የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን እውቅና አገኘ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ስራዎችን በማዘመን አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተቆጣጣሪ ተቋም ለመሆን ባደረገው ጥረት ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። ዛሬ ካሳንቺስ ኤሊሊ ሆቴል በተካሄደው ፣ ባለስልጣኑ በምግብና መድኃኒት ቁጥጥር እንዲሁም በሕክምና መሳሪያዎች ጥራት ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እውቅና ተቀብሏል።
በዚህም መሰረት የባለስልጣኑ የመድኃኒት ኢንስፔክሽንና የምግብ ላቦራቶሪ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ ሲሆን፣ በዚህ በጀት ዓመት የመድኃኒትና የሕክምና ላቦራቶሪዎች እውቅናቸውን ያደሱ ሲሆን፣ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም ለመጀመሪያ ጊዜ በISO 17020/2017 እውቅና አግኝቷል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም የመድኃኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ በISO 17025/2011 ዓ.ም የመጀመሪያውን እውቅና ማግኘቱን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በ2012 ዓ.ም. በኮንዶም ጥራት ምርመራ በአምስት መለኪያዎች በISO 17025፣ በ2022 የመድኃኒት ኢንስፔክሽን በአይሶ 17020፣ በ2023 ምግብ ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ፣ እንዲሁም በ2023 በሕክምና ጓንት ጥራት ምርመራ እውቅና ማግኘቱንና ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል። በቅርቡም በሲሪንጅ በሁለት መለኪያዎች እና በፈጣን መመርመሪያ ኪት በአራት መለኪያዎች አዲስ ዓለም አቀፍ እውቅና ከዓለም አቀፍ አክሪዲቴሽን ቦርድ ISO 17025/2017 ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦንሳ ባይሳ በበኩላቸው፣ ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል እንደሆነ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ድጉማ እና ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ይህ እውቅና የኢትዮጵያን ምግብና መድኃኒት ቁጥጥርና ጥራት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን በምግብና መድኃኒት ዘርፍ 43፣ በሕክምና ግብዓት ደግሞ 5፣ በጠቅላላው በ48 ዘርፍ እውቅና መገኘቱን አስታውቀዋል። ይህ ስኬት ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ተቆጣጣሪ ተቋም የመሆን ራዕዩን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ብለዋል።
በመጨረሻም፣ ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲገኝ ላደረጉ የባለስልጣኑ የስራ ክፍሎች፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎትን ጨምሮ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ይህ ስኬት ባለስልጣኑ የምግብና ጤና ግብዓቶች ጥራት፣ ደህንነትና ውጤታማነት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤና ለማበልፀግ የሚደረገውን ጥረት ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።

1 year ago