Logo
Getu Temesgen
“ግብፆች የዓባይ ልጆች ነን ካሉ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ንጉሦች ነን”
#ethiopia | ግብፆች ከኢትዮጵያ የሚፈሰውን ወንዝ ተጠቅመው "የዓባይ ልጆች ነን" ካሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ "የዓባይ ንጉሦች ነን" ሲሉ ኡስታዝ ጀማል በሽር ገለጹ።

ኡስታዝ ጀማል በሽር ይህንን ያሉት "ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጉባ ባዘጋጀው የ"ስለ ኢትዮጵያ" መድረክ ላይ ነው።

ግብፆች ስለ ዓባይ ወንዝ የሚያስተላልፉትን መልዕክት "ኪንግስ ኦፍ ዓባይ" በተሰኘ የዩቲዩብ ሚዲያ በመተርጎም የሚታወቁት ኡስታዝ ጀማል፤ ኢትዮጵያ የወንዙ መነሻ ሆና ሳለ ለዘመናት ሳትጠቀምበት መቆየቷ ግብፆች የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው በር ከፍቷል ብለዋል።

ግብፅ የዓባይ ወንዝን በመጠቀም 163 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ መያዟን የጠቀሱት ኡስታዝ ጀማል፤ ይህም በሕዳሴ ግድብ የተፈጠረው የንጋት ሐይቅ የሚይዘውን ውኃ በሦስት እጥፍ እንደሚበልጥ አስረድተዋል።

የሕዳሴ ግድብ ታላቅነቱ በኃይል ማመንጨት ዘርፍ እንጂ በውኃ የመያዝ አቅሙ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንዳልሆነ መገንዘብ እንደሚያስፈልግም አክለዋል።

ግብፆች ድርቅ ቢከሰት እንኳ ለ10 ዓመት የሚበቃ ውኃ መያዛቸውን የገለጹት ኡስታዝ ጀማል፤ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ልትቸገር ስለምትችል ያላትን ሁሉንም የውኃ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል ይኖርባታል ሲሉ አሳስበዋል።
#ጋዜጣ +

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.