6 months ago
አይ ሲ ኤም ሲ በቱሉ ዲምቱ አዲስ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል በይፋ አስመረቀ
#ethiopia | ለረጅም ዓመታት በልብ ሕክምና ዘርፍ አገልግሎት የሰጠው አይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 (ቱሉ ዲምቱ) ያስገነባውን ዘመናዊ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም መርቆ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።
ይህ አዲስ ማዕከል በተለይ ለቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጨ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ሸገር ከተማ እና በአቅራቢያው ለሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች ጥራት ያለው ሕክምና በቅርበት እንዲያገኙ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
ሆስፒታሉ የውስጥ ደዌ ሕክምናየማማከር እና የታካሚዎች ክትትል ዘመናዊ ምርመራ፣የISO እውቅና ያለው ላብራቶሪ፣ የራጅ እና አልትራሳውንድ አገልግሎት፣የድንገተኛ አደጋ ሰው ሠራሽ መተንፈሻና የነፍስ አድን መሣሪያዎች የተገጠመላቸው ዘመናዊ አምቡላንሶች እንዳሉት ተገልጿል።
በቅርቡ የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት እጥበት (Dialysis) አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቴን አጠናቅቃለሁ ብሏል።
እ.ኤ.አ በ2001 በትንሽ የልብ ክሊኒክነት ጉዞውን የጀመረው ተቋሙ፣ ዛሬ ላይ ከ3,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን በማቀፍ ወደ ትልቅ አጠቃላይ ሆስፒታል አድጓል። ሆስፒታሉ የካትላብ (Cath Lab) መሣሪያን ጨምሮ ዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #icmc #healthethiopia #tuludimtu #addisababa #medicalcenter #ethiopia #healthcare #አይሲኤምሲ #ጤና

Comments