በቦንጋ ከተማ ለወጣት ስፖርተኛ ንቃተ ህሊና የመሬትና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ድብልቅ ማርሻል አርት ወይም MMA ውድድር በማስተዋወቅ ስሙን ላስጠራው ወጣት ስፖርተኛ ንቃተ ህሊና ዮሐንስ ምስክር በቦንጋ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል::
ስፖርተኛው ወደ ከተማዋ ሲገባ የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል::
በእለቱ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ስፖርተኛው ዞኑንና ሀገሩን በስፖርቱ ዘርፍ በማስጠራቱ ምስጋና አቅርበው የዞኑ አስተዳደር ለንቃተ ህሊና 300 ሺህ ብር እንዲሁም ለአዘጋጁና ለአሰልጣኙ እያንዳንዳቸው 100 ሺህ ብር በድምሩ የ500 ሺህ ብር ስጦታ ማበርከታቸውን ገልጸዋል::
በተመሳሳይ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ተክለዓብ ቡሎ ስፖርተኛው በሀገራችን አዲስ የውድድር ምዕራፍ በመክፈቱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ 500 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ለስፖርተኛው ንቃተ ህሊና በስጦታ መስጠቱን አብስረዋል::
ከንቲባው አክለውም የከተማው ህዝብ ሁልጊዜም ከስፖርተኛው ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል::
አሰልጣኝ ማስተር ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው ለስፖርተኛው ያላቸውን አድናቆት ገልጸው በቀጣይ ንቃተ ህሊናን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ሌሎች የአካባቢውን ወጣቶች በዘርፉ ለማሰልጠን ቃል ገብተዋል::
ስፖርተኛ ንቃተ ህሊናም ለተደረገለት የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቦ ይህ ስኬት ገና ጅምር መሆኑንና በቀጣይ በበለጠ ስራ ሀገሩንና ህዝቡን እንደሚያኮራ ተናግሯል::
በመጨረሻም በወጣት ሰዓሊ አብርሃም ተስፋዬ የተዘጋጀ ውብ የስነ ጥበብ ስራ ለስፖርተኛውና ለአሰልጣኙ በስጦታ ተበርክቶላቸዋል::
ፎቶ÷ በሠለሞን ተስፋዬ
የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
#bonga #kaffa #mma #ethiopiansport #nikat_hilina #martialarts #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago