19 days ago
ቫቲካን፡ ተፈጥሮን መጉዳት ከፈጣሪና ከፍጥረት ጋር የተያያዘ ኃጢአት ነው
#ethiopia | ሮም — የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአካባቢ ጥበቃን ከእምነትና ከሞራል ጉዳይ ጋር በማያያዝ፣ ተፈጥሮን ከፍተኛ ሁኔታ መጉዳትን “በፍጥረትና በፈጣሪ ላይ የሚፈጸም ኃጢአት” በሚል የሥነ-መለኮት እይታ እንዲታይ አሳስባለች።
ይህ አቋም በዓለም አቀፉ የሥነ-መለኮት ኮሚሽን (International Theological Commission) ያወጣው “Caring for Our Common Home – A Responsible and Fraternal Response to the Triune God” የተሰኘ አዲስ ሰነድ ላይ ተቀምጧል። ሰነዱ በመስከረም 2 ቀን 2026 በሊዮ 14ኛ ፓፕ ፈቃድ ይፋ መሆኑን ቫቲካን ገልጻለች።
ተፈጥሮን መጉዳት ለምን ኃጢአት ተባለ?
ሰነዱ የአካባቢ ችግርን እንደ ሳይንሳዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ብቻ አይመለከተውም። በካቶሊክ ሥነ-መለኮት አመለካከት፣ ሰው ከእግዚአብሔር፣ ከሌሎች ሰዎች እና ከፍጥረት ጋር በተያያዘ ሕይወት እንዲኖር የተጠራ ነው።
በመሆኑም ተፈጥሮን ማውደም ወይም ሀብቷን ያለገደብ መበዝበዝ የተፈጥሮ ጉዳት ብቻ ሳይሆን፣ ፈጣሪ ለሰው የሰጠውን የኃላፊነት ግዴታ መጣስ እንደሆነ ሰነዱ ያብራራል።
ሰነዱ በተለይ “ኃጢአት በፍጥረት ላይ እና በፈጣሪ ላይ” የሚለውን አገላለጽ ያቀርባል። ይህም የአካባቢ ጥፋትን ከሰው ሞራላዊ ምርጫ፣ ከፈጣሪ ዕቅድ እና ከሰው ኃላፊነት ጋር ያገናኛል።
ብክለት፣ የውኃ ጥፋትና የብዝሃ ሕይወት መጥፋት
የቫቲካን ሰነድ በዓለም ላይ እየተባባሱ ካሉ የአካባቢ ችግሮች መካከል የብዝሃ ሕይወት መቀነስን፣ የአየር ብክለትን፣ የውኃ ጥራት መቀነስን እና በጦርነት የሚፈጠረውን የአካባቢ ውድመት በማስጠንቀቅ ይጠቅሳል።
በተለይ የብዝሃ ሕይወት መጥፋት የተፈጥሮ ውበት መቀነስ ብቻ እንዳልሆነ፣ ለምግብ ዋስትናም ወሳኝ እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል። የውኃ መበከልና የአየር ብክለትም በሰዎች ጤናና ኑሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ተገልጿል።
የተፈጥሮ ጥፋት በድሆች ላይ የበለጠ ይጫናል
ሰነዱ በተለይ በአካባቢ ጥፋት እና በድህነት መካከል ያለውን ትስስር አጽንዖት ይሰጣል።
በተፈጥሮ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጥገኛ የሆኑ ድሆች የአካባቢ መበላሸትን በቀጥታ የሚጋፈጡ መሆናቸውን ቫቲካን ትገልጻለች። የውኃ እጥረት፣ የመሬት መራቆት፣ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአካባቢ ብክለት በድሃ ማህበረሰቦች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥር ሰነዱ ያብራራል።
ይህም የተፈጥሮን “ጩኸት” ከድሆች ጩኸት ጋር በማያያዝ፣ የአካባቢ ጥበቃን ከማህበራዊ ፍትሕ ጋር እንዲታይ ያደርገዋል።
የኢኮሎጂ ለውጥ ከመንፈሳዊ ለውጥ ጋር
ቫቲካን ችግሩ በቴክኖሎጂ ወይም በሕግ ብቻ እንደማይፈታ ትገልጻለች። የምርት፣ የፍጆታ፣ የመጓጓዣ እና የኃይል አጠቃቀም ሥርዓቶች ለውጥ ከሚያስፈልገው ጎን ለጎን የሰዎች እሴትና አኗኗርም መለወጥ እንዳለበት ትጠይቃለች።
ይህንን ለውጥ ሰነዱ “ecological conversion” — የኢኮሎጂ መለወጥ በሚል ይጠራዋል። ሰዎች ተፈጥሮን እንደ ማያልቅ የሀብት ምንጭ ከማየት ይልቅ የጋራ መኖሪያ ቤት እንደሆነች በማየት የአኗኗር ለውጥ እንዲያደርጉ ይጠይቃል።
ውኃን መጠበቅም የእምነት ጉዳይ ነው
ፓፕ ሊዮ 14ኛ በመስከረም 2026 ለ“የፍጥረት ጥበቃ የጸሎት ቀን” ባስተላለፉት መልእክትም ውኃን መጠበቅ፣ ብክለትን መቃወም እና የሁሉም ሰው ንጹሕ ውኃ የማግኘት መብትን መጠበቅ ከፍጥረት ጥበቃና ከድሆች ሕይወት ጋር አያይዘዋል።
በዚያው ወር ለ11ኛው የፍጥረት ጥበቃ የጸሎት ቀን ባስተላለፉት መልእክት፣ ጦርነት እና የአካባቢ መበላሸት እርስ በርስ የሚጠናከሩ ችግሮች መሆናቸውን ገልጸዋል። ጦርነት አየርና ውኃን ከመበከል በተጨማሪ የምግብ ዋስትናን እንደሚያሳንስ፣ ድህነትንና እኩልነት እጦትንም እንደሚያባብስ አስጠንቅቀዋል።
ከካቶሊክ ትምህርት አንጻር አዲስ ቃል ብቻ አይደለም
“ተፈጥሮን መጉዳት ኃጢአት ነው” የሚለው ሀሳብ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ አዲስ አይደለም። የ2019 የአማዞን ሲኖድ ሰነድ እንኳን “ecological sin” የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ በመጠቀም፣ ብክለትና የአካባቢ ውድመት በእግዚአብሔር፣ በሰው ልጆች፣ በማህበረሰብ እና በወደፊት ትውልዶች ላይ የሚፈጸም ጥፋት እንደሆነ ገልጾ ነበር።
ስለዚህ የ2026 ሰነድ ይህንን አቋም ወደ ሰፊ የሥነ-መለኮት ማብራሪያ በማስፋት፣ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የሳይንስና የፖሊሲ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰው ሞራላዊ ኃላፊነት እና ከፈጣሪ ጋር ያለው ግንኙነት ጉዳይ እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣል።
በአጠቃላይ፣ የቫቲካን መልእክት “ምድርን መጠበቅ” ከተራ የአካባቢ ፖሊሲ ጉዳይ ወደ የእምነት፣ የሞራል፣ የማህበራዊ ፍትሕ እና የትውልድ ኃላፊነት ጉዳይ እንዲታይ ያደርገዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

4 months ago
#june 16/2026
ELiDA Ethiopia proudly celebrates the establishment of the National Anti-Technology Facilitated Gender-Based Violence (Anti-TFGBV) Network.
