6 months ago
ጎግል የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮውዘራቸውን በአፋጣኝ እንዲያዘምኑ አሳሰበ።
ጎግል በክሮም ብሮውዘር ላይ የተገኘን እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት ለመጠገን አስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያ ማውጣቱን አስታወቀ።
ይህ የጥቃት ተጋላጭነት "CVE-2026-2441" የተሰየመ ሲሆን፣ በጎርጎሮሳውያኑ 2026 ዓ/ም ክፍተት መሙያ የተደረገለት የመጀመሪያው ከፍተኛ የጥቃት ተጋላጭነት ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት "Use-after-free" በሚባል የስህተት ዓይነት የተፈጠረ ነው።
የመረጃ መንታፊዎች (Hackers) ይህንን ክፍተት በመጠቀም የብሮውዘሩን ሲስተም ማሰናከል፣ መረጃዎችን መመንተፍ፣ ሌሎች ያልተፈለጉ ትዕዛዞችን በኮምፒውተራችሁ ላይ ማከናወን እንደሚችሉ ጎግል ገልጿል።
ጎግል እንዳረጋገጠው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ጥቃት የሚያደርሱ አካላት በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብሏል።
ምን ማድረግ ይገባል?
ተጠቃሚዎች ጥቃቱን ለመከላከል ጎግል የለቀቃቸውን የሚከተሉትን የክሮም ብሮውዘር ስሪቶች #versions እንዲጠቀሙ ይመከራል፦
-ለዊንዶውስ #windows ) እና ለማክ #macos ተጠቃሚዎች፦ 145.0.7632.75/76
-ለሊኑክስ #linux ተጠቃሚዎች፦ 144.0.7559.75
#update እንዴት መተግበር ይቻላል?
1. በክሮም ብሮውዘርዎ ላይ በቀኝ በኩል ያሉትን ሦስት ነጥቦች ይጫኑ።
2. #help የሚለውን መርጠው #about_google_chrome የሚለውን ይጫኑ።
3. ብሮውዘሩ አዲስ ዝማኔ ካለ በራሱ ይፈልጋል፤ ፍለጋውን እንደጨረሰም #relaunch የሚለውን በመጫን ብሮውዘሩን እንደገና ያስጀምሩት። #insa
seledadotio

11 months ago
ጉግል በክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ ላይ ለተከሰተዉ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ማስተካከያ ለቀቀ
#ethiopia | ጉግል በክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ #browser ላይ የታዩና ቀድሞ ያልተለዩ #zero_day ተጋላጭነቶችን የሚቀርፍ የደህንነት ማሻሻያዎችን ለቀቀ፡፡
ይህ ክፍተት (CVE-2025-10585) አደገኛ ከሚባሉ ክፍተቶች መካከል የሚመደብ እንደሆነ ጎግል ገልጿል፡፡ እንዲህ አይነት ቀድሞ ያልተለዩ (zero-day) ተጋላጭነቶች በፈረንጆቹ 2025 ብቻ በክሮም ላይ ለስድስተኛ ጊዜ እንደተከሰቱ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ አደጋ ስጋት ለመጠበቅ የጎግል ክሮም የመረጃ ማፈላልጊያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው ስሪት መሰረት ማዘመን እንደሚያስፈልግ ጉግል አሳስቧል፡፡
ዊንዶውስ #windows እና ማክ ኦኤስ #macos ምርት ተጠቃሚዎች ወደ ክሮም ስሪት: 140.0.7339.185/.186 ማዘመን እንዲሁም የሊነክስ #linux ምርት ተጠቃሚዎች ደግሞ ወደ ክሮም ስሪት፡140.0.7339.185 ማዘመን ይጠበቅባቸዋል።
በተጨማሪም እንደ #microsoft_edge፣ #brave፣ #opera እና #vivaldi ያሉ ሌሎች በክሮሚየም #chromium ላይ ለተመሰረቱ የመረጃ ማፈላልጊያዎች ላይ የክፍተት መሙያ መለቀቁንና ተጠቃሚዎች በፍጥነት እንዲያዘመኑም ኩባንያው መክሯል።
እርስዎም ወደ ክሮም የመረጃ ማፈላልጊያ በመሄድ ክሮም ምርትዎን በማዘመን ሊደርስብዎት የሚችለዉን የጥቃት ተገላጭነት ይድፈኑ።#insa

Comments