3 months ago
ከኒኮቲንና ትምባሆ ነጻ ቀን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በየዓመቱ ግንቦት ወር ላይ ትምባሆ መጠቀም ወይም ለትምባሆ ጭስ መጋለጥ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ሊያስገነዝቡ በሚችሉ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
በተለይም መንግሥታት፣ ህብረተሰቡና ውሳኔ ሰጪ አካላት የትምባሆን ዘርፈ ብዙ የጤና ጉዳቶችና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመገንዘብ ቁጥጥሩን እንዲያግዙ ጥሪ ይቀርብበታል።
ዘንድሮም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ34ኛ ጊዜ ‘ለኒኮቲንና ለትምባሆ ሱሰኝነት አጋላጭ የሆኑ ስልቶችን እናጋልጥ’ በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ በዋናነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የትምባሆ እና የኒኮቲን ምርቶች አጠቃቀም ድብቅና አሳሳች መረጃዎችንና የተለያዩ ስልቶችን በተመለከተ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡
በዚህም መሰረት የዚህ ዓመት የዓለም የትምባሆና ኒኮቲን ነጻ ቀን ዋና ዓላማ ከሱሰኝነት መከላከልና ወደፊት የሚኖረውን የአጫሾች ቁጥር መቀነስ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መረጃ ያመለክታል።
የትንባሆ አጠቃቀም ለበርካታ የጤና ስጋቶች አጋላጭ መሆኑን የሚገልጸው ባለሰልጣኑ፤ አፋጣኝ እና የረጅም ጊዜ ጉዳት፡ ልብ እና ደም ዝውውር፣ የመተንፈሻ አካላት እና ስኳር በሽታን ጨምሮ ከ20 በላይ ለሚሆኑ የካንሰር አይነቶች እንደሚያጋልጥ ያብራራል።
በየዓመቱ በዓልም ላይ ከ8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከትምባሆ ጋር በተያያዘ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሲሆን፤ ህጻናትን ጨምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን አጫሽ ያልሆኑ ሰዎች ሌሎች በሚያጨሱት የተነሳ ለሞትና ለበሽታ ይዳረጋሉ።
ችግሩን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የትንባሆ ኢንዱስትሪው አሳሳች ስልቶችን በመጠቀም አዳጊዎችን ዋነኛ ኢላማ አድርገው መንቀሳቀሳቸው ከፍተኛ ፈተና መሆኑ ይነገራል።
ምርቶቹ ማራኪ እንዲሆኑ እንደ ቸኮሌት፣ ቫኒላ እና ፍራፍሬ ያሉ ጣዕሞችን መጠቀማቸው እንዲሁም ሲጋራን በረቀቀ ቴክኖሎጂ (እንደ ኢ-ሲጋራ) መተካት ችግሩን ያወሳስበዋል።
በመሆኑም የኢንዱስትሪውን ተለዋዋጭ ስልቶች በማጋለጥ ችግሩን ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል።
በመሆኑም መንግሥት፣ ሚዲያ፣ ወላጆች እና ሲቪክ ማህበራት በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል።

4 months ago
ባለስልጣኑ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ከ60 በላይ የምግብ ምርቶች ላይ የጥንቃቄ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ የንግድ ማዕከላት ላይ ባደረገው ጥብቅ የድህረ-ገበያ ዳሰሳ፣ አስገዳጅ የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉና ለጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ከ60 በላይ የምግብ ምርቶችን በመለየት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳሰበ።
ባለስልጣኑ ባደረገው ፍተሻ 32 የገበታ ጨው፣ 19 የምግብ ዘይት፣ 6 የለውዝ ቅቤና 5 የማር ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የከረሜላና የህፃናት ምግቦች ተገቢው የጥራት ምልክት (CES 73)፣ የአምራች ሙሉ አድራሻና የምርት መለያ ሳይኖራቸው ለገበያ ቀርበው በመገኘታቸው፣ ሸማቾች ማንኛውንም ምርት ሲገዙ ገላጭ ጽሁፎችን፣ ክብደትንና የአገልግሎት ማብቂያ ቀናትን በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል።
seledadotio

