7 months ago
ሲፒጄ በኢትዮጵያ የታሰሩ ሴት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ (CPJ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ።
የሲፒጄ መግለጫ ጋዜጠኞች መስከረም አበራ እና ገነት አስማማው መሆናቸውን አስታውቋል።
ከአማራ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ በሰሯቸው ዘገባዎች ሳቢያ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለሦስት ዓመታት ያህል በእስር ላይ ይገኛሉ።
ሁለቱ ጋዜጠኞች በመጪው ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለፍርድ ቤት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የእነዚህ ጋዜጠኞች መታሰር በተለይ በፖለቲካና በግጭት ዙሪያ የሚዘግቡ ሴት ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅ የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ሲፒጄ ገልጿል።
ሙያዊ ዘገባዎችን እንደ ወንጀል የመቁጠር አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተቋሙ በጽኑ ተችቷል።
የሴት ጋዜጠኞች መታሰር በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ወደ ኋላ የሚመልስ መሆኑ ተመልክቷል።
በሙያው ላይ በተሰማሩ ሴቶች ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና እና የስራ ዋስትና ስጋት እንደሚፈጥር ሲፒጄ አስገንዝቧል።
ሲፒጄ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፕሬስ ነፃነትና ለሴት ጋዜጠኞች መብት ክብር በመስጠት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጋዜጠኞቹን እንዲፈታ አሳስቧል።
#cpj #pressfreedom #ethiopia #journalismisnotacrime #meskereabber #genetasmamaw #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments