4 days ago
የእንኳን ደስ አላችሁ እና የመልካም ምኞት መግለጫ!
*****
በአገራችን የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የመንግሥት ምሥረታን ምክንያት በማድረግ ለመላው የአገራችን ሕዝቦችና ለአዲሱ መንግሥት እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ ለሰላማዊ የፖለታካ ሂደቶች ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን፤ ህዝባችን በአስከፊ የፀጥታ ስጋትና መዋከብ ውስጥ ሆኖም ስልጣን የሚፀናው በድምፄ ብቻ ነው በሚል ቁርጠኝነት በነቂስ ወጥቶ ምርጫ በማድረግ ከምርጫ ውጪ ላሉ የስልጣን ፍላጎቶች ግልፅ መልእክቱን አስተላልፏል።
በመሆኑም በዚህ የላቀ ህዝባዊ ቁርጠኝነት በታየበት ምርጫ የተመሠረተው መንግሥት አገራችንን ወደ ተሻለ ሁለንተናዊ የዕድገት እና ሰላም የሚያሸጋግር፤ የሕዝባችንን ጥያቄዎችና እውነተኛ ፍላጎቶች የሚመልስ እንዲሆን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምኞቱን ይገልጻል።
ዛሬ ለተሾሙት የመንግሥት አመራሮች በሙሉ የተጣለባችሁን ታሪካዊና አገራዊ ኃላፊነት በታማኝነት፣ በፍትሐዊነትና በትጋት በመወጣት አገራችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የምታደርጉት ጉዞ የስኬትና የድል እንዲሆንላችሁ አብን እየተመኘ፤ በሰባተኛ ዙር አንደኛ መደበኛ መስራች ጉባኤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሜ የተመረጡትን ክቡር ዐብይ አሕመድን (ዶ.ር) ፓርቲያችን አብን እንኳን ደስ አለዎት ማለት ይወዳል።
አገራችን ያለችበትን ሁለንተናዊ ነባራዊ ሁኔታ፣ ያጋጠሙንን አገራዊና ቀጣናዊ ተፎካካሪ ሁኔታዎች እንዲሁም የሕዝባችንን የልማትና የፍትህ ጥያቄዎች በተገቢው በመረዳት አገራችንን ወደ ተሻለ የዕድገትና የሰላም ምዕራፍ ይመራሉ ብለን እናምናለን። በመሆኑም ድርጅታችን አብን፤ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት እንዲሁም የሕዝባችንን የኑሮ ውድነት የሚያቃልሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ለመተግበር በሚወሰዱ ሀገራዊ እርምጃወች በትብብር ለመሥራት ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።
በመጨረሻ ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገራዊ ጥቅም፣ አንድነትና ህልውና በሚጠይቀው ቦታ ሁሉ ጽኑ አጋርነታችንን እየገለጽን፣ ፍትሕና እውነት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ድምፅ ሆነን መቆማችንን እንቀጥላለን። በድጋሜ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና ለአዲሱ መንግስታቸው ስኬትን እንመኛለን።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
መስከረም 25/2019 ዓ.ም

11 days ago
የመደመር መንግሥት ታላቅ ራእይ፦ ጠንካራ ተቋማትና የማትበገር ኢትዮጵያን መገንባት
*********************
ሀገር መገንባት በጥቂት ዓመታት የሚጠናቀቅ ስራ ሳይሆን ትውልዶች የሚፈፅሙት ታላቅ ጉዞ ነው፤ ኢትዮጵያም ዛሬ በዚህ የዘመናት የታሪክ ምእራፍ ውስጥ ትገኛለች።
የሀገራችን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስኑ ወቅታዊ የፖለቲካ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎችን ወደ ተቋማዊ መፍትሄ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት የሀገረ መንግስት ግንባታን በጠንካራ መሰረት ላይ የመጣል አስፈላጊነትን አጉልቶ አሳይቷል።
የመደመር መንግስትም ጊዜያዊ ስኬትን ብቻ ሳይሆን ለዘመናት የሚፀና ሀገረ መንግስት የመገንባት ራእይ ይዞ ተነስቷል።
ይህ የሀገረ መንግስት ግንባታ ራእይ በሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ መልህቁን የጣለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ምሰሶ የፀና ሀገረ መንግስት ግንባታ ሲሆን በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎች ባሉበት ሁኔታ እንኳ ዜጎቿ በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን የሰጡበትን ነፃ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ጠቅላላ ምርጫ በስኬት አጠናቃለች።
ምርጫ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማጠናከሪያ በመሆኑ ይህ እርምጃ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ጠንካራ ሀገር የሚገነባው ደግሞ በጠንካራ ተቋማት ብቻ በመሆኑ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የፍትህና የፀጥታ ተቋማት እንደ አዲስ ተደራጅተው በስኬት ጎዳና ላይ ይገኛሉ።
ሁለተኛው ምሰሶ የማትበገር ሀገር መገንባት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ስርአቶችና መንግስታት ቢያልፉም ተቋማት ሲጠነክሩ ሀገር መሻገሯ አይቀሬ ነው። በመሆኑም ዛሬ የሚገነቡት ተቋማትና ሀሳቦች ሀገርን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሸጋግሩ ናቸው።
ሶስተኛው ምሰሶ የብልፅግና ተምሳሌትነት ሲሆን የትናንትናውን ታሪካዊ ቅርስ በማደስ የዛሬውን ትውልድ በማነቃቃትና ነገንም በማሻገር የትውልድ ተከታታይነት በተግባር እየተረጋገጠ ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ በጥልቅ የተሳሰረ ማንነት የሚያጋሩ መሆናቸው ዋናው መሰረት ነው አንዳንዶች ልዩነትን ለመዝራት ቢሞክሩም አብሮነቱ ከጥንት ጀምሮ የነበረና የጋራ ሀገር የመገንባት ፍላጎት ውጤት ነው።