5 months ago
ሔራል የገበታ ጨዉ ምርት ማህበረሰቡ እንዳይጠቀመው ተባለ።
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የህብረተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ እና ህገ ወጥነትን ለመከላከል በሚያደርገው የቁጥጥር ስራ ህገወጥ፣ ምንጩ ያልታወቀና ጥራት የጎደለው ሔራል የገበታ ጨዉ የተሰኘ ምርት አግኝቷል።
በቁጥጥር ወቅት የተገኝው ሔራል የገበታ ጨዉ ምርቱ በላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የአይወዲን ይዘቱ ከደረጃ በታች የሆነ ፣የምርት መያዣ ከረጢቱ ደረጃዉን ያልጠበቀ እና ታሽጎ ለገበያ የቀረበዉ ምርት የንፅህና ጉድለት እና ባዕድ ነገር ያለበት መሆኑ ተደርሶበታል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ሔራል የገበታ ጨዉ በሚል ስያሜ ከአዲስ አበባ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጣ የብቃት ማረጋገጫ እንዳወጣ በማስመሰል እና የጨዉ መያዣ ከረጢቱ ላይ ባልተገባ መልኩ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ስም በመጥቀስ ተጠቃሚዉን ማህበረሰብ በማጭበርበር በገበያ ላይ ምርቱ የተሰራጨ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡
በመሆኑም ባለስልጣኑ በገበያ ላይ የተሰራጨው የጨው ምርት የጤና ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መልዕክት እያስተላለፈ የተጠቀሰው የጨው ምርት የሚመለከተው አካል እንዲሰበስበው ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ኃላፊነት መሰረት ድርጁቱ የብቃት ማረጋገጫ ሳያወጣ በህገወጥ መንገድ ምርቱ በገበያ ላይ በማዋል ፣ ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ፣የባለስልጣን መስሪያቤቱን ስም በህገወጥ ምርት ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም እና የንፅህና ጉድለት እና ባዕድ ነገር ያለበት ምርት ለገበያ በማቅረቡ ምርቱ ከገበያ እንዲሰበሰብ ማህበረሰቡም እንዳይጠቀም እንዲሁም አምራች ድርጅቱ በህግ እንዲጠየቅ አድርጓል፡፡
ህብረተሰቡ በዚህ ጉዳይም ሆነ መሰል ህገ ወጥ ተግባራት ሲመለከት በ8864 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ባለሳልጣኑ ያሳስባል።

ዝልግልግ ባዕድ ነገር የተገኘበት የፋይን ውሃ ከገበያ እንዲሰበሰብ ታዘዘ
የአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መለያ ቁጥራቸው 620 (የሆኑ የፋይን (Fine) የታሸጉ ውሃዎች ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆናቸውን አስጠነቀቀ።
ባለስልጣኑ ባደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ፣ በምርቱ ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር መገኘቱን አረጋግጧል።
ይህ ብክለት የማምረት ሂደቱ የመልካም አመራረት ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን፣ ህዝቡ ይህን መለያ ቁጥር ያለውን ውሃ እንዳይጠቀም ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
በመሆኑም፦
አምራች ድርጅቱ ከየካቲት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን እንዳያመርትና እንዳያሰራጭ ታግዷል።
በገበያ ላይ የሚገኘው መለያ ቁጥር 620 ምርት በ5 ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ እንዲያልቅ ውሳኔ ተላልፏል።
ማህበረሰቡ ምርቱን ከመግዛት እንዲቆጠብና በጤናው ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣኑ አሳስቧል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
‘ፋይን’ (Fine) የታሸገ ውሃ ጥንቃቄ ይደረግበት ተባለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በገበያ ላይ በስፋት የሚገኘው ‘ፋይን’ (Fine) የታሸገ ውሃ ምርት ላይ የጥራት ጉድለት በመገኘቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰበ።
በተለይም የመለያ ቁጥር (Batch number) 620 የሆነው ምርት ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
እገዳው ለምን ተላለፈ?
ባለስልጣኑ ከባለድረሻ አካላት በደረሰው ጥቆማ መሰረት በፌደራል ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አማካኝነት የላብራቶሪ ምርመራ እንዲደረግ አድርጓል።
በምርመራውም የሚከተሉት ግኝቶች ተመዝግበዋል፦
* ባዕድ ነገር፦ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር (Slime/Biofilm formation) ተገኝቶበታል
* የአመራረት ጉድለት፦ የማምረት ሂደቱ የመልካም አመራረት ሥርዓትን (GMP) ያልተከተለ መሆኑ ተረጋግጧል።
* የጤና ስጋት፦ ምርቱ በውስጡ በያዘው ባዕድ ነገር ምክንያት ለሰው ልጅ ጤና እጅግ አደገኛ መሆኑ ተገልጿል።
የተወሰኑ እርምጃዎች
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአምራች ድርጅቱ ላይ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፦
* የምርት ዕገዳ፦ ድርጅቱ የችግሩን መንስኤ ለይቶ አውቆ ማስተካከያ ማድረጉ እስካልተረጋገጠ ድረስ፣ ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን ማምረትና ማሰራጨት እንዳይችል ታግዷል።
* ምርትን የመሰብሰብ ትዕዛዝ፦ በገበያ ላይ የዋለውና ችግር ያለበት Batch number 620 ምርት በአምስት ቀናት ውስጥ ከገበያ ተሰብስቦ እንዲያልቅ ተወስኗል።
ለህብረተሰቡ የቀረበ ጥሪ
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ማህበረሰቡ የተጠቀሰውን መለያ ቁጥር ያለው ውሃ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል። በተጨማሪም ይህ ምርት በገበያ ላይ ሲሸጥ ካጋጠመዎት፦
* በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቅርንጫፍ ቢሮ ጥቆማ ይስጡ።
* ወይም በነጻ የጥቆማ መስመር 8864 በመደወል ያሳውቁ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የጤና_ጥንቃቄ #ታሸገ_ውሃ #ፋይን_ውሃ #አዲስ_አበባ #የምግብና_መድኃኒት_ባለስልጣን #ethiopia #healthalert #finewater