We extend our sincere gratitude to government institutions, civil society organizations, media, social media influencers, justice actors, academia, and development partners who have united behind one clear message: online violence must end.
Together, we are building a stronger movement for safer digital spaces, survivor-centered responses, effective laws, accountability, and justice.
This is not just a network—it is a national commitment to ensure that every woman and girl can participate, lead, and thrive online without fear.
ኤሊዳ ኢትዮጵያ (ELiDA Ethiopia) ብሔራዊ የፀረ-TFGBV (ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት) መረብ መመስረቱን በኩራት ያበስራል።
«የኢንተርኔት ጥቃት ሊቆም ይገባል!» በሚለው አንድ ግልጽ ዓላማ ሥር ለተሰለፋችሁ፦
ለመንግሥትና ለፍትህ ተቋማት፣
ለሲቪል ማኅበረሰብ እና ለልማት አጋሮች፣
ለሚዲያ፣ ለማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ለአካዳሚዎች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በጋራ በመሆን፦ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ምኅዳር፣ ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ ምላሽ፣ ጠንካራ ሕጎች እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት እንገነባለን።
ይህ ዝም ብሎ መረብ አይደለም፤ እያንዳንዱ ሴት እና ሴት ልጅ ያለ ፍርሃት በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንዲሳተፉ፣ እንዲመሩ እና እንዲበለጽጉ የተገባ ብሔራዊ ቃል ኪዳን ነው!
#የፀረTFGBVመረብ #tfgbvይብቃ #tfgbv #elidaethiopia ! #antitfgbvnetwork #endtfgbv #digitalsafety #technology #የቴክኖሎጂ_ጥቃት_ይቆም #ዲጂታል_ደኅንነት
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር Ethiopian Civil Society Organizations Council Ethio telecom Sustainable Technology Solutions-STS Christian Aid Institute for Peace and Security Studies UN Trust Fund to End Violence against Women Ethiopian Women Development Organization - EWDO የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ የመንግሥት ሰራተኞች
7 months ago
ትልቁ የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ሴራ ወታደራዊ ሰፈር (Military Base)
ወታደራዊ ሰፈር (Military Base) ምንድን ነው ? ከጀርባውስ ምን ሴራ ይዟል ?
ወታደራዊ ሰፈር ማለት አንድ አገር ከገዛ ድንበሩ ውጭ ወይም በውስጥ የጦር ኃይሉን የሚያሰፍርበት፣ ትጥቅ የሚያከማችበት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያዝበት ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው።
እነዚህ ሰፈሮች እንደ መጠናቸውና ዓላማቸው ሊለያዩ ይችላሉ
የአየር ኃይል ጣቢያዎች ለጦር አውሮፕላኖችና ለድሮኖች የባሕር ኃይል ወደቦች ለጦር መርከቦችና ለባሕር ውስጥ ሰርጓጅ መርከቦች የደኅንነትና የመረጃ ማእከላት የጠላትን እንቅስቃሴ ለመሰለልና መረጃ ለመሰብሰብ ይውላሉ
ለምንድን ነው እንደ አሜሪካ ያሉ አገራት በሌሎች አገሮች ላይ ወታደራዊ ሰፈር የሚገነቡት?
አሜሪካ በዓለም ዙሪያ ከ800 በላይ ወታደራዊ ሰፈሮች አሏት ይህ የሚደረግበት ዋና ዋና ምክንያቶች
1 ፈጣን ምላሽ ለመስጠት (Rapid Response) ነው ይህም ጦርነት ቢነሳ ጦርን ከአሜሪካ ከማጓጓዝ ይልቅ በአቅራቢያው ካለ የጦር ሰፈር ተነስቶ በፍጥነት እርምጃ ለመውሰድ ይውላል
2 ስትራቴጂካዊ ቁጥጥር (Global Dominance) ለማድረግ ይውላላል ለምሳሌ እንደ ቀይ ባሕር፣ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ እና የሆርሙዝ ወሽመጥ ያሉ የንግድ መስመሮችን ለመቆጣጠር ይረዳል
3 በቀጠናው ተጽዕኖን ማስፋፋት (Power Projection) ይረዳል ይህም በአካባቢው ያሉ ወዳጅ አገራትን ለመጠበቅ እና ተቀናቃኞችን (እንደ ኢራን፣ ሩሲያ ወይም ቻይና) ለማስፈራራት ትጠቀምበታለች
4 የመረጃ ምንጭ ለመሰብሰብ ይረዳል ከየአቅጣጫው የሚነሱ የሚሳይል ጥቃቶችን ቀድሞ ለመለየትና መረጃ ለመሰብሰብ።
ከወታደራዊ ሰፈሮች በስተጀርባ ያለው "የፖለቲካ ሴራ" ምንድን ነው ?
