3 months ago
የማራካና ስታዲየሙ ልብ ሰባሪ ትዕይንት ለብራዚል
**************
ዓለም ዋንጫ አራት ዓመታቱን ጠብቆ በተመላለሰ ቁጥር ከሚታወሱ ክስተቶች አንዱ ይህ ነው። ብራዚልን ከ ኡራጓይ ያገናኘው የ1950 ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ።
በአንድ ስታዲየም ውስጥ ይህን ያህል ሰው ይታደማል ብሎ ለማሰብ የራቀ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ከብራዚላውያኑ የእግር ኳስ ታሪክ መቼቶች አንዱ የሆነው ማራካና የዚያን ዕለት ከ170,000 በላይ ሰዎችን ማስተናገዱ ይነገራል።
እንደውም ይህ ግምታዊ እንጂ ቁጥሩ ወደ 200,000 ሊያሻቅብ ይችላል ተብሎም ተፅፏል።
ያን ዕለት ሪዮ ዲጄኔሮ በማጀቷም በጎዳናዎቿም በተስፋ የጠበቀችውን የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ድሏን የጨበጠች ያህል በደስታ ተውጣለች። ተስፋን በቀላቀለ ደስታ። በዛ ጨዋታ ለ'ሴልሳኦዎ'ቹ ሻምፒዮን ለመሆን የአቻ ውጤት በቂያቸው ነበር።
በእርግጥም በሁለተኛው አጋማሽ ፍሪያካ ለብራዚል ያስቆጠራት ግብ ያን ሁሉ ጥበቃ ተጨባጭ፤ ተስፋዋንም አረጋጋጭ አስመስላ ነበር።
ሆኖም በደቂቃዎች ልዩነት ሁዋን አልቤርቶ ሺያፊኖ ያስቆጠራት የአቻነት ግብ የብራዚሎችን ሻምፒዮንነት የምታሳጣ ባትሆንም፣ የሰማያዊዎቹን ተስፋ አለምልማለች።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ 11 ደቂቃዎች ሲቀሩ አልሲደስ ጊጊያ ያስቆጠራት ግብ ሁሉንም ነገር ቀየረች። ማራካና ሰው የሌለበት ይመስል በጥልቅ ዝምታ ተዋጠ፤ ፀጥ ረጭ አለ።
ተጫዋቾች በሽንፈት ሜዳውን ለቀው ሲወጡ፤ ድፍን ሀገር ብዙ ጠብቆ ነበርና የሆነውን ባለማመን ሀዘኑን ይገልፅበት መንገድ ጠፋው። የሆነው ጉም የመዝገን ያክል የማይጨበጥ፤ አግኝቶ የማጣት ያክል መራራ ነበር።
ግዙፉ ማራካና ስታዲየም እግር ኳስ የተጠበቁት ብቻ ሳይሆኑ አንዳንዴ ከዓይን የማይገቡት፣ ግምትም የማይሰጣቸው ድል የሚነሱበት ስፖርት እንደሆነ እማኝ ሆነ። ከ76 ዓመታት በፊት የተከሰተው 'ማራካናዞ' የማራካናው ስብራት ዛሬም እየታወሰ ቀጥሏል።
ብራዚል በዚያ ልብ ሰባሪ ሽንፈት ወድቃ አልቀረችም። ስምንት ዓመታት ጠብቃ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን አነሳች። አምስት ጊዜም ደጋግማ አሸንፋ በምድር ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ የስኬት ምሳሌ ሆነች። እግር ኳስ በስማቸው ቢጠራ የማያንሱ እልፍ ክዋክብትን ለዓለም አበረከተች።
ዓለም ዋንጫ ከድል እና ሽንፈት ዜናዎች የሚሻገሩ ታሪኮችን ያጨቀ የትዝታ አውድማ፤ ወድቆ የመነሳትን ምሳሌ ገሀድ የሚያደርግ ትዕምርት ነው። በዘመን ሳይደበዝዝ፤ በጊዜ ርዝማኔ ሳያረጅ አሁንም ቀጥሏል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ #ebcsport #football #brasil

Comments