በስኬት የጠናቀቀዉም ሀገራዊ የምክክር ሂደትም የዘመናት የታሪክ ስብራቶችን በመጠገን ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚናን ተጫዉቷል።
ይህ ያልተቋረጠ ርብርብ የሚያስፈልገው የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ከተራ የአስተዳደር መዋቅር ማጠናከር ባለፈ በመንግስትና በዜጎች መካከል አዲስ "ማህበራዊ ውል" የሚፈጥር ነው።
በዚህ ማእቀፍ ውስጥ መንግስት የህግ የበላይነትን ፍትህ የሰላምንና የልማት እድሎችን የማረጋገጥ ሀላፊነት ሲወስድ ዜጎች ደግሞ ተመልካች ሳይሆኑ ባለቤት በመሆን ህግን በማክበርና የሀገራዊ ጥቅምን በማስቀደም ይሳተፋሉ።
ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ከዚህ የጋራ ባለቤትነት ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ በመሆናቸው አዲሱ ማህበራዊ ውል የዛሬን ፈተናዎች ከመመለስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገር ተቋማዊና ማህበራዊ መሰረት የሚጥል ይሆናል።
በብሌን ደምበሎ

21 days ago
የመደመር አንቀጽ
በእጃችን ላይ ያሉ የጎብኚ መዳረሻዎችን በሚገባ አገልግሎት ላይ ማዋልና ከዚህም ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ጥቅም ሁሉ መሰብሰብ ተገቢና በቀጣይ ለምንጓዘው አቅጣጫ ትልቅ ግብዓት የሚሆን ነው።
ከዚህ አንጻርም ብዙዎችን በፍጥነት ወደ ሥራ አስገብተናል፤ ትሩፋቶችንም እያጣጣምን እንገኛለን።
በእነዚህ ጥረቶች ምክንያት ሀገራችንን የሚጎበኙ የውስጥም ይሁን የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው። ይሁንና ዘርፉ ከፍተኛ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።
ሀገራችን ከቱሪዝም ሊገኝ የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መለኪያዎች (Strategies) ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።"
የመደመር መንግስት
ገፅ 272-273
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #yemedemermengist #መደመር #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ

1 month ago
የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር።
ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሮጀክቶች ጉብኝት እና ምረቃ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል። አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችን እና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል።
ማኅበራዊ ጉዳይ፦
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።
#pmoethiopia
#ethiopiadelivers

ከግለሰቦች በላይ - የክብር ማኅተም የሆነው አትሌቲክሳችን እና የተፈተነው ንግሥናችን
********************
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ከግለሰቦች ፍላጎት እና ከወቅታዊ የሥልጣን ውዝግብ በላይ የሆነ፣ የሀገር ፍቅር እና የማንነታችን መገለጫ የሆነ ታላቅ ሀገራዊ ሀብት ነው።
በዓለም አደባባይ የአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቃችን ከፍ ብሎ ሲውለበለብ፣ ከድል በላይ የሆነ ስሜት ይፈጠራል። የብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የደስታ፣ የጽናት እና የጋራ ኅብረት ምንጭ ሆኖ ኖሯል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ በባዶ እግራቸው ዓለምን ካስደመሙት የጀግንነት ገድሎች ጀምሮ እስከ አሁኖቹ ወጣት ባለታሪኮች ድረስ በደም፣ በላብና በጥቁር ሕዝቦች የነጻነት አርማ ተምሳሌትነት የተገነባ የክብር ማኅተም ነው።
አትሌቶቻችን የሚሮጡት ለግል ዝና ብቻ ሳይሆን፣ የሕዝብን ተስፋ እና ሀገራዊ ክብር በልቦቻቸው ተሸክመው ነው።
ይህ ታላቅ የድል ታሪክ ሕዝቡን የዘር፣ የሃይማኖት እና የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበው መላውን ኢትዮጵያዊ በአንድ ልብ የሚያቆም የኅብረታችን ጠንካራ ምሶሶ ነው።
ሆኖም ስፖርቱ አሁን ካለበት የአመራር ውጥረት እና የውጤት ውጣ ውረድ ወጥቶ ዘላቂ ተቋም ይሆን ዘንድ የሁሉም አትሌቲክስ ወዳድ የበሰለ ውሳኔ እና ጥረት ያስፈልገዋል።
አትሌቲክሱ ከግለሰባዊ ሽኩቻ በላይ በመሆኑ ሕግን፣ ተቋማዊ አሠራርን እና የሙያ የበላይነትን ማስቀደም ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው።
የፌዴሬሽኑ አሠራር በግልጽነት፣ በተጠያቂነት እና በግልጽ የሥራ ድርሻ ክፍፍል ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። ደንብ እና መመሪያ በማክበር፣ የሥራ ድርሻን በግልጽ በመለየት እና ውሳኔዎችን በሙያዊ መርሕ በመወሰን ተቋሙን ከግለሰባዊ ተጽዕኖ መጠበቅ ይገባል።
ውስጣዊ አለመግባባቶችን በሰከነ ውይይት በመፍታት የአትሌቶቻችንን ሥነ-ልቦና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል።
የአትሌቲክሱ ዘላቂ ስኬት የሚለካው በዛሬ ሜዳሊያ ብቻ አይደለም። የነገ አትሌቶችን በማፍራት፣ የሥልጠና ማዕከላትን በማጠናከር፣ የአሠልጣኞችን እና የቴክኒክ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ እንዲሁም ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ከስፖርቱ ጋር በማቀናጀት ነው።
