Logo
Getu Temesgen
የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018 በይፋ ተከፈተ

​#ethiopia | በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም "የአዋሽ ብር ፕሮ ፋሲካ ኤክስፖ 2018" በሚል ስያሜ የንግድ ትርኢትና ባዛር በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።

ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ኤክስፖ፣ ሸማቾችና ነጋዴዎች የበዓል ግብይታቸውን በአንድ ስፍራ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በቆይታውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ይሳተፍበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ዮሐንስ መርጊያ ባንኩ በኤክስፖው ወቅት ለሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዘመናዊና የተቀናጀ የባንክ አገልግሎትን በማዕከሉ ውስጥ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

​አዋሽ ባንክ በዚህ ዝግጅት ላይ "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" የተሰኘውን አዲስ የዲጂታል መተግበሪያ በይፋ ሥራ ላይ ያዋለ ሲሆን፣ ይህም አገልግሎት ማንኛውንም ዓይነት ኩነት የሚያዘጋጁ አካላት ቲኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ደህንነቱ የተጠበቀ መድረክ ነው።

መተግበሪያው የወረቀት ቲኬቶችን በQR ኮድ በመተካት ለዝግጅት አዘጋጆችና ለታዳሚዎች ዘመናዊና ምቹ አሠራርን ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ በኤክስፖው ላይ የሚታደሙ ሸማቾችም በባንኩ ዲጂታል መሠረተ ልማት በመታገዝ ፈጣን ግብይት እንዲፈጽሙ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።

በተጨማሪም "አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ" በመጠቀም ግብይት የሚፈጽሙ ደንበኞች የመኪና ዕድል ሽልማቶችን የሚያገኙበት አጋጣሚ የተመቻቸ ከመሆኑም በላይ፣ በ"አዋሽ ብር" ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች የ5 በመቶ ተመላሽ ማበረታቻ ተዘጋጅቶላቸዋል።

የዘንድሮውን ኤክስፖ አዋሽ ባንክ ከታሜሶል ኮሚኒኬሽን ጋር በጥምረት ማዘጋጀቱን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#awashbank #awashbirr #easterexpo2018 #ethiopia #digitalbanking #eticketing #addisababa #holidaymarket

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.