16 days ago
📢የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት🎯
ነገ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-
✅ከጠዋቱ 1:00 – 11:00
👉ገርጅ መብራት ሃይል፣ ጃክሮስ፣ የረር ሆስፒታል፣ ጎሮ፣ ICMC ሆስፒታል፣ እስኩል ኦፍ ቱሞሮ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ መሪ መስጅድ፣ ሳፋሪ እና ፉሪ፣ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2:00 – 9:30
👉ሆለታ፣ ህዳሴ፣ መናገሻ፣ ቡረዩ ከተማ አስተዳደር፣ ቡራዩ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2:00 – 6:00
👉ደብረ ብርሃን ከተማ ውሃ አቅርቦት፣ አልዩ አምባ፣ ሃኪም ግዛው ሆስፒታል፣አስራት ወ/ኢየሱስ ካምፓስ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2:00 – 12:00
👉መቀሌ ቀበሌ 18፣ ዲያስፖራ ሰፈር፣ ቀዳማይ ወያነ፣ ማጅክ ትምህርትቤት፣ ደብረ ዳሞ፣ አብርሃ ካስት፣ ሃውልቲ ሰማታት፣ DW ቢሮ፣ ፕላኔት ሆቴል እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2:30 – 10:30
👉ሱሉልታ 10 ኪሎ በከፊል፣ ዶሮ እርባታ፣ ቀንብሬ፣ አፍሪካ ልሕቀት ማዕከል፣ጭሮ ከተማ፣ኦዳቡልቱ ዩንቨርሲቲ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3:00 – 8:00
👉ቤተ መንግስት፣ ቴክስታይል፣ ሐሙሲት ወጪ መስመሮች እንዲሁም ከባህርዳር ቁጥር 1 እና ከወረታ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሃይል የሚያገኙ አካባቢዎች፣
✅እንዲሁም ከሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ ጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ንጋቱ 12፡00 ድረስ:-
👉ከሻሸመኔ ወደ አዳሚ ቱሉ የሚሄደው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
👉 በአሰላ፣ በአዳሚቱሉ፣ በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በቡኢ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Seledadotio

4 months ago
"የሲኦል በሮች የሚከፈቱት ለእናንተ ነው" - ኢራን
ኢራን የትራምፕን የ48 ሰዓት ማስጠንቀቂያ ቀነ ገደብ ውድቅ አድርጋለች።
የኢራን ጦር ማዕከላዊ እዝ (ICMC) አዛዥ ጄነራል አሊ አብዱላሂ አሊአባዲ የትራምፕን ማስጠንቀቂያ "ለሰላም ምንም እገዛ የሌለው" ሲሉ ተችተውታል።
አክለው፣ "በስሜት የተወሰነ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ የእብደት ድርጊት ነው" ብለውታል።
"ከመልዕክቱ ዋና ትርጉም እንዳየነው፣ የሲዖል በሮች የሚከፈቱት ለእናንተ ነው" በማለትም አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን እንድትከፍት ለሁለተኛ ጊዜ የ48 ሰዓት ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወቃል።
seledadotio

6 months ago
አይ ሲ ኤም ሲ በቱሉ ዲምቱ አዲስ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል በይፋ አስመረቀ
#ethiopia | ለረጅም ዓመታት በልብ ሕክምና ዘርፍ አገልግሎት የሰጠው አይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 (ቱሉ ዲምቱ) ያስገነባውን ዘመናዊ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም መርቆ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።
ይህ አዲስ ማዕከል በተለይ ለቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጨ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ሸገር ከተማ እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች ጥራት ያለው ሕክምና በቅርበት እንዲያገኙ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
