8 days ago
የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የኃይል ዘርፍ ትብብር
******************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገሪቱን የኢነርጂ ዘርፍ ወደ ላቀ የዲጂታል እና የዘመናዊነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ወሳኝ ውይይት ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካን ጋር አካሂዷል።
ውይይቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ በአሜሪካ መንግስት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል የተመራውን ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
በምክክሩ ላይ የኤሌክትሪክ ስርጭት አውታር መረብን (Grid) ማዘመን፣ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን፣ ስማርት ቆጣሪዎችን ማስፋፋት፣ ንጹህ ኢነርጂን ማልማት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን (EVs) ማበረታታት ዋነኛ አጀንዳዎች ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።
ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በውይይቱ ወቅት፣ ተቋማቸው ለደንበኞች ምቹ፣ ጠንካራ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈጠራንና ቴክኖሎጂን አቅፎ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የረጅም ዓመታት ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የልማት ፕሮጀክቶች እንደሚሸጋገር ያላቸውን ጽኑ እምነት መግለጻቸውን ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ሚስተር ማርክ ትራውንተር ሚቼል እና ልዑካን ቡድናቸው በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘመናዊነት እርምጃዎችን አድንቀው፣ የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ አስተማማኝነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋፋት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል።
#ethiopia #ethiopianelectricutility #energysector #cleanenergy #usethiopia

Comments