Logo
Getu Temesgen
🌳 ቴፒን በጋራ እናልማ
የ"ትንሿ ኢትዮጵያ" ዳግም ውልደትና የልማት ጥሪ
#ethiopia | ​የታሪክ ድርሳናት እንደሚነግሩን ቴፒ ከተማ በ1911 ዓ.ም የተቆረቆረች፣ የኢትዮጵያ የዘመናዊነት አውራ ጎዳና ቀዳሚ ተጠቃሚ የነበረች ታሪካዊ የንግድ ማዕከል ናት። ገና በ1960ዎቹ የአውሮፕላን ትራንስፖርት፣ በ1966 የጤና ጣቢያና የጠጠር መንገድ የነበራት ቴፒ፤ ዛሬም ያንን ገናና ታሪኳን አድሳ ወደ ከፍታ ለመመለስ ቆርጣ ተነስታለች።

​🇪🇹 ቴፒ፦ የብዝሃነትና የተፈጥሮ ዕንቁ

​አረንጓዴ ካባ የደረበችው ቴፒ፣ "ትንሿ ኢትዮጵያ" ተብላ ትጠራለች። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ የቡናና የቅመማ ቅመም ምርቷን ለዓለም ገበያ የምታቀርብ የኢኮኖሚ ምሰሶ ናት።

​🚧 የልማት እንቅፋትና አዲስ ተስፋ

​ከተማዋ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ምርት የምታቀርብ ብትሆንም፣ የዘመናዊ መንገድ መሠረተ ልማት እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኖባት ቆይቷል። ይህንን ችግር ለመፍታት፦
​ከሚዛን፣ ከማሻ-ጎሬ እና ከሽሽንዳ የሚመጡ ዋና ዋና መንገዶች በፍጥነት እየተገነቡ ይገኛሉ።

​ነገር ግን፦
የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሁላችንንም እገዛ ይሻሉ።

​🤝 የ"ህብረት" ጥሪ ለቴፒ ልጆችና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!
​የቴፒ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነባራዊ እድገትና ቀደምት ስልጣኔ ባገናዘበ መልኩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በራስ አቅም ለመገንባት ፕሮጀክት ነድፎ ወደ ተግባር ገብቷል።

​በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ የቴፒ ተወላጆች፣ ወዳጆችና የልማት አጋሮች በሙሉ፦ "ዘንድሮ የምትሞሸረውን ቴፒን በጋራ እናስውብ!" ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

​💰 የልማት ተሳትፎዎን በሚከተለው የባንክ አካውንት ያድርጉ፦
​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000731791558
​የአካውንቱ ስም፦ ቴፒ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ አስፓልት ግንባታ

​💡 መፈክራችን፦ "በኅብረት ሁሉን እንችላለን!!"

​የከተማችን መልማት የሀገራችን ብልፅግና መሠረት ነው። ዛሬ ለቴፒ የምናደርገው ድጋፍ ለነገው ትውልድ የምናስቀምጠው ትልቅ አሻራ ነው።

​የቴፒ ከተማ አስተዳደር፤
በመምህር ኃይማኖት ተስፋዬ እና
በናትናኤል ዳኜ በኩል የተላለፈ መልዕክት

​#tepi #ethiopia #development #communityservice #infrastructure #coffeeland #unityindiversity #ethiopiaprogress #tepicity

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.