙ ፖሊሲዎች በትክክል ተግባር ላይ እንዲውል መስራት ይገባል ብለዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ የስፖርት ስብራቶችን ለማከም ምን እየተሰራ ነው በሚል የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።
ሚኒስትር ዲኤታው እንደገለፁት፣ ስፖርት ለሀገር ያለውን አበርክቶ ሰፋ አድርገን ማየት ስብራቱን ለመጠገን አየነተኛ መፍትሄ ነው።
የመጀመሪያው የስፖርቱ ስብራት ችግር የሲስተም ችግር ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፣ በተለይ ደሞ የአገልግሎት አሰጣጡ ፣ የቅንጅት ችግር እንዲሁም የአካዳሚዎች የስልጠና ማእከላት በበቂ አቅም አለመሆን ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህን ስብራቶች ለማከም ምን እየተሰራ ነው ለሚለው በመጀመሪያ የገጠመውን የእይታ ችግር ለመፍታት ሰፊ ስራ በመስራት ከለውጡ ወዲህ ትልቅ ለውጥ እንዳለ፣ስፖርቱን የልማት መሳሪያ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሆኑ ፣ገቢን ለማሳደግ ፣የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሆነ እና ከፖሊሲ ጋር የተያያዙ ስብራቶችን ለመጠገን ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በውይይቱም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተጋበዙ የስፖርት ቤተሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

Comments