ማንኛውም በስፖርቱ ላይ የሚደረግ ሪፎርም የግለሰቦችን የበላይነት ሳይሆን፣ የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ጥቅም፣ የፋይናንስ አጠቃቀም፣ የአትሌቶች መረጣ፣ የዓለም አቀፍ ጉዞዎች እና የውድድር ዝግጅቶች በግልጽ መሥፈርት እና በሙያዊ ጥናት እንዲመሩ ሊያግዝ መሆን አለበት።
ይህ የሚጠቅመው ተቋሙን ብቻ ሳይሆን፣ የአትሌቶችን መብት፣ ዕድል እና የወደፊት ሕልም እንዲሁም ስፖርቱንም ነው።
በተለይ የወጣቶች ተሰጥኦ ልየታ እና ልማት ላይ የሚደረገው ሥራ የአትሌቲክሱ የነገ መሠረት ነው። የዛሬን ሻምፒዮኖች ለማክበር ብቻ ሳይሆን፣ የነገ ሻምፒዮኖችን ለማፍራት የሚችል ሥርዓት መገንባት ይገባል።
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ያላትን የንግሥና ዙፋንን አጠናክራ እንድትቀጥል፤ የስፖርቱ አስተዳደር በይቅርታ፣ በአንድነት እና በበሰለ አመራር ሊመራ ይገባል። የዛሬ ውሳኔ የነገን አትሌቲክስ ስለሚወስን፣ የግል ሽኩቻን በማስቀረት የትውልድን አደራ ማስቀደም ግድ ይላል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የትናንት ትውልድ በባዶ እግሩ የገነባው፣ የዛሬው ትውልድ የተረከበው እና የነገው ትውልድ የሚወርሰው ሀገራዊ አደራ ነው።
ስፖርቱን የሚመሩ ሰዎች ይቀየራሉ፤ አመራሮች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ግን ከሁሉም በላይ ሆኖ መቀጠል አለበት።
የአትሌቲክሱ ጉዳይ የግለሰቦች ወይም የተቋም ብቻ ሳይሆን የሀገር ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አትሌቲክሳችን ስፖርት ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ክብር፣ የሕዝቧ አንድነት እና የትውልዶች ተስፋም ጭምር ነው።
በአዲስ የሺዋስ
#athletics #athlete #ethiopia #ethiopianathletics #sportleadership #sports #ebc

Sponsored by
Surafel
2 months ago
በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት የኢትዮጵያን የአባይ ወንዝ ፍትሐዊ የመጠቀም መብት የሚያስከብርና የካሳ ጥያቄ የሚያነሳ ስትራቴጂካዊ ጥናት ተዘጋጀ
#ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ፍትሐዊና ምክንያታዊ የመጠቀም መብት በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ለማስከበር እንዲሁም በዚሁ ሰበብ ለደረሱባት ጉዳቶች የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል ባለ 160 ገጽ አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጥናት ተዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ እንደሆነ ተገለጸ።
በኢንጂነር አልጣህ ረጋስ ታቦር የቀረበው ይህ አጠቃላይ ጥናት በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአምስት ዓመት ሕጋዊ ጥበቃ የተደረገለት ሲሆን በማመልከቻ ቁጥር LTR/W/11627/2018 እና በምዝገባ ቁጥር 1/2/5/00122 ይፋዊ ዕውቅና ተሰጥቶታል።
ይህ ሰነድ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የሉዓላዊነት መብት በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በዲፕሎማሲ፣ በቴክኒክ ማስረጃዎችና በሰላማዊ የሕግ ተቋማት አማካኝነት እንዴት ማስጠበቅ እንደሚቻል በጥልቀት ያብራራል።
ጥናቱ ሀገራዊ ጥቅምን ማዕከል በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን፣ ቀጣይነት ያለው ትብብርንና የትውልድን መብት ለማረጋገጥ እንዲሁም በሀገሪቱ ላይ ለደረሱ ሁሉን አቀፍ ጉዳቶች የካሳ ጥያቄ ማዕቀፍን አዘጋጅቶ ያቀርባል።
ሰነዱ የሕግ መሠረቶች፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ ስትራቴጂካዊ የውሳኔ ሃሳቦች እና አባሪዎች የተሰኙ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስትከተለው የቆየችውን ውጤት አልባ የድርድር መንገድ በመቀየር መብቷን በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ፊት በጽናት እንድትጠይቅ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ ነው።
የጥናቱ አዘጋጅ ኢንጂነር አልጣህ ረጋስ ታቦር በ1995 ዓ.ም ከአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመስኖ ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት በላይ በውሃ ምህንድስና እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በሙያቸው አገልግለዋል።
በቀድሞው የውሃ ስራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ የውሃ ፕሮጀክቶች ላይ እስከ 2002 ዓ.ም የሰሩ ሲሆን ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት በግል የምህንድስና አማካሪነት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#nile #abbay #ethiopianrights #icj #internationallaw #waterengineering #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ወደ የመጨረሻ የውሳኔ መድረክ የሚያልፉ የማጣሪያ ምክረ ሀሳቦች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመጨረሻውን የውሳኔ መድረክ ለመጀመር መሠረት የሚጥሉ የማጣሪያ ምክረ ሀሳቦች ለተመካካሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በተለያዩ የውይይትና የማጣሪያ ሂደቶች ካለፈ በኋላ፣ በስልታዊ ቡድኖች የተጣሩና የተስማሙባቸውን ሀሳቦች ወደ ዋናው የውሳኔ መድረክ ተሸጋግረዋል።
