8 days ago
አሜሪካን ያስደነገጠው የጋና መንግስት ውሳኔ!
#ethiopia | የጋና መንግሥት ከወደ ዋሽንግተን የቀረበለትን የ109 ሚሊዮን ዶላር የጤና ድጋፍ ስምምነት "ብሔራዊ ክብርንና ሉዓላዊነትን ይነካል" ሲል ውድቅ አደረገ።
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ከአሜሪካ የጤና ድጋፍ ጀርባ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች "የሚያዋርዱ እና የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ናቸው" ብላለች።
በዚህም የቀረበላትን የ5 ዓመት ዕቅድ እንደማትቀበለው አስታውቃለች።
የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን ማሃማ ካቢኔያቸው ስምምነቱን ውድቅ ማድረጉን ሲገልጹ ለአሜሪካ እጅ ላለመስጠት ምክንያት የሆኑትን ዋና ዋና ነጥቦች ይፋ አድርገዋል።
ስምምነቱ ጋና አጠቃላይ የዜጎቿን የሕክምና መረጃዎች ለዋሽንግተን እንድታስረክብ የሚያስገድድ አንቀጽ ይዟል።
አሜሪካ በዚሁ ፕሮግራም ሥር ወደ ጋና የምታስገባቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶች የጋና ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዳይመረምርና እንዳይፈትሽ የሚከለክል አ አሰራር ተካቶበታል ብለዋል።
አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ብትገልጽም ጋና ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የራሷን በጀት አውጥታ እንድትመድብ መጠየቋ ቅሬታን ፈጥሯል።
ፕሬዚዳንት ማሃማ ሁኔታውን "አዋራጅ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን ጋና ይህ ድጋፍ ቢቀርባትም በራሷ አቅም መቆም እንደምትችል ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው በአክራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በበኩሉ ውዥንብር መፈጠሩን ጠቅሷል።
ኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ የሕመምተኞችን ግላዊ ማንነት የሚያሳይ መረጃ ሳይሆን የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመለካት የሚያግዝ አጠቃላይ የጤና መረጃ ብቻ መሆኑን አስረድቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #ghana #presidentmahama #ghanaus #healthfunding #nationalsovereignty #dataprivacy #biosecurity

20 days ago
የባሕር በር ጥያቄያችን እውነታና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ
******************
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ሀገራችን ብቻዋን የምታቀነቅነው አጀንዳ መሆኑ ቀርቶ አሁን ላይ በርካታ የዓለም ሀገራት ጥያቄው በታሪካዊ፣ ሕጋዊ እና ኢኮኖሚያዊ እውነታዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን እየተገነዘቡት ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ለዘመናት ፍትህ ተነፍጓት ያለ ባሕር በር መቆየቷ በኢኮኖሚ ዕድገቷ እና በጂኦፖለቲካዊ አቅሟ ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ እያደረገችው ያለው ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና ድጋፍ ነው።
የኢትዮጵያ ፍላጎት የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፋ የኃይል አካሄድ ሳይሆን በጋራ ተጠቃሚነት እና በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ ማዕቀፎች ላይ የተመሠረተ ታሪካዊ ስህተቶችን በዲፕሎማያዊ መንገድ የማስተካከል መሆኑን አጋር ሀገራት ተረድተውታል።
ሀገራችን በምስራቅ አፍሪካ በሰላም ማስከበር እና በኢኮኖሚ አቅሟ ባላት ቁልፍ ሚና ልታገኘው የሚገባትን የባሕር በር በሰላማዊ መንገድ መጠየቋ ተቀባይነት አግኝቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የንግድ፣ የሎጂስቲክስ እና የኢንቨስትመንት ፍሰት ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ ለአህጉራዊ ትስስር እና ለዘላቂ ሰላም ጠንካራ መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል እየታመነበት ነው።
ኢትዮጵያ በሰከነ ስትራቴጂያዊ ዲፕሎማሲ በመታገዝ የባሕር በር ጥያቄዋን ከሁለትዮሽ ውይይት አልፎ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ ወደሚያገኝበት አዲስ ምዕራፍ አድርሳዋለች።
ሀገራችን ለዘመናት ከናፈቀችው የባሕር በሯ ጋር በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ሰላማዊ መንገድ ልትገናኝ ከምንጊዜውም በላይ እየተቃረበች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ የውጭ አጋሮቻችንን ድጋፍ ከውስጥ አንድነታችን ጋር አስተስስሮ በጋራ መቆም የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
በሃና ምንዳሁን
#hornofafrica #ethiopia #seaaccess #redsea #nationalsovereignty #diplomacy #ebc #ebcdotstream

