3 months ago
ሰሜን ሽዋ በአምስት አመት ያስመዘገበው ውጤት
https://youtu.be/gAHKt6lrq...
#ethiopia #northshewa #pmabiyahmed #development #selfreliance
5 months ago
አንድ ሳንቲም የበጎ አድራጎት ድርጅት በይፋ ስራ ጀመረ
#ethiopia | በከፍተኛ የህክምና ወጪ ለሚቸገሩ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ዓላማ ያነገበው "አንድ ሳንቲም" የተሰኘው ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በዛሬው ዕለት ማምሻውን በግዮን ሆቴል ስነ-ስርዓት በይፋ ስራውን ጀምሯል።
ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለይም የልብ፣ የኩላሊት እና የካንሰር ታማሚዎችን ለመርዳት በኢትዮጵያውያን ተመስርቶ በቅርቡ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፍቃድ መውሰዱ በመርሃግብሩ ላይ ተገልጿል።
ድርጅቱ ከህዝብ የሚሰበሰበው መዋጮ ምንም አይነት የአስተዳደር ወጪ ሳይቀነስበት 0% የአስተዳደር ወጪ መቶ በመቶ ለታለመለት የህክምና እርዳታ ብቻ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።
የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ሹምዬ ባደረጉት ንግግር የድርጅቱን ዋና ፍልስፍና ሲያስረዱ፦
"ድርጅታችን ከውጭ ሀገር የሚጠበቅ ምንም አይነት እርዳታ አይጠይቅም። ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ብቻ የሚንቀሳቀስ ነው። ይህ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ ማሳያ ከመሆኑም በላይ፣ በራስ የመተማመን መንፈስን የሚያጎለብት ነው" ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #charity #yeandsantim #healthsupport #selfreliance #addisababa #philanthropy

ዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ድጋፍ አደረገ
#ethiopia | ዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት የ1447 ዓመተ ሂጅራ የረመዷን ጾምን በማስመልከት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር በዛሬው ዕለት አከናወነ።
በመርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ ታፈሰ አመንሲሳ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ከተመሠረተ ጥቂት ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ የቆመለትን ዓላማ ለማሳካት ሰፊ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ድርጅቱ ሥራውን ለማከናወን የውጭ ፈንዶችን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም፣ የታሰበው ድጋፍ ባልተገኘበት ወቅት "ዮዳሄ እጃችን ለድጋፍ፣ ልባችን ለፍቅር " በሚል መሪ ቃል መንፈስ አባላቱን በማስተባበር በወረዳው ለሚገኙ ወገኖች የረመዳንን ጾም በማስመልከት የማዕድ መርሐግብር ማከናወኑን ገልጸዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደህንነት ገብሩ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ በዚህ ፈታኝ ወቅት ያሳየው የተራድኦ ተግባር የሚመሰገን መሆኑን ገልጸው፤ መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች የሕዝቡን የአንድነትና የመረዳዳት እሴት እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለዝግጅቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የድርጅቱ አባላት፣ የወረዳው አመራሮችና በጎ ፈቃደኞች ምስጋና ቀርቧል።

በዕለቱ የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደህንነት ገብሩ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የዮዳሄ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011፣ በምዝገባ ቁጥር 7460 ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ መንቀሳቀስ መጀመሩ ይታወቃል።
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን
#yodahecharity #ramadankareem #iftarsharing #ethiopia #socialimpact #communityservice #charityevent #kirkossubcity #selfreliance

Comments