በሂደቱ ወደ 500 የሚጠጉ ተመካካሪዎች በ250 የስልታዊ ቡድኖች ተደራጅተው፣ በስምንቱ ዋና ዋና አጀንዳዎችና በንዑሳን አጀንዳዎች ላይ የተመረጡ ሀሳቦችን በዝርዝር በመመካከር ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች በፊርማ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት የቃለ ጉባኤ ያዦችና አመካካሪዎች እነዚህን በፊርማ የተረጋገጡ ሀሳቦች ለተመካካሪዎች በግልጽ ሁኔታ ቀርበዋል። ወደ የመጨረሻው የውሳኔ መድረክ የሚያልፉትን ጉዳዮችም አብራርተዋል።
ተመካካሪዎች በበኩላቸው የተመረጡት ሀሳቦች በትክክል በቃለ ጉባኤ መዝገብ መካተታቸውና ለውሳኔ መድረኩ መቅረባቸው ግልጽነትን እንዲሁም የሂደቱን ተዓማኒነት እንደሚያጠናክር አንስተዋል።
በውይይቱ ወቅት በዋና አጀንዳዎች ላይ ተጨማሪ ማሻሻያ፣ ማስተካከያ ወይም ያልተካተቱ ሀሳቦች ካሉ በዚህ ደረጃ እንዲቀርቡ ዕድል የሰጠ ሲሆን፤ ይህም ወደ የመጨረሻው የውሳኔ መድረክ የሚቀርቡ ሀሳቦች ሁሉን አቀፍ እንዲሆኑ እና ሰፊ ስምምነት እንዲያገኙ አግዟል።
ተመካካሪዎች፣ ከግላዊ አመለካከት ይልቅ ሀገራዊ ጥቅምን፣ ሀገራዊ መግባባትንና ህብረ ብሔራዊነትን ያስቀደመ ውይይት መካሄዱን ገልጸው፤ የመድረኩ ሂደት ከ"እኔ" ወደ "እኛ" የሚያሸጋግር የመግባባት ባህልን ያጠናከረ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የቀረቡት ሀሳቦች በሙሉ በቃለ ጉባኤ መያዛቸው፣ መነበባቸው እና በአመካካሪዎች ማብራሪያ መሰጠቱ የሂደቱን ግልጽነትና አሳታፊነት ያጠናከረ እንደሆነ ተመላክቷል።
በዮናስ ጌትነት

3 months ago
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚመራባቸው መርሖች
**************
✅ በአወያይ የመናገር ዕድል ሳይሰጥ ያለመናገር
✅ ተመካካሪዎች አድማጭና ሃሳብ አመንጪ ሆኖ መሳተፍ
✅ ሀሳብን ግልጽና አጭር አድርጎ ማቅረብ
✅ የሀሳብ ልዩነትን ማክበር
✅ የሌላውን ሀሳብ ለመረዳት መጣር
✅ ሀገራዊ መግባባት ላይ መድረስን ከግምት ማስገባት
✅ አሉታዊ ከሆኑ ትችቶችና ፍረጃዎች መቆጠብ
✅ አወያዮች ተመካካሪዎች ለምክክሩ የመገኘታቸውን አስፈላጊነት ዕውቅና መስጠት፣ መደማመጥና መከባበርን መሠረት ማድረግ
✅ በምክክሩ ወቅት ሀገራዊ ጥቅምን ማስቀደም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በጠቅላላ ምርጫው በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክር ቤት ወንበር ማሸነፋቸው የዴሞክራሲ ምህዳሩን መስፋት ያረጋገጠ ነው፡- የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
*******************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስኬት የተካሄደውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክር ቤት ወንበሮችን ማሸነፋቸው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየሰፋ መመጣቱን በተግባር ያሳየ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ።
ይህ ስኬት በክልል እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻለ የሀሳብ ብዝኃነት እንዲኖርና ጠንካራ የመንግሥት ተቋማትን የመገንባት ሂደትን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል።
በተገለጸው የምርጫ ውጤት መሠረት ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን ሲያገኝ፤ ኢዜማ 13፣ አብን 6፣ ነእፓ 3፣ መድረክ 3፣ አዴኃን 3፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 2 ወንበሮችን ያሸነፉ ሲሆን ሌሉች 10 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ የምክር ቤት ወንበር አግኝተዋል።
ለክልል ምክር ቤት በተደረገው ውድድርም ኢዜማ 73፣ ነእፓ 35፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 34፣ ኦብነግ 20፣ ጉህዴን 14፣ መድረክ 11፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 6፣ ሕዳሴ ፓርቲ 5 እና ቤህነን 5 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል።
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ነቢሃ መሀመድ ምርጫው የሕዝብ ድምፅ መንግሥት ለመመስረት ብቸኛው መንገድ መሆኑንና መንግሥት የሚመሰረተው በኃይል ሳይሆን በሐሳብ ብቻ መሆኑን ያስተማረ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አያይዘውም ፓርቲያቸው በሀገራዊ ጥቅም፣ በሉዓላዊነት፣ በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና በምግብ ዋስትና ዙሪያ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል የወሎ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ነጻነት ጣሰው ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እስከ ታችኛው መዋቅር ተቀራርቦ መሥራት ሀገር ለማሻገር ቁልፍ ሚና እንዳለው በመጥቀስ፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታና ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት ፓርቲያቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን በጥናት ለይቶ በማቅረብ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
#ethiopiaelections #democracy #politicalpluralism #nationalunity #ethiopianbroadcastingcorporation

4 months ago
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ...
