ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሲጋራ ኢንዱስትሪ ካልተሰማሩባቸው ሁለት የአፍሪካ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች ተባለ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሲጋራ ኢንዱስትሪን ተፅዕኖ ከተቋቋሙ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗም ሪፖርት አመላክቷል።
የአፍሪካ የትምባሆ ቁጥጥር ጥምረት (ATCA) የኢትዮጵያ መንግስት ማኅበረሰቡን ከሲጋራ ጉዳት ለመጠበቅ የወሰደውን ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች አድንቋል።
ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ አጋርነትን በመቀነስ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ከኢንዱስትሪው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግና በመንግስት ተቋማት የሚኖርን የጥቅም ግጭት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማስቀረት ተሳክቶላታል ተብሏል።
በሪፖርቱ ኢትዮጵያ የሲጋራ አምራቾች በትላልቅ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችና የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ ማድረጓ በትልቅ ስኬትነት ተነስቷል።
ኢትዮጵያ የመንግስት አካላት ከሲጋራ አምራቾች ጋር አጋርነት እንዳይፈጥሩ ከ6 አመት በፊት አዋጅ ያወጣች ሲሆን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣንም ከኢንዱስትሪው ጋር የሚኖርን አጋርነት በመከታተል ጉልህ ሚና ተወጥቷል።
በተጨማሪ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከኡጋንዳ በተጨማሪ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሲጋራ ኢንዱስትሪውን ያልተቀላቀሉበት ወይም ከሲጋራ ኢንዱስትሪ የመጣ ሰው ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያልተቀመጠበት ሀገር ናት ተብሏል።
መንግስት በብሔራዊ የትምባሆ ኢንተርፕራይዝ የነበረውን ድርሻ ለጃፓን ቶባኮ ኢንተርናሽናል በመሸጥ ከኢንዱስትሪው ሙሉ ለሙሉ መውጣቱንም ሪፖርቱ አስታውሷል።
በሌሎች ሀገራት የሲጋራ አምራቾች ተጽዕኗቸውን ለማሳደግ የማኅበራዊ ኃላፊነት ላይ የሚሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ይኸው ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል።
የመረጃው ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
seledadotio

9 months ago