የፋይን (Fine) የታሸጉ የውሃ ምርቶች ታገዱ!
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ በገበያ ላይ የዋሉ (Batch number 620) መለያ ቁጥር ያላቸው የፋይን (Fine) የታሸጉ የውሃ ምርቶችን ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ።
በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር የተገኘበት ሲሆን፣ ይህም ለሰው ልጅ ጤና አደገኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
አምራች ድርጅቱ ከየካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱን እንዳያመርትና ወደ ገበያ እንዳያሰራጭ የታገደ ሲሆን፣ በገበያ ላይ ያለውንም በ5 ቀናት ውስጥ እንዲሰበስብ ታዟል።
ድርጅቱ ምርቱን ሲያመርት የመልካም አመራረት ሥርዓትን ያልተከተለ መሆኑን ባለስልጣኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ማህበረሰቡ ይህንን መለያ ቁጥር (Batch 620) ያለውን ውሃ ከመጠቀም እንዲቆጠብና በገበያ ላይ ሲያገኝም በነጻ የጥቆማ መስመር 8864 ላይ ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።
ድርጅቱ የችግሩን መነሻ ለይቶ አሳውቆና ማስተካከያ ማድረጉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ምርቱን ማከፋፈል እንደማይችል ተገልጿል።

⚠️ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ፦ "ፋይን" (Fine) የታሸገ ውሃ ከገበያ ታገደ!
የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን "ፋይን" (Fine) በተሰኘው የታሸገ ውሃ ላይ ባደረገው ምርመራ፣ የምርት ቁጥር 620 ጥራትና ደህንነቱን ያልጠበቀ መሆኑን አረጋግጧል። ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በተደረገው ፍተሻ፣ በውሃው ውስጥ ዝልግልግ ያለ ባዕድ ነገር የተገኘ ሲሆን የማምረት ሂደቱም የጤና መስፈርቶችን ያልተከተለ መሆኑ ተረጋግጧል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን የምርት ቁጥር ያለውን ውሃ ለጤናው ሲባል እንዳይጠቀም ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ባለስልጣኑ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት፣ ድርጅቱ ችግሩን በቋሚነት ማስተካከሉ ተረጋግጦ በጽሁፍ ፈቃድ እስካላገኘ ድረስ ከየካቲት 24 ጀምሮ ወደ ገበያ ምርት እንዳያሰራጭ ታግዷል። በተጨማሪም በገበያ ላይ የሚገኘው የምርት ቁጥር 620 ውሃ በ5 ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ ለባለስልጣኑ ሪፖርት እንዲደረግ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ይህም እርምጃ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና የተበከለው ምርት ስርጭትን ለመግታት ያለመ ነው።
የባለስልጣኑ ዳይሬክተር እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደገለጹት፣ ህብረተሰቡ ይህንን የታገደ ምርት በገበያ ላይ ሲያገኝ በነፃ ስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል። ጤናዎን ለመጠበቅ ሲሉ የታሸጉ ውሃዎችን ሲገዙ የምርት ቁጥሩን በጥንቃቄ እንዲያዩና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከቱ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የበኩልዎን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