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ታሪክ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በርካታ አመርቂ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በተለይም በፈታኝ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋ ሚዛናዊ፣ አጋርን ማብዛት ላይ ያተኮረና ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ተራማጅ የውጭ ግንኙነት ፍልስፍና በመከተሏ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ቅቡልነት እና ተደማጭነት ከፍ አድርጋለች።
በዚህም በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፎ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ ችላለች።
ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረትን ሙሉ አባል ሆና መቀላቀሏ በታሪኳ ያገኘችው ታላቅ የዲፕሎማሲ ስኬት እና የታሪክ አሻራ ነው።ይህም በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ መስክ ያላትን ሚና ከፍ አድርጎታል።
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2026 ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ መመደቧ በአህጉሪቱ ሰላም ማስከበር ላይ ያላትን ቁልፍ ሚና ያሳየ የዲፕሎማሲ ስኬቷ ነው።
በሁለትዮሽ ግንኙነትና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን ትስስር አጠናክራለች።
በዚህም በቅርቡ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት በኢኮኖሚ፣ በደህንነት እና በቀጣናዊ ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ከሕንድ ጋር ያላት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያደገ ሲሆን÷ ከገልፍ ሀገራት ጋርም በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢንቨስትመንት ዙሪያ ሰፊ ትብብሮችን መፍጠር ችላለች።
በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር፣ የአንካራው ስምምነት አማካኝነት የተመዘገቡት ስኬቶች በቀጣናው መረጋጋትን የፈጠሩና የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከበሩ ነበሩ።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸው የልማት ስኬቶች ለውጭ ዲፕሎማሲዋ ጥንካሬ እንደጀርባ አጥንት አገልግለዋል።
ኢትዮጵያ ለስንዴ ምርትና ለምግብ ዋስትና የሰጠችው ትኩረት ዓለም አቀፍ አድናቆትን ከማስገኘት ባሻገር ከጣሊያን መንግሥት ጋር በመተባበር 2ኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔን በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ በር ከፍቷል።
ዓለም አቀፍ አጀንዳ መሆን የቻለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርም ወደ ሀገር ውስጥ የሚመጡ የዓለም መሪዎችና ዲፕሎማቶች በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሏል።
ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እና መሰል ታላላቅ መድረኮችን በስኬት ማስተናገድ መቻሏ ኢትዮጵያን ብሎም አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከልነት ይበልጥ ያጠናከረ ነው።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም ኢትዮጵያ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችላለች፤ በዚህም ባለፉት አጭር ጊዜያት ብቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ትውልድ ቀያቸው በሰላም መመለስ ተችሏል።
በአጠቃላይ መንግሥት የተከተለው ዘመናዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን አስከብራ እንድትቀጥል እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት ተደማጭነት ይበልጥ እንዲጎለብት አስችሏል።
በሶስና አለማየሁ

ወደ ዋናው ምክክር - የሀገርን ምሶሶ በጋራ የመጠገን ታሪካዊ ጥሪ
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
በሀገራችን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ሂደት በታሪካችን፣ በማንነታችን እና በፖለቲካ አመለካከታችን ዙሪያ ለዘመናት የቆዩትን ስር የሰደዱ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ልዩነቶችን በሰለጠነ ውይይት ለመፍታት የሚደረግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ጥረት ነው።
ይህ ሂደት በተለይ በኢትዮጵያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዘላቂ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ለዓመታት ሀገርን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ሲያስከፍል የቆየውን እና ሀገራዊ አንድነታችንን ሲፈታተን የኖረውን "የእኔን ሃሳብ ካልተቀበላችሁ" የሚለውን የጥፋት የዜሮ ድምር አስተሳሰብ እና የጥርጣሬ ድባብ በመስበር፣ በጠመንጃ ሳይሆን በሀሳብ የበላይነት፣ በጠላትነት ሳይሆን በውይይት፣ እንዲሁም በሴራ ሳይሆን በግልጽነት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት የተከፈተ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ የፈረሰውን ለመጠገን፣ የላላውን ለማጥበቅ፣ የቆዩ የፖለቲካ ቁስሎችን ለመፈወስና አዲስ የጋራ መጻኢ ዕድልን በጥንካሬ ለመንደፍ የቀረበ ወርቃማ እና ወደር የሌለው ሀገራዊ ዕድል ነው።
የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ እንዲሁም ልዩ ትኩረት በመስጠት የሴቶችና የወጣቶችን ድምፅ በማካተት ከመላው ሀገራችን በተሰበሰቡት አጀንዳዎች ላይ ከመጪዉ ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዋናዉ ምክክር ለመጀመር ተዘጋጅቷል።
ይህ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ያሳተፈ ብሄራዊ መድረክ የምክክሩ እውነተኛ ባለቤትና መሪ ራሱ ህዝቡ እንዲሆን የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ መሰረታዊ የልዩነት ነጥቦች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙና ዉይይት እንዲደረገባቸዉ ያስችላል።
በጥንቃቄ የተለዩት አጀንዳዎች የምክክሩን ዕድሜ፣ አቅጣጫ እና የመጨረሻ ውጤት የሚወስኑ ስለሆነ ዋነኛ ትኩረታቸዉ መሠረታዊ የልዩነት ነጥቦች ላይ ብቻ ማድረግ ምክክሩን ውጤታማ ያደርገዋል።
የምክክሩ መሳካት በዋና ዋና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መግባባት ላይ ለመድረስ፣ ህዝቡ በተለያዩ መንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማት ላይ ያለው እምነት እንዲጠነክር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲጠቆሙ እና ከዚህ ቀደም የነበሩ ቁስላችንን በራሳችን ውስጣዊ አቅምና መድኃኒት በመፈወስ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጽናት ለመግታት ያስችላል።
