የመድፈኞቹ የ22 ዓመት ትጋትና ፅናት ያስገኘው የድል ደስታ በአዲስ አበባ
******
የለንደኑ መድፈኞች የ22 ዓመታት ረጅም የዋንጫ ጥበቃን በስኬት አጠናቀው የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነታቸውን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ልዩ የደስታ ማዕበል ተፈጥሯል።
የዚህን ታሪካዊ የታሪክ ምዕራፍ ወሳኝ ጨዋታ በትልቅ ስክሪን ለመታደም በርካታ ቁጥር ያላቸው የአርሰናል ደጋፊዎች በጊዮን ሆቴል አዳራሽ በጋራ የተሰበሰቡ ሲሆን ምሽቱም ስታዲየምን በሚያስንቅ የደጋፊዎች ጩኸት፣ መዝሙርና በከፍተኛ ስፖርታዊ ስሜት የታጀበ ነበር።
ይህንን ልዩ ምሽት ይበልጥ ማራኪ ያደረገው ደግሞ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የስፖርት ባለሙያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ከደጋፊው ጋር አብረው በመገኘት ደስታውን መጋራታቸው ነው፡፡
በተለይም ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የመጣው ታዋቂው ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ "ዴላን ፔጅ" በቦታው ተገኝቶ ይህንን አስደናቂ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፍቅርና ስሜት አብሮ ተካፍሏል።
በጊዮን ሆቴል የነበረውን ደማቅ ትዕይንት የታደሙት ደጋፊዎች ማራኪ ምስሎችንና ተንቀሳቃሽ ቪዲዮዎችን ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው በቀጥታ በማጋራት የአዲስ አበባን የአርሰናል ደጋፊነት ስሜት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተላልፈዋል።
መድፈኞቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በበላይነት አጠናቅቀው ዋንጫውን ከ22 ዓመታት በኋላ በክብር ተረክበዋል።
በብሌን ደምበሎ
#arsenalmustvisitethiopia #arsenal #premierleaguechampions #addisababa #dylanpage #ethiopianbroadcastingcorporation

2 months ago