የአይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) ሜዲካል ሴንተር አዲስ የሕክምና ማዕከል በቱሉ ዲምቱ በይፋ አስመረቀ
#fastmereja I አይ ሲ ኤም ሲ (ICMC) ሜዲካል ሴንተር ለኅብረተሰቡ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በማስፋት፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 (ቱሉ ዲምቱ) ያስገነባውን አዲስ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማዕከል ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስመረቀ።
ይህ አዲስ ማዕከል መከፈቱ ለቱሉ ዲምቱ፣ ለኮዬ ፈጨ፣ ለአቃቂ ቃሊቲ፣ ለሸገር ከተማ እንዲሁም አጎራባች ለሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች የሕክምና ፍላጎት ትልቅ ምላሽ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
አይ ሲ ኤም ሲ እ.ኤ.አ በ2001 በትንሽ የልብ ክሊኒክነት ተመስርቶ፣ ደረጃ በደረጃ በማደግ አሁን የደረሰበት ደረጃ ደርሷል። አክሲዮን ማህበሩ ከ3,000 በላይ ባለአክስዮኖችን ያቀፈ ሲሆን ስመጥር የሕክምና ባለሙያዎችንና በርካታ የልዩ ልዩ ሙያ ባለቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።
በሆስፒታሉ የሚገኙ ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችን (ለምሳሌ የካትላብ መሣሪያ) እና የISO ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን የላብራቶሪ አገልግሎት በጋራ በመጠቀም የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል።
በማዕከሉ ውስጥ የውስጥ ደዌ ሕክምና የማማከርና የሕክምና አገልግሎት፣ የላብራቶሪ፣ የራጂ እና የአልትራ ሳውንድ ምርመራ፣ ሰው ሠራሽ መተንፈሻና የነፍስ አድን መሣሪያዎች የተገጠመላቸው ዘመናዊ አምቡላንሶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ፋርማሲ፣ በተጨማሪም ሆስፒታሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የእናቶችና የሕፃናት ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት እጥበት (Dialysis) አገልግሎቶችን ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
አይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል የተገልጋዮችን አቅም ያገናዘበና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑ ተነግሯል።
#ጤና መረጃ

6 months ago