በጠረጴዛ ዙሪያ መቀራረብ እና መወያየት የሀገርን ሉዓላዊነት የማጽናት እና መረጋጋትን የማጠናከር የህልውና ጉዳይ ነው።
በዚህ ታላቅ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የህብረተሰቡ አይንና ጆሮ የሆኑት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሃይማኖት እና የጦር ልሂቃን ያላቸውን ከፍተኛ ተሰሚነት፣ ተፅዕኖና እውቀት ተጠቅመው ህዝቡን በማንቃት ሂደቱን በቅንነት እና በዕውቀት የመምራትና የማገዝ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው።
በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ በሩን ክፍት አድርጎ ሐሳብን ሲቀበል ቆይቶ ወደ መጨረሻው እና ወሳኙ ምዕራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ፣ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ምርጫ ሳይሆን የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።
የተበታተነ ሀሳብና ልዩነት ሀገርን ስለማያቆም እና ለጋራ መረጋጋት ስለማይበጅ፣ ሁላችንም እንደየድርሻችን ለብሔራዊ ጥቅማችን በጋራ ልንቆም እና ታሪክ ልንሰራ ይገባል።
በአንድነት መምከር፣ በልዩነት መከባበር፣ ለጋራ ውጤት በቅንነት መስራት እና ሀገራዊ ጥቅምን ማስቀደም የዘመኑ ታሪካዊ ጥሪ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ እውነተኛ ምክክር፣ ይቅርታ እና መግባባት ትጸና ዘንድ ሁላችንም ለስኬታማነቱ በቁርጠኝነት ልንተጋ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምክክር #ሐምሌ8 #ኢትዮጵያ #nationaldialogueethiopia

5 months ago
የመደመር አንቀጽ
በእጃችን ላይ ያሉ የጎብኚ መዳረሻዎችን በሚገባ አገልግሎት ላይ ማዋልና ከዚህም ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ጥቅም ሁሉ መሰብሰብ ተገቢና በቀጣይ ለምንጓዘው አቅጣጫ ትልቅ ግብዓት የሚሆን ነው። ከዚህ አንጻርም ብዙዎችን በፍጥነት ወደ ሥራ አስገብተናል፤ ትሩፋቶችንም እያጣጣምን እንገኛለን።
በእነዚህ ጥረቶች ምክንያት ሀገራችንን የሚጎበኙ የውስጥም ይሁን የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው። ይሁንና ዘርፉ ከፍተኛ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።
ሀገራችን ከቱሪዝም ሊገኝ የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መለኪያዎች (Strategies) ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።"
የመደመር መንግስት
ገፅ 272-273
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #yemedemermengist #መደመር #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲና የፕሮግራም ክርክር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ
#fastmereja I በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጥናት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት፣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ያተኮረ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲና የፕሮግራም ክርክር ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ። በመድረኩ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በልማት ፖሊሲዎች፣ በሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎቶች ዙሪያ የየራሳቸውን አማራጭ ሃሳቦች አቅርበዋል።
በዩኒቨርሲቲው የፕሬዚዳንት ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ወቅት መድረኩ ሙሉ በሙሉ አካዳሚያዊ፣ ገለልተኛና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንደሚመራ አረጋግጠዋል። ዜጎች ሉዓላዊ ፍቃዳቸውን ተጠቅመው መፃኢ እድላቸውን የሚወስኑበት ወቅት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስራት፣ ታዳሚው የቀረቡትን ሃሳቦች በሂሳዊ መንገድ እንዲመረምር አሳስበዋል።
የስትራቴጂና ወቅታዊ ጉዳዮች ጥናት ክፍል አስተባባሪ አቶ ሀቢብ ሰይድ በበኩላቸው፣ ዳይሬክቶሬቱ ሀገራዊ ጉዳዮችን በገለልተኝነት የመመርመርና ስትራቴጂካዊ አማራጮችን የማመንጨት ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት "የውይይት ባህል ለሀገር ግንባታ" እና "የውክልና ዲሞክራሲና የምርጫ ስርዓት" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራዊ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በአቶ ጀምበሩ አረጋ አወያይነት በተመራው የፓርቲዎች ክርክር፣ ተወካዮቹ ከታዳሚዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩም መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የሲቪክ ማህበራትና የሚዲያ አካላት በተገኙበት በሰላም ተጠናቋል።

11 months ago
ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ ፣የዜጎች ሚና ከብሔራዊ ጥቅም ዓይን
#ethiopia | አሁንም መነሻችን በተለይ በእኔ ዘመን ላሉ የትውልዱ አካል እና በትናንትና ሀቲት ላይ ሳይኖሩ ለአገራቸው ቀና ሀሳብ ላላቸው በውስጣቸው የአገር ፍቅር ንዳድ ሌት ከቀን ለሚሳስባቸው ለእኔ ዘመን ትውልድ አካል(As a member of this generation)ይህ እይታዬ (perspective )እንዲሆንልልኝ እመኛለሁ ።
ትናንት የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲገነባ በቀንነት ልማትን እና እድገት ሲደገፉ የነበሩ ዜጎች ይደርስባቸው የነበረው ያልተገባ አስተያየት ቆም ብሎ በማስተዋል ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ አባው ሳይረፍድብን በክቡር የኢ.ፊ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሰሞኑ በህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሀሳብ በመመልከት እንደ ዘመኑ የትውልድ አካል በትንሹ ከቀሰምኩት (Global studies and international relations ) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት አኳያ የግል ምልከታዬን አካፍላለሁ ።
