Logo
Getu Temesgen
🏃🏽‍♂️ "እንጦጦ ፓርክ ሩጫ ተመለሰ! በፍቅረኛሞች ቀን ልዩ ሽልማት!" ❤️🌳

​#ethiopia | My Valentine is Running! - ከፍቅረኛዎ ጋር ይሮጡ፤ በኩሪፍቱ ሪዞርት ይሸለሙ!

​በጉጉት የሚጠበቀው እና በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚዘጋጀው ወርሃዊው 'እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ' (Entoto Park CBE Run) ከየካቲት ወር ጀምሮ ዳግም ተመልሷል!

​የፊታችን እሁድ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር፤ ከስፖርት እንቅስቃሴው በተጨማሪ የፍቅረኛሞች ቀንን (Valentine's Day) ታሳቢ ያደረጉ ልዩ ዝግጅቶች ተካተዋል።

​ልዩ እድሎች:
✅ ሽልማት: አሸናፊ ለሚሆኑ ጥንዶች በኩሪፍቱ ሪዞርት ልዩ ሽልማቶች ይበረከቱላቸዋል።

✅ ምዝገባ:
በ"CBE Birr Plus" መተግበሪያ አማካኝነት በነፃ እና በቀላሉ መመዝገብ ይችላሉ።

✅ ትራንስፖርት:
የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን አዳዲስ መዳረሻዎችን እያስጎበኘ ወደ ፓርኩ አድርሶ የሚመልስ የነፃ ትራንስፖርት አዘጋጅቷል።

​ጤናዎን እየጠበቁ፣ ፍቅርን እያደሱ ለመሮጥ ተዘጋጁ!

​#entotoparkrun #greatethiopianrun #cbe #valentinesrun #myvalentineisrunning #addisababa #health #love #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.