8 months ago
"ውሳኔው ይነሳ! የዋዜማ ሬዲዮ ፈቃድ ይመለስ!"
- የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#ethiopia | "ባለስልጣኑ የወሰደው እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ የሚዲያ ምህዳሩን በፍርሃት ይሞላል!"
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በዋዜማ ሬዲዮ ላይ ያሳለፈውን የሥራ ፈቃድ እግድ በተመለከተ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል።
የማኅበሩ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች:
🛑 እግዱን መቃወም:
ማኅበሩ ባለስልጣኑ በዋዜማ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በጽኑ የተቃወመ ሲሆን፤ የሚዲያ ተቋሙ ላይ የቀረበው "ሚዛናዊነት ይጎድለዋል" የሚለው ውንጀላ ከእውነታው የራቀ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
🛑 የመፍትሔ አግባብ:
ስህተቶች ቢኖሩ እንኳን በ "ሚዲያ ካውንስል" ደንብ መሰረት መታረም ሲገባቸው፤ ፈቃድ መንጠቅ ግን ለዲሞክራሲ ግንባታው ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሚፈጥር ጠቁሟል።
🛑 የሚዲያ አፈና:
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚዲያዎች ላይ የሚደረገው ጫና መጨመሩን ያወሳው መግለጫው፤ አሻም ቲቪ ከስራ ውጪ መደረጉን እንዲሁም ጋዜጠኞች (ዮናስ አማረ፣ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ተስፋለም ወልደየስ) ለእስር መዳረጋቸውን በማሳያነት ጠቅሷል።
ጥሪ:
ባለስልጣኑ ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤን እና የዋዜማ ሬዲዮ የስራ ፈቃድ ተመልሶ ወደ ስራ እንዲገባ ማኅበሩ ጠይቋል።
ምንጭ፡
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#wazemaradio #pressfreedom #ethiopia #aejc #mediarights #journalism

Comments