የኢትዮጵያ ወደብ አልባነት (Landlocked status) ለኢኮኖሚያዊና ለፀጥታ ችግሮች ዋነኛ መንስዔ መሆኑን በማመን፣ቀይ ባህርን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው። ይህን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ መሻት ለማሳካት ዜጎች የሚከተሉትን ሚናዎች መጫወት ይገባቸዋል።በሀገራዊ መግባባት እና አንድነት ላይ መስራት (የውስጥ መደመር) ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር የሚጀምረው በጠንካራ የውስጥ አንድነት ነው፥ዜጎች በሁሉም ልዩነታቸው "በመደመር" መንፈስ በመተባበር፣ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎችን መደገፍ አለባቸው።
የዜጎች ሚና በተለያዬ ሀሳቦች ያለመከፋፈል በቀይ ባህር ዙሪያ ያሉ ጥያቄዎችን ከፓርቲና ከማንነት ፖለቲካ በላይ በማስቀደም፣ለብሔራዊ ዓላማ በጋራ መቆም ይገባል።አሉባልታዎችን መዋጋት በዘመነ ድህረ እውነት ( misleading content deliberately spread to deceive people ) በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዙሪያ የሚነሱ የውስጥና የውጭ የጥላቻና የጥፋት ወሬዎችን በእውነት ላይ በተመሠረተ ግንዛቤ በማሸነፍ በሁሉም አውዶች ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዙሪያ ድምጽ መሆን (የውጭ መደመር) ኢትዮጵያ የምትመርጠው መንገድ የኃይል ሳይሆን የሰላማዊ ድርድርና ትብብር መሆኑን ለዓለም ማሳመን(Collaboration,not confrontation)። የዲያስፖራው ሚና በውጭ ሀገር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን( ከምናባዊ ሀገር )በመውጣት የአገራቸውን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጎችንና ምክንያቶችን መሠረት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ማስረዳት፣ የሎቢ( Looby )ሥራ መሥራት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን መደገፍ ይገባቸዋል ።ይህ ጊዜ እንደትናንቱ እንዳይቆጨን በአስታውሎት ማጤን ያስፈልጋል ።
እውቀትን ማጋራት(Dissemination, knowledge transfer, communication, and education) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ፣ምሁራን፣ የሕግ ባለሙያዎችና የታሪክ ተመራማሪዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብቷን የሚያረጋግጡ ታሪካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ዓለም አቀፍ የሕግ መረጃዎችን አጥንተው ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ( International community) በማቅረብ ለህዝባቸው ያላቸውን ወገንተኝነት ማሳየት አለባቸው ።
ለቀይ ባህር ተጋሪነት ጥያቄ መሠረቱ ጠንካራ ኢኮኖሚና ብሔራዊ አቅም ነው። ወደብ ማግኘት ዋናው ግብ አይደለም፤ ነገር ግን ወደቡን በብቃት መጠቀም መቻል ነው።ምርታማነትን ማሳደግ እያንዳንዱ ዜጋ በየሥራው ምርታማነትን በመጨመር የሀገርን ኢኮኖሚ ማጠናከር ይኖርበታል።ጠንካራ ኢኮኖሚ የዲፕሎማሲው አውራ ክንድ ነው በእጥፍ እያደግን እና እየተለወጥን ስንመጣ በኢንቨስትመንት አቅም እና እድል የኢትዮጵያ ዲያስፖራና ባለሀብቶች (የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ) ወደፊት ለሚከፈቱ የሎጂስቲክስና ወደብ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስና እውቀት በማፍሰስ የባህር በርን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይችላሉ ።
ለቀጣናዊ ሰላም መስበክ (የሰላም መደመር) ቀይ ባህር መልህቅ እንዲሆን የሚቻለው ቀጠናው ሲረጋጋ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ በልዩ ልዩ መንገድ ስለ ሰላም አስፈላጊነት እና ጥቅም በሚገባ መግለጥ ይገባል ከእያንዳነዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ ይጠበቃል ።
አዎንታዊ ትርክት መፍጠር ( Pragmatic narratives-self-interests, national aspirations, and global complex interdependence) ኢትዮጵያ ወደብ የምትፈልገው ጎረቤቶቿን ለመጉዳት ሳይሆን የሁሉንም ወገን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር መሆኑን የሚያሳይ አዎንታዊ መልእክት ማስተላለፍ፤ቀይ ባህር የኢትዮጵያ መልህቅ እንዲሆን የዜጎች ተግባር የተናጠል ትርፍን ትቶ ለጋራ ብሔራዊ ጥቅም በጠንካራ የ"መደመር" መንፈስ መቆም ነው።
ይህ የአስተሳሰብ ለውጥ ወደ አንድነት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ እና ቀጣናዊ ሰላም የሚያደርስ ዘላቂ የሀገር ህልውና ዋስትና በመሆኑ ዛሬን ከተጉበት ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ዘላቂ ውጤት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ። በቀጣይነትም ከዚህ አጀንዳ እና ሀገራዊ ጥቅም አንፃር የሚኖረኝን መረዳት አካፍላለሁ ።
በሀብታሙ ደባሱ አዲሱ

#ቀይ_ባህር_ለኢትዮጵያ_ሀገራዊ_ጥቅም
#ethiopia | ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቀይ ባህርን በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሀሳብ የኢትዮጵያን ዘላቂ ህልውና የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ነው። ይህን መሰረታዊ ሀቅ በተለያዩ መመዘኛዎች ለማሳየት እሞክራለሁ :-
የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ ግዴታ፦ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት በፍጥነት እያደገች ያለች ሀገር ናት።የዓለም አቀፉ የንግድና ልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) መረጃ እንደሚያሳየው፣ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት (Landlocked Countries) ከባህር በር ካላቸው ሀገራት በአማካይ ሁለት እጥፍ የበለጠ የትራንስፖርት ወጪ ይሸከማሉ። ይህም የሀገሪቱን ምርት ተወዳዳሪነት በመቀነስ፣ የዋጋ ግሽበትን በማባባስ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ይገድባል። ለአንድ ትልቅ ኢኮኖሚ የባህር በር ወሳኝ መሠረታዊ መብት ነው።
ጂኦ-ፖለቲካዊ እና የንግድ ደህንነት፦የቀይ ባህር መስመር ለዓለም ንግድ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ደህንነት ከሌሎች ሀገራት ወደቦች ጋር መያያዝ በፖለቲካዊ እና ሎጂስቲካዊ ውሳኔዎች ላይ ጥገኛ ያደርጋታል።የራሷን የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የንግድ መስመሯን አደጋ የመከላከል እና የብሔራዊ ጥቅሟን የማስጠበቅ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አለው።
የታሪክና የህግ እውነታ፦ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የባህር በርዋን በህጋዊና ተቋማዊ ውሳኔ አለማጣቷ፣ ለጉዳዩ ፍትሃዊ እና ዘላቂ መፍትሄ የመፈለግን የታሪክ ግዴታ ያሳያል። የኢትዮጵያ ጥያቄ የጦርነት ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነትና የሰላማዊ ድርድር ነው።
ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሁሉን ስልት እና አቅም በማየት ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ ማሳካት አለባት። ይህ የህልውና ጥያቄ ከፖለቲካ በላይ፣ የኢኮኖሚ ፍትህና የልማት መብት ጉዳይ ነው ።
የዚህ ዘመን ትውልድ( Politically Active Person )እንዲሆን እና ትናንት በተለያየ ፖለቲካዊ ምክንያት እና ሁኔታ ለውይይት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይቀር ለማሰብ የተገታን ጉዳይ እንደገና ለንግግር መነሻ እና የብሔራዊ የልማት አጀንዳ አድርጎ ማቅረብ ኢትዮጵያ በቀጣይነት እና በዘላቂነት ለማሳካት ከምትፈልጋቸው የልማት ትልሞች መሰረት የሚጥል ነው ። የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል እና ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ እንዲህ አይነት ጉዳዬችን በድፍረት ወደ ፖለቲካ መድረክ መምጣታቸው ሊደነቅ ይገባል ።
#ኢትዮጵያ #ሀገራዊ_ጥቅም #ቀይባህር #ሰላምናልማት

12 months ago
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያቋቋመው የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል በይፋ ስራ ጀመረ
#ethiopia | የሚዲያ ልህቀት ማዕከሉ ዛሬ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ፣ ሠልጣኞች ፣ አጋር አካላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ስራ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ሚዲያ ልህቀት ማዕከል የመገናኛ ብዙኃንና የማስታወቂያ ዘርፉ ወቅቱ በሚጠይቀው ሙያና ቴክኖሎጂ ታግዞ እንዲሰራ የባለሙያዎችና የሚዲያ ተቋማትን አቅም የመገንባት ዓላማ የያዘ ሲሆን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ እና የመገናኛ ብዙኃንን አቅም ከማሳደግ አንፃር የላቀ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት በመድረኩ ተገልጿል፡፡
የልህቀት ማዕከሉ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ፣ ህጎችና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ይሰጣል ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፣ በሀገራችን ያለው ጋዜጠኝነት ኢትዮጵያን መምሰል አለበት። መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን ሕብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያጠናክሩ ፣ የህዝብን ትብብርና አንድነት የሚያሳዩ መሆን አለባቸው ብለዋል።
የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የሚዲያ ልኅቀት ማዕከሉ ዋና አላማ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚሰራቸዉ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በተጨማሪ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ጠንካራ ሙያዊ መርህዎች እንዲኖራቸው ለማስቻል እና ብሔራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ለማስቀጠል ያለመ ነዉ ብለዋል፡፡
በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ጠንካራ ሙያዊ መርህዎች እንዲኖራቸው ለማስቻል እና ብሔራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ለማስቀጠል ያለመ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው አመላክተዋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው እንደ ሀገር የሚዲያ ልኅቀት ማዕከል መቋቋሙ የመገናኛ ብዙኃንን ዘርፍ ወቅቱ በሚፈልገው መንገድ ለማሳደግ የጎላ ሚና እንዳለው ገልፀው የአቅም ግንባታ ሥራዎችም ተጠናክረው መቀጠል ከቻሉ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በመሙላት ብቁ እና ተወዳዳሪ ተቋማትን መፍጠር ይቻላል ብለዋል። በጋራ በመሥራትም ሀገራዊ ጥቅም እና ዕድገትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሚዲያ ልኅቀት ማዕከል ከዚህ በፊት ከሚከናወኑ የመገናኛ ብዙኃን ክትትል እና ቁጥጥር ተግባራት ባለፈ ወደ አቅም ግንባታ የሚያሳድግ እንደኾነ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን ማዕከሉ ጋዜጠኞች በትምህርት ቤት ከሚወስዱት ትምህርት ባሻገር የጋዜጠኝነት ሙያዎች ላይ ብቁ የሚኾኑበት ሥልጠና እንደሚሰጥም ተገልጿል።
#ethiopia #centerofexcellence #የሚዲያልህቀትማዕከል

1 year ago
የባህል ጥበባትና ስፖርት ሚዲያ ፎረም ምስረታ እየተከናወነ ነው
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተደራጀ መረጃ ለማቅረብና ለሀገራዊ ጥቅም በሚውሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ያለመ የሚዲያ ፎረም ምስረታ በቢሾፍቱ ከተማ እያከናወነ ይገኛል።
የባህል፣ ጥበባትና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ በሚዲያ ፎረም ምስረታ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ የሚዲያ ፎረሙ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ሚኒስቴሩ በባህል ጥበባትና በስፖርት ዘርፍ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለህዝብ ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማድረስ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም፣ ሚኒስቴሩ በስፖርት፣ በኪነጥበብ እና በባህላዊ እሴቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ለህዝብ የሚደርሱት በበመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት በመሆኑ፣ ፎረሙ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተደራጀና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
ይህ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ስነምግባር ላይ ተመስርተው ለህዝብ መረጃ እንዲያደርሱና ሀገራዊ ጥቅሞችን በሚያጎሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የብዝሃ ባህል፣ ማንነትና ቋንቋ ያላት ሀገር መሆኗን ገልጸው፣ የህዝቦችን የጋራ አብሮነትና አንድነት በሚያጎሉ፣ እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችን ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የጋዜጠኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሚኒስቴሯ አብራርተዋል።
ሚኒስቴሩም ከወረዳ እስከ ብሄራዊ ደረጃ ባሉ የኪነጥበብ ውድድሮች ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በማውጣትና በማበረታታት የሀገር ገፅታ ግንባታ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

Comments