15 days ago
የመደመር አንቀጽ
በእጃችን ላይ ያሉ የጎብኚ መዳረሻዎችን በሚገባ አገልግሎት ላይ ማዋልና ከዚህም ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ጥቅም ሁሉ መሰብሰብ ተገቢና በቀጣይ ለምንጓዘው አቅጣጫ ትልቅ ግብዓት የሚሆን ነው። ከዚህ አንጻርም ብዙዎችን በፍጥነት ወደ ሥራ አስገብተናል፤ ትሩፋቶችንም እያጣጣምን እንገኛለን።
በእነዚህ ጥረቶች ምክንያት ሀገራችንን የሚጎበኙ የውስጥም ይሁን የውጭ ጎብኚዎች ቁጥር በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው። ይሁንና ዘርፉ ከፍተኛ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።
ሀገራችን ከቱሪዝም ሊገኝ የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መለኪያዎች (Strategies) ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።"
የመደመር መንግስት
ገፅ 272-273
#ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation #yemedemermengist #መደመር #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ

9 months ago
የምንደመረው በአንድ ጭንቅላት ለማሰብ ሳይሆን ለአንድ ሀገር ለማሰብ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር እሳቤ ዙሪያ አራተኛ መጽሐፋቸውን አስመርቀዋል።
የመደመር መንግሥት የተሰኘው መጽሐፋቸው በቀደሙት የመደመር መፃሕፍት የተቀመጡ ነጥቦች ወደ መንግሥታዊ ወይም ተቋማዊ ፍኖት የሚመጡበትን ዓውድ የሚያትት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ፥ ኢትዮጵያ ለሁላችንም ትበቃለች፤ የምንደመረው በአንድ ጭንቅላት ለማሰብ ሳይሆን ለአንድ ሀገር ለማሰብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የአቅም እና የአቋም ድምር ካለ ኢትዮጵያውያን የማይሻገሩት ፈተና የለም፤ የምትመስል ሳይሆን የምትመሰል ሀገር ነው መገንባት የምንፈልገው ነው ያሉት።
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኝ መትከል መቻል ቀዳሚው ትዕምርት መሆኑን አንስተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በትውልድ መካከል ሳይቆም ፈተናዎችን ተሻግሮ እውን የሆነው ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል።
በራስ አቅም፣ በራስ ገንዘብ ከጭለማ ልምምድ ነፃ የወጣ ከተማ ግንባታ አካል የሆነው የኮሪደር ልማትም ሌላኛው ተምሳሌት ነው ብለዋል።
የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የስንዴ ልማትም በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ተምሳሌት የሚያደርጓት ሥራዎች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ የይቻላል እሳቤን ለሌሎች ሀገራት የማስተጋባት አቅም አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከተደመርን፣ በጋራ ለመስራት ከወሰንን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
በታሪክ ካየነው ስብራት ተምረን ወደ ምንፈልገው ራዕይ መድረስ አለብን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቀጣዩ መጽሐፋቸው የመደመር ስሌት በፍሪሊዮን በሚል ርዕስ ለንባብ እንደሚበቃ ጠቁመዋል።
በቤተልሔም ገረመው #yemedemermengist #pmabiyahmed