ሆስፒታሉ የውስጥ ደዌ ሕክምናየማማከር እና የታካሚዎች ክትትል ዘመናዊ ምርመራ፣የISO እውቅና ያለው ላብራቶሪ፣ የራጅ እና አልትራሳውንድ አገልግሎት፣የድንገተኛ አደጋ ሰው ሠራሽ መተንፈሻና የነፍስ አድን መሣሪያዎች የተገጠመላቸው ዘመናዊ አምቡላንሶች እንዳሉት ተገልጿል።
በቅርቡ የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት እጥበት (Dialysis) አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቴን አጠናቅቃለሁ ብሏል።
እ.ኤ.አ በ2001 በትንሽ የልብ ክሊኒክነት ጉዞውን የጀመረው ተቋሙ፣ ዛሬ ላይ ከ3,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን በማቀፍ ወደ ትልቅ አጠቃላይ ሆስፒታል አድጓል። ሆስፒታሉ የካትላብ (Cath Lab) መሣሪያን ጨምሮ ዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #icmc #healthethiopia #tuludimtu #addisababa #medicalcenter #ethiopia #healthcare #አይሲኤምሲ #ጤና

የአይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) ሜዲካል ሴንተር አዲስ የሕክምና ማዕከል በቱሉ ዲምቱ በይፋ አስመረቀ
#fastmereja I አይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) ሜዲካል ሴንተር ለኅብረተሰቡ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በማስፋት፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 (ቱሉ ዲምቱ) ያስገነባውን አዲስ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ።
ይህ አዲስ ማዕከል መከፈቱ ለቱሉ ዲምቱ፣ ለኮዬ ፈጨ፣ ለአቃቂ ቃሊቲ፣ ለሸገር ከተማ እንዲሁም አጎራባች ለሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች የሕክምና ፍላጎት ትልቅ ምላሽ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
አይ ሲ ኤም ሲ እ.ኤ.አ በ2001 በትንሽ የልብ ክሊኒክነት ተመስርቶ፣ ደረጃ በደረጃ በማደግ አሁን የደረሰበት ደረጃ ደርሷል። አክሲዮን ማህበሩ ከ3,000 በላይ ባለአክስዮኖችን ያቀፈ ሲሆን ስመጥር የሕክምና ባለሙያዎችንና በርካታ የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።
በሆስፒታሉ የሚገኙ ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችን (ለምሳሌ የካትላብ መሣሪያ) እና የISO ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን የላብራቶሪ አገልግሎት በጋራ በመጠቀም የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል።
በማዕከሉ ውስጥ የውስጥ ደዌ ሕክምና የማማከርና የሕክምና አገልግሎት፣ የላብራቶሪ፣ የራጂ እና የአልትራ ሳውንድ ምርመራ፣ ሰው ሠራሽ መተንፈሻና የነፍስ አድን መሣሪያዎች የተገጠመላቸው ዘመናዊ አምቡላንሶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ፋርማሲ፣ በተጨማሪም ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የእናቶችና የሕፃናት ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት እጥበት (Dialysis) አገልግሎቶችን ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
አይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል የተገልጋዮችን አቅም ያገናዘበና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑ ተነግሯል።
#ጤና መረጃ

Sponsored by
Surafel
7 months ago
ታዋቂ ሰዎች ስለ ነጻነት ምን አሉ?