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በኢራን መካከል ባለው ውጥረት ሰለባ የሚሆኑት እንደ እስራኤል፣ ኳታር፣ ሳውዲ ዓረቢያ፣ ባህሬንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ያሉ አገራት ናቸው እዚህ ጋር ያለው እውነታ የሚከተለው ነው
1- የሰው ጋሻ (Human Shield) ፖለቲካ፦
አሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮቿን በእነዚህ አገራት ላይ ስታስቀምጥ ኢራን አሜሪካን ለመምታት ስትፈልግ መጀመሪያ የምታርፈው በእነዚህ አገራት ላይ ነው ይህም አሜሪካን በቀጥታ ከሚደርስ ጥቃት ይከላከልላታል።
2- የመሣሪያ ሽያጭና ኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት - እነዚህ አገራት ጥቃት ሲሰነዘርባቸው ወይም ስጋት ሲገባቸው ከአሜሪካ የመከላከያ ስርዓት (እንደ ፓትሪዮት ሚሳይል) ለመግዛት ይገደዳሉ ይህም የአሜሪካን የጦር መሣሪያ ኢንዱስትሪ በእጅጉ ይጠቅማል።
3- ሉዓላዊነትን መጋራት፦ ወታደራዊ ሰፈር የሚያስተናግዱ አገራት የውጭ ፖሊሲያቸውን ከአሜሪካ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም ይገደዳሉ ይህ ደግሞ አገራቱን የአሜሪካ "ተላላኪ" ወይም "ተለጣፊ" ደርጋቸዋል
አንድ ሚሳይል ግዙፏን አሜሪካን በአካል አያጠፋትም ነገር ግን የአሜሪካን ስም፣ ሞራልና የኃያልነት ግርማ (Prestige) ሊያጠፋው ይችላል አንድ የአሜሪካ ሰፈር ሲመታ ዓለም አቀፍ ገበያው ይናጋል፣ የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል፣ እናም የአሜሪካ ሕዝብ መንግሥቱን "ለምን ልጆቻችን በሰው አገር ያልቃሉ?" ብሎ መጠየቅ ይጀምራል ይህ ደግሞ ከጦርነት በላይ ፖለቲካዊ ሽንፈት ነው።
ወታደራዊ ሰፈሮች ለሰላም ማስከበር ሳይሆን ለጥቅም ማስከበር የሚቆሙ ናቸው። አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሏት ሰፈሮች ለራሷ ብሔራዊ ደኅንነት "የፊት መስመር" (Frontline) ናቸው በኢራንና በአሜሪካ መካከል በሚደረግ ፍጥጫ መሬታቸውን ለወታደራዊ ሰፈር የሰጡ አገራት ሁልጊዜም በሁለት ድንጋይ መካከል እንደሚገኝ እህል መሆናቸው የማይቀር "የፖለቲካ እውነት" ነው።
አንድ አገር ለሌላ የውጭ አገር ወታደራዊ ሰፈርን መፍቀድ ትልቅ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ እና የደኅንነት ውሳኔ ነው።
ይህ ውሳኔ እንደ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ያለው ሲሆን የወታደራዊ ቀጠና የሚሰጠው አገር የሚከተሉት ጥቅሞችና ጉዳቶች (Pros and Cons) ይኖሩታል።
1. ጥቅሞች (Pros)
አገራት የውጭ ጦርን በምድራቸው ላይ እንዲያርፍ የሚፈቅዱት በዋናነት ለሚከተሉት ጥቅሞች ነው፦
* የደኅንነት ዋስትና (Security Umbrella): ደካማ ወታደራዊ አቅም ያላቸው አገራት፣ እንደ አሜሪካ ያለ ኃያል አገር በምድራቸው ላይ ሰፈር እንዲኖረው በማድረግ ከጎረቤት አገራት ጥቃት ራሳቸውን ይከላከላሉ። "እኔን የነካ አሜሪካን ነካ" የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ።
* የኢኮኖሚ ገቢ (Economic Rent): አስተናጋጇ አገር ለሰፈሩ ኪራይ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ልታገኝ ትችላለች። በተጨማሪም በሰፈሩ ዙሪያ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችና የአካባቢው መሠረተ ልማት (መንገድ፣ መብራት፣ ወደብ) ሊሻሻሉ ይችላሉ።
* የቴክኖሎጂ እና የስልጠና ሽግግር: የአገር ውስጥ ወታደሮች ከውጭ ጦር ጋር አብረው በመሥራት ዘመናዊ የጦር መሣሪያ አጠቃቀምንና ወታደራዊ ስልቶችን ይማራሉ።
* የዲፕሎማሲ ተሰሚነት: የኃያላን አገራት ወታደራዊ አጋር መሆን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘትና የተወሰነ ተሰሚነትን ለመጨመር ይረዳል።
2. ጉዳቶች (Cons)
ጥቅሞቹ ባሉበት ልክ፣ ጉዳቶቹ ደግሞ እጅግ የከበዱና የአገርን ህልውና የሚፈታተኑ ሊሆኑ ይችላሉ፦
* ሉዓላዊነትን ማጣት (Loss of Sovereignty): በገዛ አገርህ መሬት ላይ የሌላ አገር ሕግ የሚሠራበት፣ አንተ የማትቆጣጠረው "አገር በአገር ውስጥ" ይፈጠራል።
የውጭ ጦሩ ያሻውን ሲያደርግ የአገሪቱ መንግሥት ጣልቃ የመግባት አቅሙ ደካማ ይሆናል።
* ለጥቃት መጋለጥ (Becoming a Target):
በአሜሪካና በኢራን መካከል ጦርነት ቢነሳ፣ ኢራን መጀመሪያ የምትመታው አሜሪካን ሳይሆን በአቅራቢያዋ ያሉትን የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ነው። በዚህም አስተናጋጇ አገር ባልገባችበት ጦርነት ሰለባ ትሆናለች።
* ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ችግሮች:
የውጭ ወታደሮች ከባሕል ጋር የማይሄዱ ተግባራትን ሊፈጽሙ ይችላሉ በተጨማሪም የጦር መሣሪያ ሙከራዎችና የኬሚካል ፍሳሾች የአካባቢውን ተፈጥሮና የሰዎችን ጤና ሊጎዱ ይችላሉ።
* የፖለቲካ ጥገኝነት:
አስተናጋጇ አገር የውጭ ፖሊሲዋን በነፃነት መምራት አትችልም ሰፈሩን የገነባው አገር ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ውሳኔ ማሳለፍ "እርዳታ ይቋረጣል" ወይም "ሰፈሩን እናነሳለን" በሚል ዛቻ እንድትፈራ ያደርጋታል።
3.የውጭ ወታደራዊ ሰፈር መፍቀድ "ባለ ሁለት አፍ ቢላዋ" ነው። ለአጭር ጊዜ የገንዘብ ገቢና የደኅንነት ስሜት ቢሰጥም ለረጅም ጊዜ ግን አገርን ለባዕድ ተላላኪነትና ለሌሎች አገራት ጥቃት መሸሸጊያ (Proxy Battlefield) ያደርጋል።
በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ የምናየው እውነት ይኸው ነው እንደ ኳታር እና ባህሬን ያሉ አገራት የአሜሪካን ሰፈር በማስተናገዳቸው ከኢራን ጋር በቋፍ ላይ ያለ ግንኙነት አላቸው።
አሜሪካ "የዓለም ፖሊስ" ሆና ለመቀጠል የእነዚህን አገራት መሬት እንደ ቼዝ ጨዋታ ትጠቀምበታለች። ሰላም ሲኖር ሰፈሮቹ "የጥበቃ" ምልክት ናቸው ጦርነት ሲነሳ ግን "የመጥፊያ" ምልክት ይሆናሉ።
ስለሆነም አንድ አገር ወታደራዊ ሰፈርን ከመፍቀዷ በፊት የራሷን ብሔራዊ ጥቅም እና የሚመጣውን ቀውስ በሚገባ ማመዛዘን ይኖርባታል።
አብዛኛውን ጊዜ ግን ኃያላን አገራት ደካማ አገራትን በብድር፣ በዕዳ ወይም በፖለቲካ ጫና ሰፈር እንዲሰጡ ያስገድዷቸዋል ይህ ደግሞ በስተጀርባው ያለው ትልቁ የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም (Neo-colonialism) ሴራ አካል ነው።

8 months ago
የቴዲ አፍሮ የጊዜ ፍልስፍና፦ የባሻው ምስጢር እና የነፍስ ብርሃን ፍለጋ
የዋሻው ምስጢር
በሰው ልጅ የህይወት ጉዞ ውስጥ ከሁሉ የሚከብደው ጠላት የውጭው ዓለም ፈተና ሳይሆን፣ በገዛ አእምሯችን የምንገነባው "የሀዘን ዋሻ" ነው። ቴዲ አፍሮ “ባሻው” በሚለው ዝማሬው፣ የዚህን ዋሻ በር የሚሰብር መዶሻ ይዞ ይመጣል። ይህ ዘፈን ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ ከአጥንት የሚዘልቅ፣ የሰውን ልጅ የመኖር ትርጉም የሚፈትሽ፣ በዜማ የታጀበ የፍልስፍና መፅሐፍ ነው።
በዚህ ትንተና ውስጥ፣ ቴዲ አፍሮ እንዴት የጊዜን፣ የፍቅርን እና የፅናትን ምስጢር በባሻው ህይወት ውስጥ እንደሰነቀው፣ ከዓለም ታላላቅ ፈላስፎች እና አነቃቂ ታሪኮች ጋር አዛምደን እንቃኘዋለን።
የብርሃን ሰልፍ፦ የፍቅር ጦርነት
"የብርሀን ሰልፍ ነው ያነገበ ፍቅር ሰላም፣ ጤና ለአዳም..."
ቴዲ ዘፈኑን የሚጀምረው በድል አድራጊነት መንፈስ ነው። "ባሻው" የተሰኘው ስያሜ በራሱ ለጥንታዊ የኢትዮጵያ ጀግኖች የሚሰጥ ወታደራዊ ማዕረግ ነው። ነገር ግን ቴዲ የሚነግረን ስለ ጥይትና ስለ ጎራዴ ሳይሆን፣ ስለ "ብርሃን ሰልፍ" ነው። እዚህ ጋር ታላቁን የሰላም ታጋይ ማህተማ ጋንዲን እናስታውሳለን። ጋንዲ "ፍቅር በዓለም ላይ ካሉ ኃይሎች ሁሉ እጅግ ታላቁ ነው" ይላል።
ቴዲ "እንኳን ሰው እንስሳው የፍቅር ነው ሰራዊቱ" ሲል፣ ፍቅር ድንበር የለሽ መሆኑን ይገልፃል። ይህ በኳንተም ፊዚክስ "Entanglement" ከሚባለው ህግ ጋር ይመሳሰላል፤ ሁሉም ነገር እርስ በእርሱ የተሳሰረ ነው የሚል እሳቤ። ባሻው (ሰውየው) በሀዘን ዋሻ ውስጥ ሆኖ ተፈጥሮን ሲረሳ፣ ቴዲ ግን አውሬው ጭምር የፍቅር ሰራዊት መሆኑን በመንገር ከብቸኝነት እስር ያወጣዋል።
የአሁኑ ጊዜ ኃይል (The Power of Now)
"ጊዜ ማይፈታው ምንም የለም... ጊዜም አሁን ነው ትላንት ሆኖ ቀሪ፣ የነገው ቀን ሰሪ"
ይህ የግጥም ክፍል የዘመናችንን ታላቅ ፈላስፋ ኤካርት ቶልን ምስጢር በግልፅ ያስቀምጣል። ቶል “ስቃይ የሚኖረው በትላንት ትዝታና በነገ ስጋት ውስጥ ብቻ ነው፤ አሁን ውስጥ ግን ሰላም አለ” ይላል።
እውነተኛ ታሪክ፦ የኦሽዊትዝ እስር ቤት ተረጂው ቪክቶር ፍራንክል፣ በሞት ጥላ ውስጥ ሆኖ እንዴት ሊተርፍ እንደቻለ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ "ዛሬን" የተመለከተ ነበር። "ጠባቂዎቼ የአካል ነፃነቴን ሊወስዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ለአሁኑ ሰዓት የምሰጠውን ምላሽ (Response) ሊወስዱብኝ አይችሉም" ብሏል።
ቴዲ አፍሮ "ዛሬም ራሱ ነገ ነበረ" ሲል፣ ትላንት ስንጨነቅለት የነበረው "ነገ" ዛሬ መሆኑንና አሁንም እየጨነቅን ካሳለፍነው ህይወታችን በጭንቀት አዙሪት እንደሚጠፋ ይነግረናል። "ጊዜ ማይፈታው ምንም የለም" የሚለው ቃል ደግሞ ለተሰበረ ልብ ትልቅ ተስፋ ነው። ህመም እንደ ደመና ነው፤ ይመጣል፣ ያልፋል። ፀሃይ ግን (አሁን) ሁሌም አለች።
