4 months ago
''NAN" የተሰኘው የህፃናት ወተት የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በገበያ ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | "Nestle" የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት በህፃናት ምግብ ምርቶቹ ላይ ብክለት መገኘቱን ተከትሎ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
ጥንቃቄ የሚሻው የምርት ዝርዝር
ብክለት ተገኝቶባቸዋል ተብለው ለሽያጭ እንዳይቀርቡ የተከለከሉት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* የምርት መለያ፦ NAN special pro HA 0-12
* የባች ቁጥር፦ 51660742F3
* የተመረተበት ቀን፦ 15 June 2025
* የሚያበቃበት ቀን፦ 15 December 2026
* ክብደት፦ 800 ግራም
የባለስልጣኑ የቁጥጥር ስራና የሰጠው ምላሽ
የባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና የህግ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙላቱ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ምርቱ በይፋዊ የገበያ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ ባይገባም በተለያዩ መንገዶች ሊገባ ስለሚችል በሱፐር ማርኬቶችና በማከፋፈያዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። እስካሁን ባለው መረጃ ምርቱ በገበያ ላይ ባይገኝም ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የድርጅቱ ኃላፊነት፦ የድርጅቱ ተወካዮች ምርቱን በራሳቸው ወጪ የመሰብሰብና የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው።
* የነጋዴው ድርሻ፦ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ምርት እጁ ላይ ካለ ከመሸጥና ከማከፋፈል እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
* የህብረተሰቡ ጥንቃቄ፦ ህብረተሰቡ የተጠቀሰውን የባች ቁጥርና የምርት መለያ በማየት ጥንቃቄ እንዲያደርግና ካገኘም ለባለስልጣኑ እንዲጠቁም ተጠይቋል።
ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ደረጃውን የጠበቀ ምርት ማቅረብ የአምራችና የአስመጭ ግዴታ መሆኑን አሳስበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nestle #babyfoodsafety #ethiopia #efda #healthalert #nan #የምግብደህንነት #ኢትዮጵያ

5 months ago
ለጥንቃቄ!..
የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን "Nestle" ከሚያመርታቸው የጨቅላ ህፃናትና የታዳጊ ህፃናት የምግብ ምርቶች የምርት መለያ NAN special pro HA 0-12፣ የባች ቁጥሩ 51660742F3 ፣ የተመረተበት ቀን 15 June 2025 ፣ የሚያበቃበት ቀን 15 December 2026 እና 800 ግራም ክብደት ምርት ላይ ብክለት ማጋጠሙንና ጥቅም ላይ እንዳይውሉና እንዲሰበሰብ የጥንቃቄ መልዕክት መላኩን ገልጿል።
ምርቱ በባለስልጣኑ ፈቃድ ያልተሰጠውና ጥቅም ላይ እንዲውል ያልተፈቀደለት መሆኑን ያስታወቀው ባለስልጣኑ ምርቱ በተለያዩ መንገዶች ገበያ ላይ ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ጠቅሶ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑና ህብረተሰቡ እንዳይገዛና ጥቅም ላይ እንዳያውል ጠይቋል።
ባለስልጣኑ ምርቱን ያገኘ ወይም የያዘ አካል ለይቶ በማስቀመጥ ለባለስልጣኑ እንዲያሳውቅ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ በሌሎች የድርጅቱ ምርቶች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝና ተጨማሪ መረጃ እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ኔስሊ(Nestle) የተሰኘው የህፃናት ምግብ አምራች በመላው አለም ያሉ የተወሰኑ ምርቶቹ ወደ ኩባንያው እንዲመለሱ ጠይቋል።
Nestle የተሰኘው የህፃናት ምግብ አምራች ኩባንያ "SMA, BEBA, NAN እና Alfamino" የተሰኙት የህፃናት ምግቦች ላይ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ የሚያስከትል "cersulide" ከተሰኘ ኬሚካል ጋር የተነካኩ ናቸው በማለት ምርቶቹ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።
ድርጅቱ መጀመሪያ ጥሪውን ያቀረበው በአውሮፓ በሚገኙ አንዳንድ ምርቶች ላይ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ጥሪውን ወደ አፍሪካ፣ አሜሪካና እስያ አስፍቷል።
ኩባንያው እስካሁን ከምግቦቹ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ የጤና እክል እንደሌለ ቢገልጽም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 37 ሃገራት ከህፃናት ምግቡ ጋር በተያያዘ የጤና ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
የብራዚል የጤና ሚኒስቴር መርዛማው ነገር የተገኘው በኔዘርላንድስ በተመረቱት ላይ ነው ሲል፣ የኔዘርላንድስ ተቋሙ በስዊዘርላንድ የተመረቱት ላይ ነው ብሏል።
የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር ወደ ኩባንያው እንዲመለሱ የተጠሩት ምርቶች በባለፈው ሰኔ የተመረቱና የ18 ወራት ቆይታ ያላቸው እንደሆኑ ገልጿል።
ዜናው ከተሰማ በኋላም የህፃናት የምግብ አምራቹ ኩባንያ ነስትል የአክሲዮን ዋጋ በ5.7% ቀንሷል።
Nestle ከዚህ ቀደም ወደ አፍሪካ በሚልካቸው የህፃናት ምግቦች ላይ ከመጠን በላይ ስኳር ይጨምራል ተብሎ መከሰሱ ይታወሳል።
seledadotio

Comments