Logo
SeledaPost
ባለስልጣኑ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ከ60 በላይ የምግብ ምርቶች ላይ የጥንቃቄ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ የንግድ ማዕከላት ላይ ባደረገው ጥብቅ የድህረ-ገበያ ዳሰሳ፣ አስገዳጅ የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉና ለጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ከ60 በላይ የምግብ ምርቶችን በመለየት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳሰበ።

ባለስልጣኑ ባደረገው ፍተሻ 32 የገበታ ጨው፣ 19 የምግብ ዘይት፣ 6 የለውዝ ቅቤና 5 የማር ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የከረሜላና የህፃናት ምግቦች ተገቢው የጥራት ምልክት (CES 73)፣ የአምራች ሙሉ አድራሻና የምርት መለያ ሳይኖራቸው ለገበያ ቀርበው በመገኘታቸው፣ ሸማቾች ማንኛውንም ምርት ሲገዙ ገላጭ ጽሁፎችን፣ ክብደትንና የአገልግሎት ማብቂያ ቀናትን በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል።

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.