"የእናት ቀለም"፦ የውስጥ ፀሃይነት
"ቀኑ ቢመሻሽ ብለሽ አትስጊ ፋኖስ የለም፣ ፀሃይ ነሽና ለዚች ዓለም"
ይህ ለሴት ልጅ (ለእናት) የተገጠመው ስንኝ፣ ቴዲ አፍሮ ለሰው ልጅ ያለውን ክብር ያሳያል። "ፀሃይ ነሽ" ማለት ሌላ ብርሃን አትጠብቂ፣ ምንጩ አንቺው ነሽ ማለት ነው። አነቃቂው ሌስ ብራውን "በውስጣችሁ ታላቅነት አለ" (There is greatness within you) የሚለውን ሃሳብ ቴዲ በግጥም አቅልሞታል።
"የእናት ቀለም" የሚለው አገላለፅ፣ እናት በባህሪዋ ተስፋን የምትኳል፣ ጥቁርና ነጩን ዓለም በምህረትና በፍቅር የምታቀልም መሆኗን ይገልፃል። በጨለማ ውስጥ ፋኖስ የሚፈልግ ሰው ሌላ ሰው ይጠብቃል፤ "ፀሃይ" የሆነ ሰው ግን ጨለማውን በራሱ መገኘት ያባርረዋል። ቴዲ ባሻውን ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት እያሸጋገረው ነው።
የጊዜ ሚዛን እና የባለቤትነት ውሳኔ
"የጊዜ ሚዛን አይላወስም፣ ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም"
ቴዲ አፍሮ እዚህ ጋር ስለ "ሃላፊነት" (Accountability) ይናገራል። ጊዜ አያዳላም፤ ለሁሉም እኩል 24 ሰዓት ይሰጣል። ልዩነቱ ዛሬን በምን ሞላነው? የሚለው ነው። "ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን" የሚለው መስመር እጅግ ልብ አንጠልጣይ ነው። በሞትና በህይወት መካከል ያለው መስመር ቀጭን መሆኑን ያሳየናል።
ፈላስፋው ማርከስ ኦሬሊየስ እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ዛሬ የመጨረሻ ቀንህ እንደሆነ አድርገህ ኑር።" ቴዲ "የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን" ሲል፣ ዛሬን ከአሉታዊ ሃሳቦች፣ ከትላንት ፀፀት እና ከሌሎች ሰዎች ትችት ነፃ እንደሚያወጣት ይምላል። ይህ የነፍስ ነፃነት አዋጅ ነው።
"ባሻው" እንደ ህይወት ኮምፓስ
በዚህ ረጅም እና ጥልቅ ጉዞ ውስጥ ቴዲ አፍሮ ያስተማረን ቁምነገር ግልፅ ነው፦
ደስታ ውሳኔ ነው፦ "ባሻው ይደሰት" የሚለው ትዕዛዝ እንጂ ልመና አይደለም።
ፍቅር መከላከያ ነው፦ በፍቅር የታጠረ ሰው ከሀዘን ዋሻ ይወጣል።
ጊዜ ውድ ሀብት ነው፦ ዛሬን ያልያዘ ነገን አይቆጣጠርም።
በመጨረሻም፣ ቴዲ አፍሮ "ባሻው" በሚለው ስራው ለእያንዳንዳችን ጥሪ እያቀረበ ነው። ህይወት ቢከፋም ቢለማም፣ ዓለም ብታደንቅህም ባታደንቅህም፣ አንተ "የነገው ቀን ሰሪ" ነህ። የጊዜ ሚዛን ሳይዛባብህ፣ ዛሬን እንደ ፀሃይ አብረህ እንድትወጣ ይጋብዝሃል።
ባሻው ሆይ! ዛሬ የአንተ ናት። አልሰጥም በላት!
አይዞህ ልቤ አይዞህ....

በሳዑዲ በረሃዎች የረገፈው ተስፋ እና የኢትዮጵያ ‘ነፍስ አድን’ ጥሪ፡ በዲፕሎማሲያዊ ዝምታ ውስጥ የሚሰሙ ሰብዓዊ እምባዎች
በሳዑዲ ዓረቢያ የሲሚንቶ ወለል ላይ ለወራት ታጉረው፣ የፀሐይ ብርሃን የናፈቃቸው 1 ሺህ 823 ኢትዮጵያውያን ባለፈው ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲወርዱ የሚታየው ትዕይንት ግን በደስታ ብቻ የተሞላ አይደለም፤ ይልቁንም በድካም የዛሉ ሰውነቶች፣ የተሰበሩ ስብዕናዎች እና የጠፉ ህልሞች ድምፅ አልባ ሰልፍ ይመስላል።
እስካሁን ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን መመለስ መቻሉ የመንግስትን ሰብዓዊ ቁርጠኝነት ቢያሳይም፣ ከጀርባው ያለው ታሪክ ግን በሳዑዲ በረሃዎች የረገፉ ተስፋዎችንና በዲፕሎማሲያዊ ዝምታ የታፈኑ ሰቆቃዎችን የያዘ ነው።
ሶሺዮሎጂስቶች ስደትን “ማህበራዊ ሞት” (Social Death) ይሉታል። አንድ ስደተኛ ከትውልድ ቀዬው ሲወጣና በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ ሰብዓዊ ክብሩ ተገፎ ቁጥር ብቻ ሲሆን፣ ማህበራዊ ህልውናው አደጋ ላይ ይወድቃል። ባለፈው ሳምንት ከተመለሱት መካከል 35ቱ ታዳጊዎች መሆናቸው ደግሞ ቁስሉን የባሰ ያደርገዋል። እነዚህ ህፃናት የጨዋታና የትምህርት ጊዜያቸውን በሳዑዲ መጠለያዎች ውስጥ በፍርሃትና በእንግልት ማሳለፋቸው፣ በማህበረሰቡ የወደፊት ተተኪዎች ላይ የሚተውት ጠባሳ ለትውልድ የሚተርፍ ማህበራዊ ስብራት ነው።
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ለስደተኞች ያለው አያያዝ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ሲታይ እጅግ ግትርና ሰብዓዊነት የጎደለው ነው። እንደ ሂውማን ራይትስ ዎች ያሉ ተቋማት እንደሚገልጹት፣ በሳዑዲ ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ዜጎቻችን ለግርፋት፣ ለረሃብና ለከፋ በሽታ ተጋልጠዋል። ሳዑዲ ለዓመታት የጉልበት ሥራዋን ሲያከናውኑ የነበሩ ሰራተኞችን እንደ ወንጀለኛ ቆጥራ፣ ንብረታቸውንና ካሳቸውን ሳትሰጥ በባዶ እጃቸው ማባረሯ፣ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ያላትን ንቀት የሚያሳይ ነው። ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መድረክ ሳዑዲን በግልጽ እንድትወቅስ ቢገፋፋም፣ መንግስት ግን ዜጎችን በማውጣት ተግባር ላይ ብቻ ማተኮሩን መርጧል።
