4 months ago
የኬንያ መንግስት በነዳጅ ምክንያት የስራ ሀላፊዎችን እያባረረ ነው
#ethiopia | በኬንያ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ በተደረገ ጥልቅ ምርመራ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ከስልጣናቸው እንዲነሱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተወሰነ። ይህ እርምጃ የተወሰደው በሀገሪቱ የነዳጅ ዘርፍ ላይ በተፈጸመ የኢኮኖሚ አሻጥር እና የሀሰት መረጃ ስርጭት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ከሃላፊነታቸው በአስቸኳይ ከተነሱት ባለስልጣናት መካከል፦
* መሐመድ ሊባን – የነዳጅ ዘርፍ ዋና ጸሐፊ
* ጆ ሳንግ – የኬንያ ፓይፕላይን ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ
* ዳንኤል ኪፕቶ ባርጎሪያ – የኢነርጂና ነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ይገኙበታል።
የኬንያ ፕሬዚዳንት የሥራ ኃላፊ ፌሊክስ ኬ ኮስኬይ እንደገለጹት፣ ባለሥልጣናቱ በሀገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ ክምችት አስመልክቶ የተሳሳተ መረጃ ሆን ብለው በማሰራጨት ህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እንዲፈጠር አድርገዋል። ይህ "የኢኮኖሚ አሻጥር" በታክስ ከፋዩ ህዝብ ላይ ከ500 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በላይ ኪሳራ ማስከተሉ ተረጋግጧል።
ወቅታዊው እርምጃ መንግስት በስትራቴጂካዊ የሀብት አቅርቦቶች ላይ የሚታዩ ብክነቶችንና ሌብነቶችን ለመከላከል የጀመረው ዘመቻ አካል መሆኑ ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #kenyanews #oilscandal #economicsabotage #eastafricaupdate #energysector #accountability

Comments