4 months ago
የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 በይፋ ተከፈተ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም "የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018" በሚል ስያሜ የንግድ ትርኢትና ባዛር በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ኤክስፖ፣ ሸማቾችና ነጋዴዎች የበዓል ግብይታቸውን በአንድ ስፍራ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በቆይታውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ይሳተፍበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ዮሐንስ መርጊያ ባንኩ በኤክስፖው ወቅት ለሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዘመናዊና የተቀናጀ የባንክ አገልግሎትን በማዕከሉ ውስጥ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
አዋሽ ባንክ በዚህ ዝግጅት ላይ "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" የተሰኘውን አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ በይፋ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም አገልግሎት ማንኛውንም ዓይነት ኩነት የሚያዘጋጁ አካላት ቲኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ መድረክ ነው።
መተግበሪያው የወረቀት ቲኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለዝግጅት አዘጋጆችና ለታዳሚዎች ዘመናዊና ምቹ አሠራርን ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ በኤክስፖው ላይ የሚታደሙ ሸማቾችም በባንኩ ዲጂታል መሠረተ ልማት በመታገዝ ፈጣን ግብይት እንዲፈጽሙ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
በተጨማሪም "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" በመጠቀም ግብይት የሚፈጽሙ ደንበኞች የመኪና ዕድል ሽልማቶችን የሚያገኙበት አጋጣሚ የተመቻቸ ከመሆኑም በላይ፣ በ"አዋሽ ብር" ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች የ5 በመቶ ተመላሽ ማበረታቻ ተዘጋጅቶላቸዋል።
የዘንድሮውን ኤክስፖ አዋሽ ባንክ ከታሜሶል ኮሚኒኬሽን ጋር በጥምረት ማዘጋጀቱን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#awashbank #awashbirr #easterexpo2018 #ethiopia #digitalbanking #eticketing #addisababa #holidaymarket

7 months ago
በህገወጥ መንገድ የዶሮ እርድ በሚያከናውኑ ላይ እርምጃ ይወሰዳል!
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፤ እየተቃረበ ያለውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በህገወጥ መንገድ የዶሮ እርድ በሚያከናውኑ እና ንጽህናው በጎደለው መልኩ አሽገው በሚሸጡ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ከማዕከል እና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል።
🛑 ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለበዓል ሸማቾች እና ነጋዴዎች!
የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለገና እና ለጥምቀት በዓል ገበያ ላይ ባደረገው የቁጥጥር ስራ ተከታዮቹን ማስጠንቀቂያዎች አስተላልፏል፡-
ለነጋዴዎች፡-
🚫 በዶሮ መሸጫ አካባቢዎች እና ንጽህናው በጎደለው ቦታ ላይ የዶሮ እርድ ማከናወን የተከለከለ ነው።
🚫 በህገወጥ መንገድ አሽጎ መሸጥ ያስቀጣል፤ እርምጃም ይወሰዳል።
ለሸማቾች (ህብረተሰቡ)፡-
✅ ግብይት ሲፈፅሙ የብቃት ማረጋገጫ ካላቸው ህጋዊ ተቋማት ብቻ ይሸምቱ።
✅ የታሸጉ ምግቦችን የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ (Expiry Date) ያረጋግጡ።
✅ ዶሮ በሚገዙበት ቦታ ላይ እርድ አያከናውኑ።
📞 ጥቆማ ለመስጠት፡
ማንኛውንም ህገወጥ አሰራር ሲመለከቱ በሚከተለው ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ይስጡ፡
📞 8864
ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከጤና ጠንቅ ይጠብቁ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#addisababa #healthsafety #holidaymarket #fmb #ethiopia

Comments