ታዋቂው ሶሺዮሎጂስት ኤሚል ደርካይም አንድ ግለሰብ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ትስስር ሲላላ ለቀውስ ይጋለጣል ይላል። ተመላሾቹ ወደ ሀገር ሲገቡ የሚደረግላቸው አቀባበል ከምግብና ከትራንስፖርት የዘለለ መሆን አለበት። ለወራት በእስር ቤት የቆዩ ወንዶች የ"ማንነት ቀውስ" (Identity Crisis) ያጋጥማቸዋል።
በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ወንድ "ቤተሰብን የማስተዳደር" ትልቅ ሸክም ያለበት በመሆኑ፣ ባዶ እጁን የተመለሰ ስደተኛ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚሰጠው ቦታ ተስፋ እንዲቆርጥና ዳግም ለከፋ ስደት እንዲጋለጥ ያደርገዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት ከሌሎች እንደ ፊሊፒንስና ባንግላዴሽ ካሉ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር በፈጣን ምላሽ ሰጪነቱ (Emergency Response) የሚደነቅ ነው። ሆኖም፣ እነዚህ ሀገራት ከሳዑዲ ጋር ያላቸው ግንኙነት በድርድር ላይ የተመሰረተ ነው። ፊሊፒንስ ዜጎቿን ከማውጣት ባለፈ የሳዑዲ መንግስት ሰብዓዊ አያያዝን እንዲያሻሽል የጉልበት ሥራ ልውውጥን እስከማገድ ትደርሳለች። የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቋም ግን በብዛት "ተቀባይ" ላይ ያተኮረ በመሆኑ፣ በሳዑዲ ውስጥ የሚቀሩ ዜጎች አሁንም ለተመሳሳይ እንግልት ተጋላጭ ሆነው እንዲቀጥሉ አድርጓቸዋል።
በሳምንቱ ውስጥ የተመለሱት 35 ታዳጊዎች ታሪክ የሚዘገንን ነው። እነዚህ ህፃናት በደላሎች ተታልለው በየመን በረሃዎች አልፈው ሳዑዲ ቢገቡም፣ ያገኙት ግን የብረት አጥርና የወታደር ዱላ ነው። ሶሺዮሎጂያዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በእንዲህ ያለ እድሜ ላይ የሚደርስ የስነ-ልቦና ጥቃት ህፃናቱን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ "ማህበራዊ መገለል" (Social Alienation) ይዳርጋቸዋል። መንግስት እነዚህን ህፃናት ከቤተሰብ ጋር ከመቀላቀል ባለፈ፣ ልዩ የትምህርትና የስነ-ልቦና ማገገሚያ ፕሮግራም ካላዘጋጀላቸው የስደት አዙሪቱ ቀጣይ ሰለባ መሆናቸው አይቀሬ ነው።
ዜጎችን መመለስ የአንድ ወገን ስኬት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም። በሳዑዲ በኩል ያለው ግልፅነት የጎደለው አሰራርና ዜጎችን በጅምላ የማሳደድ (Mass Deportation) ፖሊሲ፣ ሂደቱን እጅግ አስቸጋሪና ውድ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ዜጎቿን ለመመለስ የምታወጣው ከፍተኛ በጀት፣ የሳዑዲ መንግስት በስደተኞች አያያዝ ላይ ያለበትን ክፍተት የሚሸፍንለት ይመስላል። ሳዑዲ ዓረቢያ ለዓመታት በኢትዮጵያውያን የጉልበት ሥራ ስትጠቀም ቆይታ፣ አሁን ግን ያለምንም ሰብዓዊ ርህራሄ በጅምላ ማባረሯ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው።
50 ሺህ ዜጎችን ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል ትልቅ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና አለው። ሶሺዮሎጂስቱ ማክስ ዌበር ስራና ስነ-ምግባር ለአንድ ሀገር እድገት ያላቸውን ፋይዳ ይገልጻል። ተመላሾቹ በሳዑዲ ያዩት ስቃይ ለስራ ያላቸውን ተነሳሽነትና በሀገራቸው ላይ ያላቸውን እምነት ሊሸረሽረው ይችላል። መንግስት እነዚህን ዜጎች ወደ ምርታማ የሰው ኃይል ለመቀየር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በር ካልከፈተ፣ ሂደቱ "ከባዕድ እስር ቤት ወደ ሀገር ውስጥ ስቃይ" መሸጋገር ብቻ ይሆናል።
መንግስት ዜጎችን መመለሱን እንደ ድል ቢቆጥረውም፣ ከጀርባው ያለው ቁስል ግን ገና አልደረቀም። "49 ሺህ 856 ዜጎች ተመለሱ" የሚለው ዜና ከቁጥር በስተጀርባ ያሉትን ሺዎች የሚቆጠሩ የተሰበሩ ልቦችንና የፈረሱ ቤተሰቦችን አይገልጽም። ሶሺዮሎጂያዊ እይታ የሚያሳስበው፣ ከተመለሱት ውስጥ ስንቱ በዘላቂነት ተቋቋሙ? የሚለው ጥያቄ ነው። ያለ ቀጣይነት ያለው የክትትል ስርአት የሚደረግ የመመለስ ሂደት፣ ችግሩን ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ ከማዛወር ባለፈ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን አይችልም።