6 months ago
''NAN" የተሰኘው የህፃናት ወተት የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | "Nestle" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት በህፃናት ምግብ ምርቶቹ ላይ ብክለት መገኘቱን ተከትሎ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ጥንቃቄ የሚሻው የምርት ዝርዝር
ብክለት ተገኝቶባቸዋል ተብለው ለሽያጭ እንዳይቀርቡ የተከለከሉት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* የምርት መለያ፦ NAN special pro HA 0-12
* የባች ቁጥር፦ 51660742F3
* የተመረተበት ቀን፦ 15 June 2025
* የሚያበቃበት ቀን፦ 15 December 2026
* ክብደት፦ 800 ግራም
የባለስልጣኑ የቁጥጥር ስራና የሰጠው ምላሽ
የባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና የህግ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ምርቱ በይፋዊ የገበያ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ ባይገባም በተለያዩ መንገዶች ሊገባ ስለሚችል በሱፐር ማርኬቶችና በማከፋፈያዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። እስካሁን ባለው መረጃ ምርቱ በገበያ ላይ ባይገኝም ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የድርጅቱ ኃላፊነት፦ የድርጅቱ ተወካዮች ምርቱን በራሳቸው ወጪ የመሰብሰብና የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው።
* የነጋዴው ድርሻ፦ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ምርት እጁ ላይ ካለ ከመሸጥና ከማከፋፈል እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
* የህብረተሰቡ ጥንቃቄ፦ ህብረተሰቡ የተጠቀሰውን የባች ቁጥርና የምርት መለያ በማየት ጥንቃቄ እንዲያደርግና ካገኘም ለባለስልጣኑ እንዲጠቁም ተጠይቋል።
ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ደረጃውን የጠበቀ ምርት ማቅረብ የአምራችና የአስመጭ ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nestle #babyfoodsafety #ethiopia #efda #healthalert #nan #የምግብደህንነት #ኢትዮጵያ

7 months ago
በህገወጥ መንገድ የዶሮ እርድ በሚያከናውኑ ላይ እርምጃ ይወሰዳል!
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፤ እየተቃረበ ያለውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በህገወጥ መንገድ የዶሮ እርድ በሚያከናውኑ እና ንጽህናው በጎደለው መልኩ አሽገው በሚሸጡ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ከማዕከል እና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል።
🛑 ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለበዓል ሸማቾች እና ነጋዴዎች!
የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለገና እና ለጥምቀት በዓል ገበያ ላይ ባደረገው የቁጥጥር ስራ ተከታዮቹን ማስጠንቀቂያዎች አስተላልፏል፡-
ለነጋዴዎች፡-
🚫 በዶሮ መሸጫ አካባቢዎች እና ንጽህናው በጎደለው ቦታ ላይ የዶሮ እርድ ማከናወን የተከለከለ ነው።
🚫 በህገወጥ መንገድ አሽጎ መሸጥ ያስቀጣል፤ እርምጃም ይወሰዳል።
ለሸማቾች (ህብረተሰቡ)፡-
✅ ግብይት ሲፈፅሙ የብቃት ማረጋገጫ ካላቸው ህጋዊ ተቋማት ብቻ ይሸምቱ።
✅ የታሸጉ ምግቦችን የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ (Expiry Date) ያረጋግጡ።
✅ ዶሮ በሚገዙበት ቦታ ላይ እርድ አያከናውኑ።
📞 ጥቆማ ለመስጠት፡
ማንኛውንም ህገወጥ አሰራር ሲመለከቱ በሚከተለው ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ይስጡ፡
📞 8864
ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከጤና ጠንቅ ይጠብቁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#addisababa #healthsafety #holidaymarket #fmb #ethiopia

