4 hours ago
ዶ/ር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን
ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ የጥላቻ ጥቃት አወገዙ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም ገብረኢየሱስ በደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ያገረሸውንና በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠረውን አሰቃቂ የመጤ ጥላቻ (Xenophobia) ጥቃት አጥብቀው ኮነኑ።
በጥቃቱ ሳቢያ ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያንና አምስት የሞዛምቢክ ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ድርጊቱን «እጅግ ልብ ሰባሪ» እና ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ሥርዓት ለመውጣት በታገለችበት ወቅት አፍሪካውያንና በተለይም ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ያሳዩትን ታሪካዊ አጋርነት የካደ «አሳዛኝ ድርጊት» ሲሉ ገልጸውታል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክትም፣ ማንኛውም ቅሬታ በሕግ የበላይነት እንጂ በቡድን ጥቃት መፈታት እንደሌለበት አሳስበው፣ ጥላቻው በአስቸኳይ እንዲቆምና ተጋላጭ ወገኖች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም «ኦፕሬሽን ዱዱላ» ከተሰኘው ንቅናቄ ጋር በተያያዘ ከሚሰነዘሩ የማግለልና የማጥቃት ቅስቀሳዎች የተነሳ በከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ውስጥ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ቃል ቢገቡም፣ የማስፈራራት፣ የአካላዊ ጥቃትና የዝርፊያ አደጋዎች አሁንም ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኤምባሲ ልዑካን ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው ማረጋገጫ ማግኘታቸውንና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ቢገልጹም፣ በአካባቢው የሚኖሩ አንዳንድ ስደተኞች ግን የመንግሥት ምላሽ ከችግሩ አጣዳፊነት አንጻር «የዘገየ» ነው ሲሉ ተችተዋል።
#stopxenophobia #southafrica #ethiopia #humanrights #africaunite #drtedros

29 days ago
የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ ቫይረስ ምክንያት ዓለማቀፍ የጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ የመጣውን የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ተከትሎ፣ ወረርሽኙን ይፋዊ የዓለማቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት አድርጎ አውጇል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (ኤክስ) ባስተላለፉት መረጃ፣ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በቫይረሱ ሳቢያ የ 88 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 300 ያህል ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን አረጋግጠዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የኢቦላ ቫይረስ ልክ እንደ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁሉ የመቀጣጠልና በከፍተኛ ፍጥነት የመስፋፋት አቅም እንዳለው በማስገንዘብ፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አስቸኳይና ጥብቅ የሆኑ የመከላከል ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ebolavirus #publichealthemergency #who #drtedros #africahealth #globalhealth #breakingnews #thiqaheth

3 months ago
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለጹ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖችና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል።
በአካባቢው የተከሰተው ይህ አደጋ በርካታ ቤተሰቦችን ለሃዘንና ለችግር የዳረገ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gamozone #landslide #who #drtedrosጸAdhanom #ethiopia #gachobaba #emergencyresponse #staysafe #humanitarianaid

Comments