በመንግስትና በአጋር አካላት መካከል ያለው ቅንጅትም ቢሆን የበለጠ መጠናከር ይኖርበታል። ዜጎችን የመመለሱ ስራ የአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም። በሳዑዲ በኩል ያለው ግልፅነት የጎደለው አሰራርና ዜጎችን በዘፈቀደ ማሰር፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ስራውን ይበልጥ ከባድ እና ውድ እንዲሆንበት አድርጎታል። ዛሬ በአውሮፕላን የወረዱት ወጣቶች፣ ነገ ዳግም በየመን በረሃና በሳዑዲ ድንበር ላይ በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ላለማየታችን ምንም ዋስትና የለንም።
ሚዲያዎች ተመላሾችን የሚያሳዩበት መንገድ ብዙ ጊዜ "ለጋሽ" እና "ተረጂ" በሚል እይታ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ደግሞ በተመላሾቹ ላይ የበታችነት ስሜት ይፈጥራል። ሶሺዮሎጂያዊ እይታ የሚያሳስበው፣ ሚዲያዎች የሳዑዲን ግፍ በማጋለጥ ረገድ ደካማ መሆናቸውን ነው። የዜጎች ክብር የሚጠበቀው በድንበር መሻገር ሳይሆን፣ በሀገር ውስጥ በሚገነባ ማህበራዊ ፍትህ እና በውጭ ሀገር በሚደረግ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ነው። ዛሬ የምናየው እምባ ነገ በሳዑዲ እስር ቤቶች እንዳይደገም፣ ሳዑዲን ተጠያቂ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል።

የፌደራል ፖሊስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ፡ ዘመናዊነት ወይስ አዲስ የቁጥጥር ፈተና?
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሽከርካሪዎቹን የሰሌዳ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል መሠረተ-ልማት እንደሚቀይር ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ በተቋሙ ዘመናዊነት ላይ ትልቅ ተስፋ የጣለ ቢሆንም፣ ከጥቅሞቹ ጎን ለጎን ሊታሰቡ የሚገቡ ነጥቦችንም ይዟል።
✅ የለውጡ ፋይዳዎች :
ተጠያቂነት : ሰሌዳዎቹ ከማዕከላዊ ዳታቤዝ ጋር በመገናኘታቸው የፖሊስ አባላት ተሽከርካሪን ለግል ጥቅም ወይም ከሥነ-ምግባር ውጭ እንዳይጠቀሙ የላቀ ቁጥጥር ይፈጥራል።
ደህንነት : በሕገ-ወጥ መንገድ የማይባዙ መሆናቸው፣ በፖሊስ ስም የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችንና ወንጀሎችን ከወዲሁ ይከላከላል።
ውጤታማነት: እንደ ዱባይና እንግሊዝ ባሉ ሀገራት እንደሚታየው፣ ቴክኖሎጂው ፖሊስ ለድንገተኛ አደጋዎች የሚሰጠውን ምላሽ (Response Time) ያፈጥነዋል።
⚠️ ሊታሰቡ የሚገቡ ተግዳሮቶች :
የመረጃ ደህንነት : ሁሉም መረጃዎች ዲጂታል መሆናቸው ሲስተሙ ለጠላፊዎች (Hackers) እንዳይጋለጥ ከፍተኛ ጥበቃን ይጠይቃል።
የሰው ኃይል ብቃት: ቴክኖሎጂው መኖሩ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ፣ ሲስተሙን የሚረዱና የሚያስተዳድሩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በበቂ ሁኔታ መኖራቸው ለስኬቱ ወሳኝ ነው።
ቀጣይነት: የዲጂታል ሲስተሞች የረጅም ጊዜ የጥገናና የማሻሻያ (Updates) በጀትና የቴክኒክ ድጋፍ የግድ ይላቸዋል።
💡 የፖሊስ ምሁራን ምን ይላሉ?
ምሁራን እንደሚሉት "ፍትህ መከናወን ብቻ ሳይሆን በግልጽ መታየትም አለበት።" ይህ የሰሌዳ ለውጥ ፖሊስን ለሕዝብ ግልጽና ተጠያቂ ለማድረግ የሚረዳ ቢሆንም፣ ውጤታማነቱ የሚለካው በተግባር ላይ በሚያሳየው ተጨባጭ ለውጥ ብቻ እንደሆነ ያስረዳሉ።

9 months ago
"እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል አይደለም፤ አሳዝኖናል!" - ዋዜማ ሬዲዮ
* "ክሱን ለተደራሲዎች እና ለታዛቢዎች የህሊና ፍርድ እንተዋለን"
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዋዜማ ሬዲዮን የሥራ ፈቃድ መመለሱን ተከትሎ፤ ጣቢያው በሰጠው ምላሽ በውሳኔው ማዘኑን ገልጿል።
ዋዜማ በመግለጫው ምን አለ?
1️⃣ ስለ ውሳኔው፡
ባለሥልጣኑ ባዘዘን መሰረት ፈቃዱን ብንመልስም፤ "እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል ነው ብለን አናምንም፤ አሳዝኖናልም" ብሏል።
2️⃣ ስለ ክሱ፡
ሀገርን ጥቅም ጎድቷል፣ ስነ-ምግባር ጥሷል ተብሎ ለቀረበበት ክስ፤ "ለኢትዮጵያ ሚዲያ ተደራሲዎች እና ታዛቢዎች የህሊና ፍርድ እንተዋለን" በማለት ምላሽ ሰጥቷል።
3️⃣ ቀጣይ እርምጃ፡
ጉዳዩን መርምሮ አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንደሚሰጥ እና ሌሎች ህጋዊ አማራጮችንም እንደሚከተል ጠቁሟል።
የባለሥልጣኑ ምክንያት ምን ነበር?