9 months ago
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሲጋራ ኢንዱስትሪ ካልተሰማሩባቸው ሁለት የአፍሪካ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች ተባለ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሲጋራ ኢንዱስትሪን ተፅዕኖ ከተቋቋሙ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗም ሪፖርት አመላክቷል።
የአፍሪካ የትምባሆ ቁጥጥር ጥምረት (ATCA) የኢትዮጵያ መንግስት ማኅበረሰቡን ከሲጋራ ጉዳት ለመጠበቅ የወሰደውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች አድንቋል።
ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ አጋርነትን በመቀነስ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ከኢንዱስትሪው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግና በመንግስት ተቋማት የሚኖርን የጥቅም ግጭት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማስቀረት ተሳክቶላታል ተብሏል።
በሪፖርቱ ኢትዮጵያ የሲጋራ አምራቾች በትላልቅ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችና የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ ማድረጓ በትልቅ ስኬትነት ተነስቷል።
ኢትዮጵያ የመንግስት አካላት ከሲጋራ አምራቾች ጋር አጋርነት እንዳይፈጥሩ ከ6 አመት በፊት አዋጅ ያወጣች ሲሆን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣንም ከኢንዱስትሪው ጋር የሚኖርን አጋርነት በመከታተል ጉልህ ሚና ተወጥቷል።
በተጨማሪ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ በተጨማሪ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሲጋራ ኢንዱስትሪውን ያልተቀላቀሉበት ወይም ከሲጋራ ኢንዱስትሪ የመጣ ሰው ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያልተቀመጠበት ሀገር ናት ተብሏል።
መንግስት በብሔራዊ የትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የነበረውን ድርሻ ለጃፓን ቶባኮ ኢንተርናሽናል በመሸጥ ከኢንዱስትሪው ሙሉ ለሙሉ መውጣቱንም ሪፖርቱ አስታውሷል።
በሌሎች ሀገራት የሲጋራ አምራቾች ተጽዕኗቸውን ለማሳደግ የማኅበራዊ ኃላፊነት ላይ የሚሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ይኸው ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል።
የመረጃው ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

1 year ago
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን እውቅና አገኘ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ስራዎችን በማዘመን አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተቆጣጣሪ ተቋም ለመሆን ባደረገው ጥረት ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። ዛሬ ካሳንቺስ ኤሊሊ ሆቴል በተካሄደው ፣ ባለስልጣኑ በምግብና መድኃኒት ቁጥጥር እንዲሁም በሕክምና መሳሪያዎች ጥራት ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እውቅና ተቀብሏል።
በዚህም መሰረት የባለስልጣኑ የመድኃኒት ኢንስፔክሽንና የምግብ ላቦራቶሪ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ ሲሆን፣ በዚህ በጀት ዓመት የመድኃኒትና የሕክምና ላቦራቶሪዎች እውቅናቸውን ያደሱ ሲሆን፣ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም ለመጀመሪያ ጊዜ በISO 17020/2017 እውቅና አግኝቷል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም የመድኃኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ በISO 17025/2011 ዓ.ም የመጀመሪያውን እውቅና ማግኘቱን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በ2012 ዓ.ም. በኮንዶም ጥራት ምርመራ በአምስት መለኪያዎች በISO 17025፣ በ2022 የመድኃኒት ኢንስፔክሽን በአይሶ 17020፣ በ2023 ምግብ ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ፣ እንዲሁም በ2023 በሕክምና ጓንት ጥራት ምርመራ እውቅና ማግኘቱንና ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል። በቅርቡም በሲሪንጅ በሁለት መለኪያዎች እና በፈጣን መመርመሪያ ኪት በአራት መለኪያዎች አዲስ ዓለም አቀፍ እውቅና ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ ISO 17025/2017 ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦንሳ ባይሳ በበኩላቸው፣ ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል እንደሆነ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ድጉማ እና ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ይህ እውቅና የኢትዮጵያን ምግብና መድኃኒት ቁጥጥርና ጥራት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን በምግብና መድኃኒት ዘርፍ 43፣ በሕክምና ግብዓት ደግሞ 5፣ በጠቅላላው በ48 ዘርፍ እውቅና መገኘቱን አስታውቀዋል። ይህ ስኬት ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተቆጣጣሪ ተቋም የመሆን ራዕዩን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ብለዋል።
በመጨረሻም፣ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲገኝ ላደረጉ የባለስልጣኑ የስራ ክፍሎች፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎትን ጨምሮ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ይህ ስኬት ባለስልጣኑ የምግብና ጤና ግብዓቶች ጥራት፣ ደህንነትና ውጤታማነት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤና ለማበልፀግ የሚደረገውን ጥረት ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

Comments