#ethiopia | በኢትዮጵያ የጥበብ ሰማይ ስር በፈገግታው ድምቀት፣ በትወናው ጥልቀትና በሰብአዊነቱ ርህራሄ ብዙዎችን ሲያስደምም የነበረው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ (ነፂ) ድንገተኛ ህልፈት፣ መላውን የሀገሪቱን ህዝብ በከባድ ድንጋጤና ሀዘን ውስጥ ዘፍቆታል። ይህ መርዶ እንደ ሰደድ እሳት ሲሰራጭ፣ ከሀገር መሪዎች እስከ ጥበብ ባለሙያዎች ድረስ ሁሉም "የኔ ንፁህ" እያሉ እንባቸውን አፍስሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአርቲስቱን ህልፈት ተከትሎ በሰጡት መግለጫ፣ ነፃነት በኪነ-ጥበቡ መስክ የነበረውን ጉልህ ሚና አስታውሰዋል። "አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገት በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በተለይም በ2016 ዓ.ም የሕዳሴ ግድብ አዲስ ዓመት መቀበያ ፕሮግራም ላይ የነበረውን ንቁ ተሳትፎና ህዝቡን ለማስደሰት የነበረውን ትጋት በታላቅ አክብሮት አንስተዋል።
በሌላ በኩል፣ የኢትዮጵያ የጥበብ ምልክት የሆነው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ የልብ ስብራቱን በገላጭ ቃላት አስፍሯል። "ውድ ወንድሜ ነፂ... እንዳልከው የማንቋቋመው የሚያሳምም ኀዘን ነው" በማለት የጀመረው ቴዲ፣ "እኛ ያሰብነውና ያቀድነው አልሆነም" ሲል የሰው ልጅ እቅድና የፈጣሪ ፈቃድ ስላላቸው ልዩነት በሀዘን ተቀኝቷል። ቴዲ አፍሮ ለነፃነት ነፍስ እረፍትን እየለመነ፣ "ፍቅር ያሸንፋል" በሚለው መሪ ቃሉ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ተመኝቷል።
የብቸኝነት ጉዞ እና ያልተሳካው ኑዛዜ
የነፃነት ህይወት ገና በልጅነቱ ነበር በትልቅ ፈተና የተጀመረው። እናትና አባቱን ገና በለጋነቱ አጥቶ በብቸኝነትና በናፍቆት ያደገው ነፃነት፣ የልጅነት እጦቱን በኪነ-ጥበብና በሰው ፍቅር ለመካስ የጣረ ታላቅ ሰው ነበር። ወላጆቹን ቢያጣም፣ እንደ እናትም እንደ አባትም ሆነው ያሳደጉትን አያቱን እጅግ ይወድና ያከብር ነበር።
ለቅርብ ወዳጆቹ ደጋግሞ የሚናገረው አንድ ልብ የሚነካ ኑዛዜ ነበረው፦ "ስሞት ከአያቴ አጠገብ አሌልቱ ጊዮርጊስ ቅበሩኝ" የሚል። ይህ ምኞቱ ከአፈር በታችም ቢሆን አብሯቸው የመሆን ጉጉቱን የሚያሳይ ነበር። የሚገርመውና ልብን የሚሰብረው ግን፣ ነፃነት ከመሞቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ወደ አሌልቱ ጊዮርጊስ ተጉዞ ቤተክርስቲያኑን ስለማደስና ስለ ልማት ስራዎች ሲመክር መቆየቱ ነው። ሞት በደጃፉ እንዳለ ሳያውቅ፣ ለአያቱ ጓሮና ለዘላለም እረፍቱ ሲዘጋጅ የቆየ ይመስላል። ሆኖም የሀገር ዕዳና የጥበብ ባለቤት በመሆኑ፣ ኑዛዜው ሳይፈጸም በቀብር ስነ-ስርዓቱ በታላቁ ስላሴ ካቴድራል እንዲሆን ተወስኗል።
የመጨረሻዎቹ ሰዓታት እና የመሪር ጩኸት ድምፆች
ያቺ ጥር 8 ቀን የጥበብ ቤተሰብን ያረገደች መርዶ ይዛ መጣች። ነፃነት ለወትሮው የስራ እንቅስቃሴው ለመውጣት እየተዘጋጀ፣ ልብሱን እየለባበሰ ሳለ ድንገተኛ ህመም ተሰማው። ወደ ጓደኛው ደውሎ "አልቻልኩም" ሲል የነገረው የመጨረሻ ቃሉ ነበር። ወደ ICMC ሆስፒታል በተደረገው አጣዳፊ ጉዞ ላይ ህመሙ እየበረታ ሄዶ፣ በምሳ ሰዓት ገደማ ያ ሁሉ ፈገግታ፣ ያ ሁሉ የጥበብ ሀብትና ያ ሁሉ የወደፊት ተስፋ ከዚህ ዓለም ተለየ።