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በበኩሉ፤ ሚዲያው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ፣ ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው እና ሁከት ቀስቃሽ ዘገባዎችን በመስራቱ እንዲሁም የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ባለመቀበሉ እርምጃውን መውሰዱን መግለጹ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#wazemaradio #mediaauthority #response #ethiopia #pressfreedom #newsupdate

Sponsored by
Surafel
10 months ago
የዱባይ መንግስት ይፋዊ የስራ ማስታወቂያ ፖርታል dubaicareers.ae በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ባሉ ክፍት የስራ መደቦች ላይ ለማንኛውም ሀገር ዜግነት ላላቸው አመልካቾች ክፍት የሆኑ ማስታወቂያዎችን አውጥቷል።
ከላይ በተጠቀሰው ሊንክ በመግባት ማመልከት ትችላላቹ።
አንዳንዶቹ የስራ መደቦች እስከ 40,000 የኤምሬትስ ድርሃም ወርሃዊ ደሞዝ አቅርበዋል።
ከወጡት ስራዎች መሀል;
1. Housing Supervisor
Company: Dubai Foundation for Women and Children
Focus: Manage client housing, orientation, medical needs, room allocation and recreational activities for abused women and children.
Qualifications: Secondary school, experience in medical/hospitality services.
Category: Social Care
Salary: AED 10,000
2. Specialist - Digital Services Development
Company: Roads and Transport Authority (RTA)
Focus: Digital Services Project Coordination, System Integration, UAX Improvement, Performance Monitoring and Compliance with IT Governance.
Qualifications: Bachelor's Degree in IT/Computer Science, 5+ years of experience.
Department: Electrical Engineering/Digital Services.
Salary: Unspecified
3. Engineer - Bus Depot (RTA)
Focus: Oversee depot operations including fuel, maintenance, bus readiness, health and safety and budget oversight.
Qualifications: Bachelor's degree in Mechanical/Industrial Engineering.
Category: Administration
Salary: Unspecified
4. Senior Site Engineer
Company: Mada Media
Focus: Billboard and Signage project supervision, technical plan review, compliance testing, reporting and coordination with internal/external entities.
Qualifications: Bachelor's degree in Civil Engineering, 5-7 years of experience
Category: Civil Engineering.
Salary; AED 30,001-40,000
5. AV Editor
Company: Dubai Government Media Office
Focus: Create and edit video/photo content for social media, events and news; support media production projects and partnerships.
Qualifications: Bachelor's degree in film/video production or visual communication, 3+ years of experience, Adobe/Final Cut skills.
Category: Media
Salary: AED 10,001-20,000
6. Emergency Medical Technician (EMT) - DCAS
Focus: Pre-hospital emergency care, patient management, ambulance readiness and field support.
Qualifications: EMS Diploma or Nursing Degree, DCAS Licensed, BLS and Trauma Certification, 2-3 years of relevant experience.
Category: Emergency Medical
Salary: AED 10,001-20,000
7. Senior Engineer - Bus Depot

Focus: Leading depot operations, ensuring bus readiness, managing maintenance, HSE compliance, crisis response, KPI analysis and technical improvements.
Qualifications: Graduate in Mechanical/Industrial/Electrical/Civil Engineering, 2-5 years of experience.
Category: Civil Engineering
Salary: Unspecified
8. Lead Specialist - HR Business Affairs

Focus: Manage HR projects, performance monitoring, contracts, audits, reporting and strategic HR support across the department.
Qualifications: Graduate in Business/HR, 11+ years of experience, strong leadership and analytical skills.
Department: Human Resources
Salary: Unspecified
9. Systems and Applications Development Specialist (Hyperion/EPM)
Company: Dubai Department of Finance
Focus: Developing and improving central financial systems, implementing IT policies, monitoring projects and optimizing system performance.
Qualifications: Bachelor's degree in IT or related field, 8+ years of experience (4+ for Masters).
Category: IT
Salary: AED 20,001-30,000
10. Specialist - Innovation & Leadership

Focus: Innovation Lab management, research and partnership planning, excellence program support and leadership project oversight.
Qualifications: Bachelor's degree in Business/Management (Master's degree preferred), 14+ years of experience, EFQM certification, ISO 9001, Six Sigma preferred.
Department: Organizational Performance and Development

1 year ago
ጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ስደተኞች ተጨናንቃለች
• ከመጋቢት ጀምሮ 50 ሺ ስደተኞች ገብተዋል
#ethiopia | በደቡብ ሱዳን መንግሥትና በተቃዋሚዎቹ ኃይላት መካከል የሚደረገዉን ጦርነት ሽሽት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ክልል መግባታቸዉን የክልሉ ባለሥልጣናትና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታወቁ።
የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናት ለዶይቸ ቬለ እንደተናገሩት፤ ካለፈዉ መጋቢት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር 50 ሺ የሚደርስ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከደቡብ ሱዳን የተፈናቀሉ ከ380ሺ በላይ ሥደተኞች ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሰፈሩ ይታወቃል፡፡
“ለስደተኞቹ በቂ ምግብ እየቀረበላቸው አይደለም” ያሉት የዋንታዋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋትዊች ቡዝ፤ ህብረተሰቡ ያለውን እያካፈላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ 50ሺህ ያህል ስደተኞች ማታርና ሙን በተባሉ የወረዳው አካባቢዎች እንደሚኖሩም አስተዳዳሪው ጠቁመዋል፡፡
በዋናነት ሴቶችና ህፃናት የሚበዙባቸው ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ ጋምቤላ ክልል፣ ዋንታዋ ወረዳ መግባታቸውን ዲደብሊው የተመድ የስደተኞች ኮሚሽንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ስደተኞቹ በድንገት አካባቢያቸውን በመልቀቃቸው ለምግብ እጥረት፣ ለህክምና እጦት፣ ለመጠለያና ለሌሎች ችግሮች መጋለጣቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፤ በዚህ ሳምንት ማዕከላዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፈንድ (Central Emergency Response Fund (CERF)) ከተባለ ድርጅት፣ 3 ሚሊዮን ዶላር ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች፣ ለነፍስ አድንና ስደተኞቹ ለሚኖሩባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጭምር፣ ለጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት የሚውል ገንዘብ መመደቡ ታውቋል፡፡
አዲስ አድማስ

Comments