Logo
Getu Temesgen
አንድ ሳንቲም የበጎ አድራጎት ድርጅት በይፋ ስራ ጀመረ
#ethiopia | በከፍተኛ የህክምና ወጪ ለሚቸገሩ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ዓላማ ያነገበው "አንድ ሳንቲም" የተሰኘው ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በዛሬው ዕለት ማምሻውን በግዮን ሆቴል ስነ-ስርዓት በይፋ ስራውን ጀምሯል።

​ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለይም የልብ፣ የኩላሊት እና የካንሰር ታማሚዎችን ለመርዳት በኢትዮጵያውያን ተመስርቶ በቅርቡ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፍቃድ መውሰዱ በመርሃግብሩ ላይ ተገልጿል።

​ድርጅቱ ከህዝብ የሚሰበሰበው መዋጮ ምንም አይነት የአስተዳደር ወጪ ሳይቀነስበት 0% የአስተዳደር ወጪ መቶ በመቶ ለታለመለት የህክምና እርዳታ ብቻ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

​የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ሹምዬ ባደረጉት ንግግር የድርጅቱን ዋና ፍልስፍና ሲያስረዱ፦
​"ድርጅታችን ከውጭ ሀገር የሚጠበቅ ምንም አይነት እርዳታ አይጠይቅም። ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥና በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ብቻ የሚንቀሳቀስ ነው። ይህ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ ማሳያ ከመሆኑም በላይ፣ በራስ የመተማመን መንፈስን የሚያጎለብት ነው" ብለዋል።

​Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#ethiopia #charity #yeandsantim #healthsupport #selfreliance #addisababa #philanthropy

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.