1 month ago
ትውልድ ያጣውን ትውልድ የሚያስመልሰው ታሪካዊው የባሕር በራችን
****************
የባሕር በር ማግኘት ልዩ ልዩ የጂኦ-ፖለቲካዊ ማደናቀፍ ሂደቶችና ሴራዎች ቢተገበሩበትም አዲሱ ትውልድ ዓይኑን ሊነቅልበት ያልቻለ፣ ለሀገር የኢኮኖሚ ደም ሥር፣ ለፖለቲካ ነፃነት ማረጋገጫና አገራዊ ክብርን መልሶ ለማንገሥ የሚደረግ ታላቅ ህልም ነው።
የቀደሙት ትውልዶች በጂኦ-ፖለቲካዊ ሴራዎችና በወቅቱ በነበሩ ውስብስብ ሀገራዊ ድክመቶች ምክንያት ካጧቸው ታላላቅ አገራዊ ሀብቶች መካከል የባሕር በር ተጠቃሚነትና የባሕር ኃይል ባለቤትነት ዋነኞቹ ነበሩ።
ይህ የታሪክ ስብራት በሀገራች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫናን ከማስከተሉ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች በከፍተኛ ፈተና ውስጥ ጥሎት ቆይቷል።
የአሁኑ ትውልድ ደግሞ ይህንን የታሪክ ጠባሳ የማረም፣ የሀገሩን ዘላቂ መፍትሔ በራሱ ትከሻ ላይ የመሸከም እና የነገዋን ኢትዮጵያ በጽኑ መደላደል ላይ የመገንባት ታሪካዊ ኃላፊነት ወስዷል።
ይህ አገራዊ ጥያቄ ቀለል ያለ የፍላጎት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ህልውና እና የመጻኢ ዕድል መወሰኛ መሆኑን ትውልዱ ጠንቅቆ ይረዳዋል።
የባሕር በር ማግኘት ማለት ለንግድ ልውውጥ የሚወጣውን ከፍተኛ የቢሊዮን ዶላሮች የወደብ ኪራይ ማስቀረት፣ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴን ማፋጠን፣ የፍጆታ ዕቃዎችን ዋጋ በመቀነስ የዜጎችን ሕይወት ማቃለል እና የአገሪቱራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በተግባር ማረጋገጥ ማለት ነው።
በቀይ ባሕርና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ፣ ተደማጭና ባለሙሉ ባለቤት ሀገር ሆኖ ለመቀጠል የራስ የሆነ የባሕር በር እና ዘመናዊ የባሕር ኃይል መኖሩ ወሳኝና አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
ትውልዱ ያጣውን የባሕር በር በጥበብ፣ በበሰለ ዲፕሎማሲና በጽኑ አገራዊ አንድነት የመመለስ ጥረት የቀደሙ አባቶችን አደራ የማስከበርና ለመጪው ትውልድ የበለፀገችና የተከበረች ሀገር የማስረከብ ታላቅ ራዕይ ነው።
ይህ ትውልድ እውነታውን፣ ሕጋዊ መብቱንና የታሪክ እዳውን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ፣ የባሕር በር ጥያቄ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቀለበስና የማይቆም ታሪካዊ አገራዊ ጉዞ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
በልዩ እሸቱ
#ethiopያSeaOutlet #redseadiplomacy #nationalsovereignty #ethiopianprosperity #hornofafricaintegration

2 months ago
የከሰረው ቡድን የስልጣን ጥማት
#ethiopianbroadcastingcorporation #peaceandsecurity #nationalsovereignty #tigray
Sponsored by
Surafel
Comments