ይህ መርዶ በስደት ለሚኖሩት ወዳጆቹ የፈጠረው ስቃይ ግን ከባድ ነበር። አርቲስት ሃና ዮሃንስ በባዕድ ሀገር ሆና የሰማችው መርዶ ውስጧን አቃጥሎታል። "ጎረቤቶቼ አብዳለች እንዳይሉኝ፣ መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ጮህኩ! አለቀስኩ!" ስትል የገለጸችው ስሜት፣ የብዙዎችን የልብ ስብራት ይወክላል። የፒያሳ ትዝታዎቻቸው፣ የአራት ኪሎ ሳቆቻቸውና በመድረክ ላይ የነበራቸው ውህደት ሁሉ በቅጽበት ትዝታ ብቻ ሆኑ።
ጋዜጠኛ መቅደስ ደበሳይም በተመሳሳይ የልብ ስብራት "የኔ ንፁህ ነፂዬ" ስትል ስትቀበር ያየችውን ህልም ለማመን ተቸግራለች። ከሁለት ዓመት በፊት ያጣችውን አርቲስት አስፋው መሸሻንና ነፃነትን እያነሳሳች፣ "በሁለት ዓመት ልዩነት እናንተን ማጣት አለመታደል ነው" ስትል የሀዘኗን ጥልቀት ገልጻለች። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌም ቢሆን "የማንቋቋመው የሚያሳምም ሀዘን" ሲል የቃለ አብን (የነፃነትን) ነፍስ ለፈጣሪ አደራ ሰጥቷል።
የጥበብ ቤተሰብ ስንብት
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ አርቲስት ማህደር አሰፋ፣ አብዱ ኪያር፣ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ሌሎችም በርካታ አርቲስቶች የገለጹት ሀዘን ነፃነት ምን ያህል የብዙዎች መሆኑን ያሳያል። ነፃነት ወርቅነህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተራ ተዋናይ አልነበረም። በ"የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራሙ እያንዳንዱ ቤት ገብቶ ደስታን የሚያድል፣ በፊልሞቹ ማህበረሰባዊ እውነታን በሳቅ የሚተርክ የቁም ነገር ሰው ነበር።
የአርቲስቱ የቀብር ስነ-ስርዓት እሁድ ጥር 10 ቀን በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲፈጸም፣ ከፖርትላንድ የምትመጣው ባለቤቱና ልጆቹ፣ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ ክብር ይሸኙታል። ምንም እንኳን የነፃነት ስጋ ወደ አፈር ቢመለስም፣ ያ ለጋስ ፈገግታውና ንፁህ ማንነቱ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም ህያው ሆኖ ይኖራል።
ነፃነት ወርቅነህ (ነፂ) ሆይ፤ በምድራዊ ህይወትህ እናትና አባትህን አተህ ብቸኝነት ቢሰማህም፣ ዛሬ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ እናትና አባት አልቅሶልሃል። ነፍስህ በአጸደ ገነት በሰላም ትረፍ!

የጥበብ ኮከቡ ነፃነት ወርቅነህ መጥለቅ
ከጠ/ሚ ዐብይ አህመድ እስከ ቴዲ አፍሮ የቀረበ የልብ ሰባሪ ስንብት
በኢትዮጵያ የጥበብ ሰማይ ስር በፈገግታው ድምቀት፣ በትወናው ጥልቀትና በሰብአዊነቱ ርህራሄ ብዙዎችን ሲያስደምም የነበረው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ (ነፂ) ድንገተኛ ህልፈት፣ መላውን የሀገሪቱን ህዝብ በከባድ ድንጋጤና ሀዘን ውስጥ ዘፍቆታል። ይህ መርዶ እንደ ሰደድ እሳት ሲሰራጭ፣ ከሀገር መሪዎች እስከ ጥበብ ባለሙያዎች ድረስ ሁሉም "የኔ ንፁህ" እያሉ እንባቸውን አፍስሰዋል።

Comments