Logo
Getu Temesgen
በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ ለፍጻሜ ደረሰች
#ethiopia | ለ13ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ሞሮኮ ጋናን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሰች፡፡

ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ 90 ደቂቃውን አንድ አቻ አጠናቀዋል፡፡ ኡዝራዎይ ለሞሮኮ ንያምክያ ደግሞ ለጋና ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

አሸናፊውን ለመለየት በተጨመረው 30 ደቂቃ ግብ ባለመቆጠሩ በተሰጠው መለያ ምት ሞሮኮ 4 ለ 2 አሸንፋለች፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ በተከታታይ ለፍጻሜ የደረሰችበትን ውጤት አስመዝግባለች፡፡

እሑድ በሚደረገው ፍጻሜ ሞሮኮ ከ9 ጊዜ ሻምፒዮኗ ናይጄርያ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
#africa #ebcsport #morroco

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.