Logo
SeledaPost
ጎግል የክሮም ተጠቃሚዎች ብሮውዘራቸውን በአፋጣኝ እንዲያዘምኑ አሳሰበ።

ጎግል በክሮም ብሮውዘር ላይ የተገኘን እጅግ አደገኛ የሆነ የጥቃት ተጋላጭነት ለመጠገን አስቸኳይ የደህንነት ማሻሻያ ማውጣቱን አስታወቀ።

ይህ የጥቃት ተጋላጭነት "CVE-2026-2441" የተሰየመ ሲሆን፣ በጎርጎሮሳውያኑ 2026 ዓ/ም ክፍተት መሙያ የተደረገለት የመጀመሪያው ከፍተኛ የጥቃት ተጋላጭነት ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ የጥቃት ተጋላጭነት ክፍተት "Use-after-free" በሚባል የስህተት ዓይነት የተፈጠረ ነው።

የመረጃ መንታፊዎች (Hackers) ይህንን ክፍተት በመጠቀም የብሮውዘሩን ሲስተም ማሰናከል፣ መረጃዎችን መመንተፍ፣ ሌሎች ያልተፈለጉ ትዕዛዞችን በኮምፒውተራችሁ ላይ ማከናወን እንደሚችሉ ጎግል ገልጿል።

ጎግል እንዳረጋገጠው ይህንን ክፍተት በመጠቀም ጥቃት የሚያደርሱ አካላት በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብሏል።

ምን ማድረግ ይገባል?

ተጠቃሚዎች ጥቃቱን ለመከላከል ጎግል የለቀቃቸውን የሚከተሉትን የክሮም ብሮውዘር ስሪቶች #versions እንዲጠቀሙ ይመከራል፦
-ለዊንዶውስ #windows ) እና ለማክ #macos ተጠቃሚዎች፦ 145.0.7632.75/76

-ለሊኑክስ #linux ተጠቃሚዎች፦ 144.0.7559.75

#update እንዴት መተግበር ይቻላል?

1. በክሮም ብሮውዘርዎ ላይ በቀኝ በኩል ያሉትን ሦስት ነጥቦች ይጫኑ።
2. #help የሚለውን መርጠው #about_google_chrome የሚለውን ይጫኑ።
3. ብሮውዘሩ አዲስ ዝማኔ ካለ በራሱ ይፈልጋል፤ ፍለጋውን እንደጨረሰም #relaunch የሚለውን በመጫን ብሮውዘሩን እንደገና ያስጀምሩት። #insa

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.